ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

የኣውሮፓ ሕብረት መሪዎች ስደተኞችን በሚመለከት ከሰሜን አፍሪካ መሪዎች ጋር ስምምነት ለማድረግ ይፈልጋሉ፡፡

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ስደተኞችን በሚመለከት ከሰሜን አፍሪካ አገሮች ማለት ግብፅ፣ ቱኒዝያ፣ ሞሮኮና ሊቢያ ጋር ስምምነት ለመደራደር ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡ ይህ የሆነውም የአውሮፓ ሕብረት በአውስትርያ ሳልስበርግ በተባለችው ከተማ በ19 – 20 መስከረም ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በጀርመን አገር ጠቅላይ ሚኒስቴር አንጀላ መርክል፣ የቡድኑ ጥምረት ከሰሜን አፍሪካ አገሮች ከአውሮፓ  መንግሥታት ጋር ስምምነት በሚያደርግበት ወቅት ካሁን በፊት የተደረገው በአውሮፓ ሕብረትና በቱርክ መንግሥት መካከል የተደረገው ስለስደተኞች ስምምነት እንደ ሞዴል መውሰድ አለበት ብለዋል፡፡ ንግግራቸው በመቀጠልም ለዶቼ ቬለ የጀርመን ሚድያ ዉሎ አድሮ በአውሮፓ ሕብረትና በቱርክ መንግሥት መካከል እንደተዋቀረው ስምምነት ዓይነት ያስፈልገናልብለዋል፡፡

በአውሮፓና በቱርክ መካከል በ2016 በተደረገው የስደተኞች ውል መሠረት፣ በግሪክ የደረሱ ስደተኞች ለጥገኝነት ካላመለከቱ ወይም ደግሞ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ካላገኘ ወደ ቱርክ እንዲመለሱ የሚል ነው፡፡ የቱርክ መንግሥትም ለእነዚሁ 3.5 ሚልዮን ስደተኞችን ለመርዳት በርከት ያለ ቢልዮን ዩሮ እርዳታ ትቀበላለች፡፡

መርከል ለአጃንስ ፍራንሴ ሲናገሩ፣ የአውሮፓ ሕብረት በሜዲቴራንያን የስደተኞች መተላለፊያ መንገድ በተሻለ ሁኔታ ለመቆጣጠር  እንዲችል ከሌሎች የሰሜን አፍሪካ አገሮች ስምምነት ማድረግ ይገባዋል፡፡

ስምምነቱ በ2016 ከተፈረመ በኋላ፣ ስምምነቱ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመግባት በሰሜን አውሮፓና ጣልያን መካከል አደገኛ መንገዶች እንዲጠቀሙ ይገፋፋል የሚል ትችት ተተንብዮ ነበር፤ በአሁኑ ጊዜም ጭራሽ ለመዝጋት እየታየ ነው፡፡

የአውሮፓ ሕብረት ከሰሜን አፍሪካ አገሮች አስቀድሞ መደራደር ጀምረዋል፡፡ ባለፈው ሓምሌ ሕብረቱ ከሊቢያ ጋር እርዳታ፣ መርከቦችና የባህር ኃይል ሥልጠና ለመስጠት፣ በአንፃሩም የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂዎች ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩት ስደተኞችን ከጉዞአቸው በማቋረጥ፣ ከአደጋ በማዳንና ወደመጡበት እንዲመለሱ በማድረግ ረገድ እንዲሠራ ተስማምተዋል፡፡ እስከ አሁን ድረስ በ2018፣ የሊብያ የባህር ሃይል ጉዞኣቸውን በማቋረጥና ከአደጋ በማዳን 10,000 ስደተኞች ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ አድርጋለች፡፡

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ታስክና የአውስትርያው ቻንሰለር ሰባስቲያን ኩርዝም ከግብፁ ፕሬዚዳንት ዓብደል ፋታሕ ሲሲ በሜዲቴራንያን ሕገ – ወጥ ስደትን ለማርገብና አማራጭ ለመፈለግ በመስከረም ላይ ሁለተኛ ስብሰባ አድርገዋል፡፡

የአውሮፓ ሕብረት መሪዎች ከዓረብ ሊግ ጋር በሚቀጥለው ዓመት በየካቲት ወር ላይ እላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ተዘጋጅተዋል፡፡

ፎቶ፡ አለክሳንድሮስ ሚካኤልዲስ/Shutterstock. ሳልስበርግ፣ አውስትርያ 20 መስከረም 2018 አንጀላ መርከል መደበኛ ባልሆነው 28 መንግሥታት መሪዎች በተሰበሰቡበት ስብሰባ ላይ ለጋዜኞች የሰጡት መግለጫ፡፡