በቬንቲሚሊያ ማሸጋገርያ ጣቢያ ለአካለመጠን ያልደረሱ ሕፃናት ግብረ ሥጋ ለመፈፀም ተገድደዋል፡፡

መግለጫ፡ በጣልያን – ፈረንሣይ ማስተላለፍያ ስደተኞች ሕፃናት ግብረ ሥጋ እንዲፈፅሙ ተገድደዋል ሲል ሴቭ ዘ ችልድረን አሰታወቀ፡፡ ፎቶ፡ ጆናታን ሃይምስ/ሴቭ ዘ ችልድረን

በጣልያን አገር ስደተኞች ፈረንሣይ ለመሻገር ሳይወድዱ ወደ የግብረ ስጋ ግንኝነት ተግባር እየተገፋፉ ነው፣ ሲል ሴቭ ዘ ችልድረን የተባለው  ዓለም አቀፉ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አጋለጠ፡፡

ያንግ ኢንቪዝብል ኤንስለቭድ፡ በጣልያን ችልድረን ቪክቲምስ ኦፍ ትራፊኪንግ ኤንድ ሌበር ኤክስፕሎይቴሽንየተባለው ጥናት ሕፃናት በጣልያን ፈረንሣይ ጠረፍ ለሚገኙት አስተላላፊዎች የገንዘብ ፍላጎታቸው ለማርካት ሲሉ በተለይ በደቡብ ሰሃራዊ አፍሪካ ከሚገኙት ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናት ለግብረ ስጋ ግምኙነት እንደተዳረጉ ያስረዳል፡፡

በእነዚህ ጉዞዎች በተለይ ልጃገረዶች ተጎጂዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ልጃገረዶች በናይጄርያና ጣልያን መካከል ላለው እዳ ጉዞ እስከ 30 ሺ ዩሮ አላቸው፡፡ (ይህ ገንዘብ በጣም የተጋነነ ስለሚመስል እንደገና ቢታይ ጥሩ ነው) ጥቂቶቹም ቢሆኑ ምግብና መጠለያ ለማግኘት ሲሉ ለግብረ ሥጋ ይገደዱ ነበር፡፡

ራፍኤላ ሚላኖ፣ በሴቭ ዘ ችልድረን የኢጣልያ አውሮፓ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሚከተለው በለዋል፡ እነዚህ በጣም ወጣቶችና በተለይም በአደጋ ያሉ ልጃገረዶች ሲሆኑ ወደ ሰሜናዊ ጣልያን ጠረፍ ካለ አዋቂ አጃቢ በሌሎች የአውሮፓ አገሮች ከሚገኙት ዘመዶቻቸውና የሚያውቋቸው ሰዎች ለመገናኘት ለሚያደርጉት ሙከራ ያለስጋትና በሕጋዊ መንገድ ለመጓዝ የተነፈጉ ናቸው፡፡  

በኢጣልያ የጠረፍ ከተማ በሆነችው የቬንቲሚልያ ከተማ ላይ ሕገወጥ ጊዜያዊ ካምፖች ከተተከሉ በኋላ ሁኔታዎች እየከፉ መጥተዋል፤ ወደ ፈረንሣይ ለመሸጋገር ለስደተኞች ዋና መተላለፍያ እምብርት የሆነችው ቬንቲሚልያ በባለሥልጣኖች በሚያዝያ ወር ተወግዳለች፡፡

ሪፖርቱ እንደገለፀው ብዙዎች ሕፃናት በየጎዳናው በዝቅተኛ ሁናቴ፣ በምንም መልኩ በማይመረጥና አደገኛ አኳኋንተገድደው እንደሚኖሩ ነው፡፡

ችግሩ በፈረንሣይና ጣልያን ጠረፎች ብቻ አይደለም፡፡ በሪፖርቱ መሠረት ስደተኞች ሕፃናት በጣልያን አገር በሌሎች አከባቢዎች ማለት በሮም፣ በቨኔቶ፣ በአብሩዞ፣ በማርሸና በሳርዲኒያ በግብረ ሥጋ ይበዘበዙ እንደነበር ታውቋል፡፡

ቀደም ብሎ በሰኔ ወር ከኦክስፋም የተላለፈው ሪፖርት እንደጠቀሰው በ2017 ጣልያን ከደረሱት 17,337 91 መቶኛ ካለ አዋቂ አጃቢ የሄዱ ናቸው፡፡ ይህ አኀዝ በዚያው ዓመት ካለ አዋቂ አጃቢ በአውሮፓ አገሮች የደረሱትን የሚገልፅ ነው፡፡

በተጨማሪ በኦገስት 2017 እና በኤፕሪል 2018 ቬንቲሚልያን ተሻግረው ወደ ፈረንሣይ ከገቡት16,500 መካከል አንድ አራተኛው ሕፃናት እንደነበሩ ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡

TMP – 24/08/2018