ብዙ ስደተኞች ከሊብያ እንዲወጡ ከማድረግ ይልቅ ወደ እስር ቤቶች እንዲመለሱ እየተደረጉ ናቸው
ምንም እንኳን በሊብያ ያለው ግጭት እየቀጠለ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ስድተኞች በባህር ላይ በሚያደርጉት ጉዞ በሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ተይዘው በአገሪቱ ወደሚገኙ እስር ቤቶች እየተመለሱ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅፈት ቤት ወኪል አስታውቀዋል።
“ ስድተኞች በሊብያ የባህር ጠረፍ ከአደጋ ከዳኑ ወይም ከተያዙ በሃላ ከአገሪቱ እንዲወጡ ከሚደረጉ ይልቅ ወደ እስር ቤቶች የሚወረወሩትን አዳዲስ እስረኞች ቁጥር የበለጠ ነው” ሲሉ የተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ጉዳይ ፅፈት ቤት ቃል አቀባይ ባበር ብሎኽ በሰኔ 4 ማከስሾ ቀን በጀኔቫ በሰጡት አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።
በዚህ አመት ከመጀመርያዎቹ አራት ወራቶች ይበልጥ በግንቦት ወር ብቻ 1224 ስደተኞች በባህር ላይ በሚያደርጉት ጉዞ በሊብያ የባህር ጠረፍ ጣበቂዎች ተይዘው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ ተደርጓል።
“ በዚንታን ያለው ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው። የእስር ቤቶች ክፍሎች በጣም የተጨናነቁና በቂ ማናፈሻ ወይም በቂ አየር የማያስገቡ ናቸው። በእያንዳንዱ ማእከል መፀዳጃ ቤቶች ሞልተው እየፈሰሱ በመሆናቸው አስፈላጊ ጥገና ያስፈልጋቸዋል። በዚህ ምክንያት ሰገራና የቆሻሻ ክምር በእስር ቤቱ ክፍል ውስጥ ለብዙ ቀናት ስለማይነሱ ለአደገኛ የጤና ጠንቅ መነሻ ሆነዋል።”ሲሉ ባሉኽ ተናግረዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ጉዳይ ጽፈት ቤት በዚንታን ትሪፖሊ እስር ቤት ውስጥ ተይዘው የነበሪቱን 96 ስድተኞች እንዲለቀቁ አድርገዋል። የተለቀቁት እስረኞች አብዛኛዎቹ ከኤርትራ፣ኢትዮጵያና ሱማልያ ሲሆኑ ሁለት በቅርቡ የተወለዱ ህፃናትም ይገኝባቸዋል። ስደተኞች ከአገሪቱ ድህንነቱ በጠበቀ ሁኔታ እሰከሚወጡ ድረስ ወደ ጊዝያዊ መጠለያ እንዲዛወሩ ተደርገዋል።
“ የተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ምግብ፣ መጠልያ፣ የህክምና እርዳታ በተጨማሪም ስነ ልቦናዊና ማህበራዊ እገዛ እንዲሁም ልብሶች፣ጫማዎች፣የንፅህና ዕቃዎችና ብርድ ልብሶች እንዲያገኙ እያደረገ ነው። ስድተኞቹ ከአገሪቱ እስከሚወጡ ድረስ በመጠልያው ይቆያሉ። “ ሲሉ ባሎኽ ተናግረዋል።
በዚንታል ሌሎች 654 ጭገኝነት ጠያቂዎችና ስድተኞች እስከ አሁን ድረስ ይገኛሉ። ሲሉ ባሎኽ ተናግረዋል።
በሊብያ እስር ቤቶች ውስጥ ተይዘው የሚገኙት ስድተኞች በአገሪቱ ባሉት ግጭቶች ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው። ስድተኞች በቂ ምግብና ውሃ አያገኙም። የሕክምና አገልግሎት ስለማያገኙም በበሽታ መስፋፋት ምክንያት እየተጠቁ ናቸው ሲሉ የመገናኛ ዜዴዎች ዘግበዋል።
የተባበሩት መንግስታት የስድተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት ባደረገው አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ ስደተኞችን ጥገኝነት ጠያቂዎች ከሊብያ እንዲወጡ ለማድረግ እገዛ ማድረግ እንዳለባቸው ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ደጋግመው ጥሪ አቅርበዋል። ባሎኽ “ በማእከላዊ ሜዲትራንያን ከአደጋ የዳኑትና የተያዙ ሰዎች ወደ ሊብያ እንዳይመለሱ አዲስ ጥረት ያስፈልጋል።” በማለት አክለው ተናግረዋል።
በሊብያ ላይ ያለው አለመረጋጋት እየባሰ በመሄዱ ምክንያት ስድተኞች ወደ አውሮጳ የሚያጓጉዙ ጃልባዎች ቁጥር ላይ ተፅዕኖ አሳድረዋል። ይህም ከሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ጋር ስድተኞች በባህር ወደ አውሮጳ ለመሻገር የሚያደርጉት ጉዞ ለመግታት በመጀመር በብዙ ሺ የሚገመቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስድተኞች በሊብያ ያለረዳት እንዲቀሩና ደህንነቱ የተጠበቀ መውጫ መንገድ እንዲያጡ አድርጓል።
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት በሊብያ የሚገኙ የጥገኝነት ጠያቂዎች ስድተኞች እስር ቤቶች ወይም ደግሞ ማጎርያ ቤቶች እንዲዘጉ ጥሪዉን አስተላልፈዋል። በሰኔ ወር ያለረዳት የተቀሩትን 62 ስድተኞች ከሊብያ ወደ ሩማንያ 149 ስድተኞች ከትሪፖሊ ወደ ጣልያን እንዲሄዱ አድርጓል።
TMP – 07/06/2019
ፍቶ : ኪቲራል ሮክቡሪ/ሻተርስቶክ
Photo caption: በሺዎች የሚቆጠሩ ስድተኞች በሊብያ እስር ቤቶች ስፍራ ይግኛሉ
ፅሑፉን ያካፍሉ