በልብያ የሚገኙ ስደተኞች ባገሪቱ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ወደ አውሮጳ ለመድረስ የነበራቸው ተስፋ እየቆረጡ ናቸው

በሊብያ በጦር መሳርያ የተደገፈ ግጭት በመቀጠሉ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ በአገሪቱ ታስረው የሚገኙ ስድተኞች  ኤርትራውያን ጨምሮ  ስለድህንነታቸውና ወደ አውሮጳ ለመድረስ የነበራቸውን ተስፋ እየቆረጡ ናቸው።

6000 በላይ የሚገመቱ በሊብያ እስር ቤቶች  ውስጥ  የሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎች ስደተኞች ባለው ሁከት ሳብያ በአጥብቂኝ ሁኔታ እንደሚገኙ የሚድያ ዘገባዎች እየገለጡ ናቸው። በዘገባው መሰረት በእስር ቤቶች ከሚገኙ አንዳንድ ስድተኞች ምግብና ውሃ እንዳያገኙ የተደረጉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ጭቆና እየደረሳቸው ነው።

ለአንዳንድ በሊብያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ምንም እንኳን በሊብያ  የባህር ጠረፍ ግጭት ቢኖርም ድህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ወደ ጣልያን እንደሚያደርሱዋቸው በሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የተነገራቸው መሆኑን ማትዮ ቪላ የተባሉ የጣልያን አለም አቀፍ ፓለቲካዊ ጥናት ተመራማሪ ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜ ስድተኞች ባገሪቱ ካለው ብጥብጥ ለመሸሽ የሚያደርጉት የጀልባ ጉዞ  የሚያስተዳደሩት ሚልሻዎች ናቸው። እየባሰ ባለው ያልተረጋጋ ሁኔታ ጥቂት ጉዞዎች ብቻ እንዲኖሩ እያደረግን መሆኑን ቪላ ገልፀዋል።

ሚልሻዎች በጦርነት ተጠመዱ ማለት ጥቂት ጃልባዎች ስድተኞችን ይዞው ይጓዛሉ ማለት ነው። ይህም ለስድተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች መጥፎ ሁኔታ ነው። ምክንያቱም ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ በአስቸኳይ እንዲወጡ ይፈልጋሉ’’ ሲሉ ቪላ ተናግረዋል።

ብዙ ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች በአገሪቱ መውጫ ለሌላቸው ስድተኞች  እየበዘበዝዋቸው ይገኛሉ።አሁን ለሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ጥሩ ግዜ ነው። አሁን ጊዝያቸው ወይ ወቅታቸው ነው’’ በማለት አንድ ኤርትራዊ ስድተኛ ተናግረዋል።

በአቡስሊም እስር ቤት ታስሮ የሚገኝ ኤርትራዊወዴት እንደምንሄድ አናውቅም ያለ ጠባቂዎች ነን ለማለት ይቻላል። በሁለት ጠባቂዎች  ብቻ ናቸው የቀሩት እነሱም ትተውን ይሄዳሉ። ጦርነቱ እየቀረበ ነው’’ በማለት ተናግረዋል።

ስደተኞች ታላቁ ፍርሃታቸው በሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ታፍነው እንዳይወሰዱ ሲሆን ይህም ጥበቃ ስለማይደረግላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከሁሉም በላይ የኛ ስጋት የሆኑት ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ናቸው። በዚህ አገር የባርያ ንግድ አለ። ወደ ቦታቸው ወስደው ገንዘብ ይጠይቁናል። ገንዘብ ከሌለህ ይደበድቡሃል። ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ። በአንዳንድ ቦታዎች ወንደቹም ይደራሉ’’ በማለት ኤርትራዊው ስደተኛ ለአልጀዚራ ተናግረዋል።

በቅርቡ አመታት የአውሮጳ መንግስታት በሊብያ በኩል ወደ አውሮጳ ለመድረስ የሞሞኩሩትን ስደተኞች ለመግታት ጠንካራ የስደት ፓሊሲዎች አስተዋውቀዋል። ለምሳሌ ጣልያን ከጃልባ አደጋ  የዳኑቱን ስደተኞች ወደ ጣልያን እንዳይወርዱ ለማድረግ  ዝግ ወደቦች’’  የሚል ፖሊሲ አቅርባለች ወይም አስተዋውቃለች።  2018 .. በሜዲትራንያን በኩል ወደ ጣልያን ለመግባት የሞኮሩትን  1500 የሚሆኑ ስደተኞች በሊብያ የባህር ጠረፍ ጨባቂዎች ተይዘው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ ተደርጓል።

በዚህ አመት ከጥር እስከ መጋቢት ባሉት ወራት ውስጥ ከሊብያ ፣ቱኒዝያና አልጀርያ ተነስተው ወደ አውሮጳ ለመድረስ የቻሉት 500 በታች ሰዎች መሆናቸውን የአውሮጳ  ድንበር ኤጄንሲ ፍሮንቴክድ አስታውቋል።

በዚህ አመት ሜዲትሪያንያን ለመሻገር የሞኮሩት 409 ሰዎች የሞቱ ወይም የጠፉ መሆናቸውን አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት /Iom / አስታውቋል። 

TMP – 16/05/2019

ፎቶ: ሹተርስቶክ ኮም

በሺዎች የሚቆጠሩ በሊብያ የሚገኙ ስደተኞች ባገሪቱ ባለው ብጥብጥ ምክንያት በአጥብቂኝ አደጋ ላይ ይገኛሉ።