ጣልያን በሰሜን አፍሪካ 1 ቢልዮን ዩሮ በሥራ ሊያውል ነው፡፡

የጣልያን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር፣ ማቴዎ ሳልቪኒ፡፡ ፎቶ፡ /ቫይስ ኒውስ/

ጣልያን ለሰሜን አፍሪካ አገሮች 1 ቢልዮን ዩሮ የልማት ፈንድበሥራ ላይ ለማዋል ወይም ኢንቬስት ለማድረግ እቅድ እንዳላት፣ የጣልያን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር፣ ማቴዎ ሳልቪኒ ከአገር ውስጥ Sky TG23. ከተባለው የዜና ማእከል ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አሳወቁ፡፡

ወደ አውሮፓ የሚያቀኑት ስደተኞች የሚነሱባቸውና ስደተኞችን የሚያስተላልፉ አገሮች ከዚሁ ከሚሰጠው ገንዘብ ተጠቃሚዎች ይሆናሉ፡፡ ሚኒስትሩ ባለፈው ኦገስት/ ነሓሴ ወር መጀመርያ ላይ እንዳሉት ገንዘቡ በየአገሮቹ የእርሻ፣ ዓሣ እርባታና ንግድ ክፍሎች ላይ እንደሚውል አሳስበዋል፡፡

ዓላማችን በደቡብ ያሉትን ጠረፎች ለመቆጣጠር . . . እኔን እንደሰይጣን የሚያዩኝን መልስ ለመስጠት፣ በችግርና በመከራ ለሚገኙት በመቶ ሺዎች ህዝብ በሥራና በኢኮኖሚ ድጋፍ ለመስጠት፣ ቢያንስ 1 ቢልዮን ዩሮ ፕሮጄክት ኢንቬስትሜንት ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ነንሲል ሳልቪኒ ተናገረ፡፡ ሳልቪኒ ንግግሩን በመቀጠል በስፋት መታየት ያለበት የተወሳሰቡና እንደ የወንጀል ቀለቤቶችና ሰደት የመሳሰሉት የደህንነት አከራካሪ ጉዳዮችን የመዋጋት ሁኔታ ነው ብሏል፡፡

ጣልያን ከሰሜን አፍሪካ የሚመጡት ሕገ-ወጥ ስደተኞችን ላለመቀበል ጠንካራ አቋም እወሰደች ናት፡፡ እ.አ.አቆ ከ2016 ጀምሮ አገሪቷ በሜዲቴራንያን ማሰተላለፊያዎች በኩል ቍጥራቸው ከጎሬቤት አገሮች የበለጠ ስደተኞች ተቀብላለች፡፡ ጣልያን ለዚሁ አፀፋዊ መልስ ስትሰጥም፣ ከአደጋ የዳኑት ስደተኞችን ይዘው የሚመጡት መረከቦች ላይ ወደቦቿን የመዝጋት እርምጃ ወስዳለች፡፡

ወደቦችን መዝጋትናሕገወጥ ስደተኞችን መልሶ ወደ ሰሜን አፍሪካ መላክ በቂላይሆን ይችላል ብሎ ሳልቪኒ ንግግሩን ሲቀጥል በተጨማሪም ስደተኞች በሚልኩት አገሮች ላይ የእድገትና የሥራ እይታ መፍጠር አስፈላጊ ነውብሏል፡፡

ሳልቪኒ በወንጀል የተመዘገቡ ስደተኞች ጥገኝነት የመጠየቅ መብታቸው የሚያሰርዝ አዲስ ሕግ እንዲያወጣ የኢጣልያ ፓርላማን እንደሚያሳምን ተናገረ፡፡ በተጨማሪም የአውሮፓ ሕብረት ከአፍሪካ አገሮች ጋር ወደፊት በሚደረጉት የንግድ ማደራጀት ሥራ ላይ ወደ አገሩ ተመልሶ ይላካልየሚል ሐረግ መጨመር እንዳለበት ሳልቪኒ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪ የሚነስቴሩ ፅ/ቤት ከኢንተርናሽናል ሰንተር ፎር ማይግሬሽን ፖሊሲ ዴቨሎፕሜንት ጋር በመሆን፣ ከአውሮፓ ሕብረት ኢመርጀንሲ ትረስት ፈንድ ፎር አፍሪካ ሥር ሆኖ ከስደት ጋር በተያያዘ ፕሮግራም የሚውል 90.5 ሚልዮን ዩሮ በቅርቡ እንዳገኘ በመግለፅ፤ ሞሮኮ፣ ቱኒዝያና ሊብያ እንደሚጎበኝ ሳልቪኒ ተናግሮአል፡፡ ፕሮግራሞቹ የታሰቡት የእነዚህ አገሮች የጠረፍ አስተዳደርና የድንገተኛ አደጋ ማስተዳደር ችሎታዎች ለማሻሻል ነው፡፡

600,000 በላይ የሆኑት አፍሪቃውያን ስደተኞች እ.አ.አቆ ከ2013 ጀምሮ በጣልያን ጠረፎች እንደደረሱ ይታመናል፡፡ ከነዚሁ ስደተኞች 80% የሚሆኑት አሁንም በአገሪቱ እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡

TMP – 22/08/2018