በሊብያ የማቆያ ማእከላት ያለ የስደተኞች ቁጥር በእጥፍ ጨመረ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ እንደገለፀው በዚህ ሶስት ወር ውስጥ በሊብያ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት ያለ የስደተኞች ብዛት በዕጥፍ መጨመሩን ገልፀዋል።
ህገ ወጥ ስደተኞች የጫኑ የወንበዴ ጀልቦች በሊብያ እና ጣልያን አድርገው የአውሮፓን መሬት ለመርገጥ በሚደረገው ጉዞ ምክንያት ሊብያ ውስጥ በተለያዩ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት የነበረ የስደተኞች ቁጥር 2018 ከገባ ወዲህ ከ 5,000 ወደ 9,300 ማሻቀቡን ተገልፀዋል። ይህ በንእዲህ እንዳለ 11,980 ስደተኞች ሜድትራንያን ባህር በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመድረስ ጉዞ የጀመሩ ስደተኞች ደግሞ ወደ ሊብያ እንዲመለሱ ተደርገዋል።
በአለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም፤ አይኦኤም የሊብያ ቃል አቀባይ ክሪስትኒ ፒተር እንዳሉት “20 የማቆያ ማእከላት አገልግሎት ይሰጣሉ” በቅርቡ ከ “ከሊብያ ባለ ስልጠናት ከተደረገ ስምምነት በኋላ ማለት ነው።” ቀደም ብለው ይወጡ የነበሩ መረጃዎች እንደምያሳዩት ግን የነበሩ ማእከላት ከ34-35 መሆናቸውን ነው። አንዳንዶች ደግሞ ከ42 በላይ ማቆያ ማእከላት እንዳሉ ይናገራሉ። “ከእነዚህ ማእከላት አብዛኞቹ በሊብያዋ መዲና ትሪፖሊ ከተማ ውስጥ ይገኛሉ” ብለዋል ፒተር።
“ስደተኞቹ በዋነኝነት የሚወሰዱት ወደ አምስት የማቆያ ማእከላት ነው።” ከልክ ባለፈ መልኩ” ብለዋል ፒተር። እንደ ፒተር አባባል ከሆነ የሰብአዊነት ጉዳዮች ክፉኛ እየተበላሹ ነው። አያይዘውም “የችግሩ መጠን ለመገመት ይቻል ዘንድ አሁን በትሪፖሊ ያለ የሙቀት መጠን ከ35-40 ድግሪሴልስ ደርሰዋል።” ብለዋል ፒተር።
በሊብያ ይሄን አይነቱ የስደተኞች ቁጥር መጨመር ምክንያት ምን ይሆን ተብለው የተጠየቁት በአይኦኤም የሊብያ ቺፍ ሚሽን የሆኑት ኦቶማን በልበሲ እንደሚሉት “ህገ ወጥ የሰዎች ደለላ ከምን ጊዜም በላይ መጠንከራቸው እና መደራጀታቸው” እንደምክንያት አስቀምጠዋል። “ደግሞም ወደ አውሮፓ የሚደርሱ ስደተኞች ጥቂት መሆናቸው አልያም ጀልባ መጠቀማቸው የምያሳየው የስደተኞች ቁጥር መቀነስን አይደለም። ይልቁንስ በተቃራኒው ነው። ታግተዋል ማለት ነው።” ይላሉ።
አይኦኤም እንዳስቀመጠው አሁን በሊብያን ሀገር ውስጥ ወደ 662,000 የሚጠጉ ስደተኞች እንዳሉ ታውቀዋል። ይህ የምያሳየው ደግሞ በትንሹ ከበላፈው ዐመት የ40,000 ጭማሪ አለው ማለት ነው። አንድ አስረኛ ከዚህ ሁሉ ስደተኛ ደግሞ ድጋፍ የሚፈልጉ አካላት (ማይኖሪቲ) ናቸው።
አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት፤ አይኦኤም ጨምሮ እንዳለው በዚህ አመት ውስጥ ባህርን በማቋረጥ የአውሮፓ ምድር የረገጡ ስደተኞች ቁጥር 50,872 ሲሆን ከግማሽ በታች የሆኑት ማለትም 109,746 የሚሆኑ ስደተኞች ባለፈው ዐመት ጁላይ አጋማሽ ላይ የገቡ ናቸው። በ2016 በተመሳሳይ ወቅት 241,859 ስደተኞችን የአውሮፓ ምድርን ረግጠዋል።
“በሊብያ የባህር ግዛት ውስጥ ያለ የሞት መጠን አሁንም ያለማቋረጥ እየጨመረ ነው” ብለዋል በልቢስ። “ሜድትራንያን በማቋረጥ ወደ አውሮፓ በሚደረግ ጉዞ፤ ህግ አስከባሪ አካል ሳይመጣባቸው በፊት ህገ ወጥ ደላሎቹ ስደተኞቹን በማሰቃየት ይዘርፍዋቸዋል” በልበሲ እንዳለው።.
ከ2014 ጀምሮ እስካሁን ባለ ሪከርድ መሰረት ጁን 2018 ላይ ወደ ጥልያን የገቡትን 3,136 ስደተኞች መሰረት በማድረግ ሲታይ ይህ ቁጥር ትንሹ የስደተኞች ቁጥር ተብሎ ተይዘዋል። ወደ ጣልያን ሃገር የሚገቡ ስደተኞች አሁን በጣም ቀንሰዋል። በተለይም ጁን ወር ዝቅተኛው ሪኮርድ ይዘዋል። በጁን ወር ብቻ 564 ስደተኞችን እንደሞቱ ወይም የገቡበት ሳይታወቅ መቅረቱም ተዘግበዋል።
TMP – 13/08/2018
የፎቶ ምስጋና፡ አይኦኤም፡ ስደተኞችን በአይኦኤም ሰራተኞች ሲመዘገቡ
ፅሑፉን ያካፍሉ