ሊብያ ውስጥ ስደተኞች ለትርፍ ሲባል ታግቷል ከባህር ውስጥ ይልቅ በየብስ ጉዞ ህይወታቸው የሚያልፉ ስደተኞች ይበዛሉ። በሁለቱም አገሮች መካከል ያለው ድንበር የተዘጋ ቢሆንም ኤርትራውያን አሁንም ወደ ኢትዮጵያ መሸሻቸውን አላቋረጡም ጣልያን ፤- በባህር ላይ ተገኝተው ወደ ሊብያ እንዲመለሱ በሚገደዱ ስደተኞች ላይ ከሊብያ ጋር የነበራት ስምምነት አድሳለች ኢትዮጵያ ፤ ለስደተኞችና ለዜጋዋ እኩል እድል የተረጋገጠባት አገር

በፈረንሳይ እና እንግሊዝ ከቤተ ሰብ ጋር ለመኖር የምያስችለኝ ማመልከቻ ማስገባት እችላለሁ?

በዳብሊን ግፍ መሰረት ቤተሰቦችን ማገናኘት የተለያዩ መመዘኛ ነጥቦች ይጠቀማሉ።

ለቤተሰቦችና በእድሜ ለደረሱ

ከቤተሰቦችህ አንዱ በደብሊን አገር ተመዝግቦ ከሆነ ያንተ የጥገኝነት ጥያቄ እንዲታይልህ ማቅረብ የምትችለው በዛው ሃገር ብቻ ነው። ከቤተሰቦች ጋር የማገናኘት ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ ከቤተሰቦችህ ጋር መገናኘት እዛው ሆነህ የጥገኝነት ማመልከቻህን መከታተል ትችላለህ። ለምሳሌ ለፈረንሳይ አገር ጥገኝነት ከጠየቅክና ለባለስልጣናት ያንተ የቤተሰብ አባል ኢንግሊዝ አገር የሚኖር መሆኑ ከነገረክ የፈረንሳይ ባለስልጣናት ለኢንግሊዝ አገር ያንተን ጥያቄ እንሲያጠኑት ይጠይቃሉ። ከቤተሰቦችህ አባላት አንዱ (ሚስትህ ወይም ልጅህ) የጥገኝነት ጥያቄ አቅርቦ የመጀመርያ ደረጃ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያለ ከሆነ ወይም የጥገኝነት ፈቃድ ወይም ሰብአዊ ከለላ በኢንግሊዝ አገር ከተሰጠው የኢንግሊዝ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄህን ለመመርመር ሓላፊነት ካለው ፤ ይህም የቤተሰቡ ቁርጠኝነት ማሳየት ከተቻለ። የኢንግሊዝ መንግስትም በልዩ ሁኔታ ልዩ ውሳኔ የአንድ ቤተሰብ አባላት አንድ ላይ መኖር እንዳለባቸው እንደ መነሻ በመውሰድ መወሰን ይችላል።

አሳዳጊ (ሞግዚት) የሌላቸው ህፃናትን በሚመለከት

ቤተሰቦችን የማገናኘት እድል ተግባራዊ የሚሆነው አንድ አሳዳጊ (ሞግዚት) የሌለው ህፃን አዛው የሚኖርበት አገር በአውሮፓ ሀብረት አባል ሃገር ጥገኝነት የጠየቀ ከሆነ ብቻ ነው። በፈረንሳይ ውስጥ የሚኖሩ ህፃናት ጥገኝነት መጠየቅና ድጋፍ ማግኘት የሚችሉት አዛው ነው። አሳዳጊ (ሞግዚት) የሌላቸውና ጥገኝነት ለፈርንሳይ መንግስት ጥያቄ ካቀረቡ በኢንግሊዝ አገር ወይም በሌላ የአውሮፓ ህብረት አባል አገር የቤተሰብ አባል እንደሚኖር ለፈረንሳይ መንገር አለባቸው። የፈረንሳይ ባለስልጣናት ለዛች አገር ጥያቄውን ለማጣራት ሃላፊነት እንድትወስድ ሊጠይቁ ይችላሉ። የቤተሰቡ ግንኙነትም የሚያሳይ ዝርዝር ማስረጃም ማቅረብ አለባቸው። ወደ ኢንግሊዝ አገር ለመዛወር ብቁ ለመሆን P.T.O ህፃኑ ወላጅ ወይም አሳዳጊ (ሞግዚት) ፣ ወንድም (እህት) ፣ አጎት (አክስት) ፣ አያት ኢንግሊዝ አገር ውስጥ መኖር አለበት። የቤተሰቡ አባል ደግሞ በኢንግሊዝ አገር በህጋዊ መንገድ የሚኖር መሆን አለበት ። ይህም ጥገኝነት ጠይቀው በሂደት ላይ ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ ። አክስት ፣ አጎት ወይም አያት ህፃኑን በሚገባ ማሳደግና መንከባከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። ሰው የሌላቸው ህፃናት በእንግሊዝ ሀገር ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ከተፈለገ ቤተሰቦቻቸው በእንግሊዝ ሀገር ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል። ይህ አሳይለም ጠያቂዎች ቢሆንም ችግር የለውም። ይሁን እንጂ እነዚህ አክስት፣ አጎት፣ አልያም ተመሳሳይ ቤተ ሰብ ሊሆን የሚችል ሰው ልጅ የማሳደግ አቅም እንዳለው ሊረጋገጥ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።

ለሌላ ያካፍሉ

የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ...
ተጨማሪ ያንብቡ

በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ...
ተጨማሪ ያንብቡ

የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ...
ተጨማሪ ያንብቡ