ድህንነቱ የጠበቀ እና ህጋዊ አማራጭ

እና ህጋዊ አማራጭ
በዙ ስደተኞች በህገ ወጥ መንገድ የሚሄዱት ብቸኛው መንገድ እሱ ነው ብለው ስለምያምኑ ነው። ይሁን እንጂ በህገ ወጥ መንገድ ለመውጣት ከመወሰንዎ በፊት ደግሞ ምንም ዋስትና በሌለውመንገድ ከመሄድዎ በፊት ያሉት ህጋዊ አማራጮችን ቢያዩ ይመከራል። ህጋዊ ከሚባሉ አማራጮች አሳይለም መጠየቅ፣ ቤተሰብ እንዲሁም በፈቃድ መመለስ ይገኙበታል።

 

በሀገርዎ ጥቃት ደርሰብዎት ከሆነ የወጡት የአለም አቀፍ ትብብር የማግኘት መብት አለዎት። በመሆኑም የአሳይለም ጥያቄ ተሎ እንድያልቅልዎት ከፈለጉ በአውሮፓ ውስጥ ያሉ ሬጂናል እና አለም አቀፍ ዝርዝር ህጎች የሚፈቅደው ሰነድ በሚገባ መሙላት ያስፈልጋል።   

ወደ አውሮፓ በሚደረግ የስደት ጉዞ አንዱ ስደተኞችን ጫና የምያሳድር ህግ “ዱብሊን ረጉሌሽን” የሚባለው ህግ ነው።  ይህ ህግ እንደሚለው ስደተኞች የአሳይለም ጥያቄአቸውን መጀመርያ ማቅረብ ያለባቸው መጀመርያ ወደገቡበት የአውሮፓ ሀገር ነው። ለምሳሌ ፈረንሳይ ሀገር ለመድረስ መጀመርያ የረገጡት ሀገርሌላ የአውሮፓ ሀገር ከሆነ እና አሳይለም የተጠየቁት ፈረንሳይ ከሆነ ወደ ገቡበት የመጀመርያው ሀገር እንዲመለሱ ይደረጋል።

ማነኛውም ስደተኛ ወደአውሮፓ እንደገባ በቀጥታ አሳይለም መጠየቅ ያለበት የገባበት ሀገር ላይ ነው። አሳይለም የጠየቀበት የሀገር ቤት ጉዳይ ወደ ሌላ ሀገር እንዲሄድ የሚያስገድድ ከሆነም በስርዓቱ መሰረት የሚሄድ ይሆናል።   

በፈረንሳይ እና በእንግልዝ ሀገር አሳይለም ሲጠይቁ ህጋዊ ወኪል እና አስፈላጊ ከሆነም አስተርጓሚ መያዝ ያስፈልጋል።  ከስራ ውጪ እንደሆኑ ስለሚታወቅ ለአኮሜዴሽን እና የትምህርት ወጪዎች የሚውል የተወሰነ የፋይናንስና ተዛማጅ እርድታ ያገኛሉ።    

የአሳይለም ጥያቄዎት ተቀባይነት ካገኘ ለተወሰነ ጊዜ የመኖር እና የመስራት ፈቃድ ይሰጠዎታል። ቋሚ የመኖርያ ፈቃድም ተከትሎ ይመጣል።  

በፈረንሳይ ሀገር ለሚደረገው የአሳይለም ጥየቄ የምያስፈልጉ ቅድመ ተከተል ስራዎች :

  • በጀመርያ የቅድመ ምዝገባ ማመልከቻ በገቡበት መስመር   ስፓዳ (SPADA) እየተባለ በሚጠራው የመጀመርያው ስደተኞችን መቀበያ ማእከል መመዝገብ ያስፈልጋል። በኢልዲ ፍራንስ (Île-de-France) ከሆነ ያሉት  ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉት ቀናት ውስጥ ከ 4 ሰዓት ጥዋት እስከ 9፡30 ከስዓት ባለ ጊዜ ውስጥ ወደ 01 42 500 900 በመደወል ወረፋ ማስያዝ ይቻላል።
  • ለስብሰባ ወደ ጉዳ (GUDA) ይጠራሉ። የአሳይለም ማመልካችም ይሞላሉ።  
  • ከስብሰባው በኋላ ከፈረንሳይ የኢመይግሬሽን እና ኢንተግሬሽን ቢሮ  (OFII) ከሚመጣ ሰው ጋር በአሳይለም ጥየቃ ሂደቱ ሊኖሩ ስለሚገባቸው ዝርዝር ነገሮች ይወያያሉ።   
  • ጉዳ ላይ ከተደረገ ስብሰባ በኋላ ባሉት 21 ቀናት ውስጥ ማመልከቻዎትን  በፈረንሳይ የስደተኞች ጥበቃና የሀገርአልባ ሰዎች ጉዳዮች ቢሮ (OFPRA) ፋይል መደረግ አለበት።  

የPADAs አድራሻ እዚሁ ማግኘት ይቻላል here.

በእንግሊዝ ሀገር ለሚደረገው የአሳይለም ጥየቄ የምያስፈልጉ ቅድመ ተከተል ስራዎች :

  • እንደገቡ የስክሪኒግ ሂደት እንዲፈፀምልዎ ከእንግልዝ ኢሚግሬሽን ኦፊሰር ጋር ይገናኛሉ። ወይም የአሳይለም ጥያቄዎትን በመልካም መንገድ ከሄደ ወደ 020 8196  4524 በመደወል በማነኛውም የስክሪን ኦፊስ ውስጥ እንዲመዘገቡ ይሆናል። የሚደዉሉት ከሰኞ እስከ ሐሙስ በስራ ሰዓት ማለትም ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጥዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡45 እንዲሁም ዓርብ ከ ጥዋቱ 3 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡40 ባለ ጊዜ ውስጥ ይሆናል።   
  • ጥያቄዎትን በስክሪን ግዜ ያቀርባሉ።
  • ከዛ በኋላ ኬዝዎትን ወደ ኬዝ ማናጀር ተላለፎ የአሳይለም ምዝገባ ካር  (ARC) ይሰጥዎታል።
  • የመረጃ ፎርም ማለትም ‘preliminary information questionnaire’ ይሰጥዎት እና ሞልተው በተፈለገው ግዜ ውስጥ ያስረክባሉ።   
  • ከኬዝ ማኒጄሩ ጋ ቃለ መጠይቅ ይኖሮዎታል። ማኒጄሩ ዝርዝር አካሄዱን ይነግሮዎታል። በመጨረሻም ራስዎን ውሳኔ ላይ ይደርሳሉ።

በጥገኝነት ጥያቂ የአውሮፓ ህብረት አካሄድና አያያዝ ጉዳይ የሚሰራ ሕግ ነው፡፡ ያ ሕግ አንድ ጥገኝነት ጠያቂ ስድተኛ ለመጀመርያ ግዜ የረገጣት የአውሮፓ አገር ሃላፊነት መሆኑን ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ስድተኛ ለመጀመርያ ግዜ ገብቶ ጥገኝነት ወደ ጠየቀላት አገር እንዲመለስ ይደረጋል፡፡ የደብሊን ሕግ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች በመረጡበት የአውሮፓ አገር የጥገኝነት ጥያቄአቸው እንዲታይ የሚፈቅድ አይደለም፡፡ ጥገኝነት ጠያቂ ጥገኝነት በጠየቀበት አገር በመረጠው አገር ወይም ከተማ እንዲኖሩ ያ ሕግ አይፈቅድም፡፡ ኦስትራልያ፣ቡልጋርያ፣ክሮኤሽያ፣ቆጵሮስ፣ቼክ ሪፓብሊክ፣ዴንማርክ፣ኢስቶንያ፣ፊንላንድ፣ፈረንሳ፣ጀርሞን፣ግሪክ፣አይስላንድ፣ሃንጋሪ፣አየርላንድ፣ ጥልያን፡ ላቲቭያ፡ ልትወንያ፡ ሌችተንስተይን፡ ላግዘንበርግ፡ ማልታ፡ ሆላንድ፡ ኖርወይ፡ ፖላንድ፡ፖርቱጋል፡ ሩሜንያ፡ ስሎቫክያ፡ስሎቨንያ፡ ስጳኛ፡ ሽወደን፡ ስዊዘርላንድና ብሪጣንያ ለደብሊን ሕግ የሚከተሉና የሚሰሩበት የአውሮፓ ህበረት አገራት ናቸው፡፡

በዳብሊን ግፍ መሰረት ቤተሰቦችን ማገናኘት የተለያዩ መመዘኛ ነጥቦች ይጠቀማሉ።

ለቤተሰቦችና በእድሜ ለደረሱ

ከቤተሰቦችህ አንዱ በደብሊን አገር ተመዝግቦ ከሆነ ያንተ የጥገኝነት ጥያቄ እንዲታይልህ ማቅረብ የምትችለው በዛው ሃገር ብቻ ነው። ከቤተሰቦች ጋር የማገናኘት ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ ከቤተሰቦችህ ጋር መገናኘት እዛው ሆነህ የጥገኝነት ማመልከቻህን መከታተል ትችላለህ። ለምሳሌ ለፈረንሳይ አገር ጥገኝነት ከጠየቅክና ለባለስልጣናት ያንተ የቤተሰብ አባል ኢንግሊዝ አገር የሚኖር መሆኑ ከነገረክ የፈረንሳይ ባለስልጣናት ለኢንግሊዝ አገር ያንተን ጥያቄ እንሲያጠኑት ይጠይቃሉ። ከቤተሰቦችህ አባላት አንዱ (ሚስትህ ወይም ልጅህ) የጥገኝነት ጥያቄ አቅርቦ የመጀመርያ ደረጃ ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያለ ከሆነ ወይም የጥገኝነት ፈቃድ ወይም ሰብአዊ ከለላ በኢንግሊዝ አገር ከተሰጠው የኢንግሊዝ መንግስት የጥገኝነት ጥያቄህን ለመመርመር ሓላፊነት ካለው ፤ ይህም የቤተሰቡ ቁርጠኝነት ማሳየት ከተቻለ። የኢንግሊዝ መንግስትም በልዩ ሁኔታ ልዩ ውሳኔ የአንድ ቤተሰብ አባላት አንድ ላይ መኖር እንዳለባቸው እንደ መነሻ በመውሰድ መወሰን ይችላል።

አሳዳጊ (ሞግዚት) የሌላቸው ህፃናትን በሚመለከት

ቤተሰቦችን የማገናኘት እድል ተግባራዊ የሚሆነው አንድ አሳዳጊ (ሞግዚት) የሌለው ህፃን አዛው የሚኖርበት አገር በአውሮፓ ሀብረት አባል ሃገር ጥገኝነት የጠየቀ ከሆነ ብቻ ነው። በፈረንሳይ ውስጥ የሚኖሩ ህፃናት ጥገኝነት መጠየቅና ድጋፍ ማግኘት የሚችሉት አዛው ነው። አሳዳጊ (ሞግዚት) የሌላቸውና ጥገኝነት ለፈርንሳይ መንግስት ጥያቄ ካቀረቡ በኢንግሊዝ አገር ወይም በሌላ የአውሮፓ ህብረት አባል አገር የቤተሰብ አባል እንደሚኖር ለፈረንሳይ መንገር አለባቸው። የፈረንሳይ ባለስልጣናት ለዛች አገር ጥያቄውን ለማጣራት ሃላፊነት እንድትወስድ ሊጠይቁ ይችላሉ። የቤተሰቡ ግንኙነትም የሚያሳይ ዝርዝር ማስረጃም ማቅረብ አለባቸው። ወደ ኢንግሊዝ አገር ለመዛወር ብቁ ለመሆን P.T.O ህፃኑ ወላጅ ወይም አሳዳጊ (ሞግዚት) ፣ ወንድም (እህት) ፣ አጎት (አክስት) ፣ አያት ኢንግሊዝ አገር ውስጥ መኖር አለበት። የቤተሰቡ አባል ደግሞ በኢንግሊዝ አገር በህጋዊ መንገድ የሚኖር መሆን አለበት ። ይህም ጥገኝነት ጠይቀው በሂደት ላይ ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ ። አክስት ፣ አጎት ወይም አያት ህፃኑን በሚገባ ማሳደግና መንከባከብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። ሰው የሌላቸው ህፃናት በእንግሊዝ ሀገር ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ከተፈለገ ቤተሰቦቻቸው በእንግሊዝ ሀገር ህጋዊ የመኖርያ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል። ይህ አሳይለም ጠያቂዎች ቢሆንም ችግር የለውም። ይሁን እንጂ እነዚህ አክስት፣ አጎት፣ አልያም ተመሳሳይ ቤተ ሰብ ሊሆን የሚችል ሰው ልጅ የማሳደግ አቅም እንዳለው ሊረጋገጥ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።

ብዙ ስደተኞች የፈረንሳይን ምድር ለመርገጥ በብዙ መከራና ስቃይ ያልፋሉ። ይሁንና እዛ ከደረሱ በኋላ የምያገኙት የህይወት እውነታ ሌላ ይሆናል።  ከጠበቁት በታችም ይሆናል።

በእንደዚህ አይነት ሁነት ከሆነ ያሉት፡ እናም ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ከፈለጉ የሚከተሉት ጥቅማጥቅሞች ያገኛሉ።

  • ፋይናንሳዊ እና ሎጂስቲካዊ ድጋፎች ያገኛሉ። ለምሳሌ ነፃ ትኬት እና ተያያዥ ድጋፎች ይደረግሎታል።  
  • የምዝገባና ከስራ የማስተሳሰር  ድጋፎች ያገኛሉ። ለምሳሌ ወደ ስራ እንዲገቡ ለምያግዝ  የአኮሜደሽን እና ስልጠና ድጋፍ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ።

ፈረንሳይ ከሆነ ያሉት :

  • ከፈረንሳይ የኢመግሪሽን እና ኢንተርገሬሽን ፊስ ጋር በመሆን በፈቃድ በሚመለሱ ስደተኞች ዙርያ የሚመክር የምክክር መድረክ ይዘጋጃል   
  • የኦፊሱ ሙሉ አድራሻ እዚሁ ጋር ማግኘት ይቻላል here.

እንግሊዝ ሀገር ከሆነ ያሉት:

  • በፈቃድ ለሚመለሱ ለሚደረግ ድጋፍ ማእከሉን በሚቀጥለው ሊንክ ኦንላይን ማመልከት ይቻላል here  
  • ከተፈለገም ማእከሉን በስልክ ቁጥር 0300 004 0202 ላይ ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጥዋት 3 ሰዓት እስከ አመሻሹ 11 ሰዓት ባለ ጊዜ ውስጥ መደወል ይቻላል።

በፈረንሳይ:

  • ስደተኞች Groupe d’information et de soutien des immigré.e.s (GISTI) ከተባለ ተቋም ጋር ነጻ የህግ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።  ይህ ይህግ ድጋፍ ማእከል ሰኞ እና ዓርብ ከቀኑ 9 ሰዓት 12 ሰዓት  እሮብ እና ዓርብ ደግሞ ከ4 ሰዓት እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት በ01 43 14 60 66 በመደወል የምክር አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።
  • የህገ ወጥ የሰው ንግድ ሰለባ የሆነ ከሆነ ወደ ናሽናል ኮኦርድኔሽን ፎር ፕሮቴክሽን ኦቭ ቪክቲሚስ ኦቭ ሁዩማን ትራፊኪንግ የተባለ ተቃም በ  0 825 009 907 መደወል ይቻላል።

በእንግሊዝ:

  • ህገ ወጥ ስደተኞች ከኢሚግረሽን ባለሙያዎች ጋር ምስጥራዊነቱ የተጠበቀ ስብሰባ አቅራብያቸው በሚገኙ የዜጎች የምክር አገልግሎት ቢሮዎች ማግኘት ይችላሉ። አቅራብያዎ ያለ ቢሮ ለማግኘት ይሄንን ይጫኑ!  here.
  • ጆይንት ኮውንስል ፎር ወልፈር ኦፍ ኢምግራንትስ የተባለውን ተቋም  ሰኞ፣ ማኽሰኞና ሐሙስ ቀን ከ4 ሰዓት ጥዋት እስከ 7 ሰዓት ባለ ጊዜ ክፍት ስለሆነ በ  020 7553 7470 በመደወል ምክርና መረጃ ማግኘት ይቻላል።
  • የእንሊዝ መንግስት ስደተኞችን የሚያግዝበት መስመር አለው፡ መስመሩ  0808 800 0630 ሲሆን ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጥዋቱ 3፡30 እስከ ከቀኑ 9 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል።
  • ህገወጥ የሰው ነጋዴዎች ሰብአዊ ጥሰት ያደረስባቸው ሰው ከሆኑ ሞደርን ስልቨሪ ሀልፕላይን ጋር በ 08000 121 700 በማነኛውም ጊዜ በመደወል መረጃ እና ምክር ማግኘት ይችላሉ።
ለሌላ ያካፍሉ

የእንገሊዝ ቻናል በማቋረጥ ላይ ለነበሩ ስደተኞች ድጋፍ አድርጋቹኋል የተባሉ ሁለት ፈረንሳውያን ታሰሩ

ሁለት ፈረንሳውያን ስደተኞች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው ወደ እንግሊዘ እንዲገቡ በማገዛቸው ምክንያት በእስር እንዲቀጡ...
ተጨማሪ ያንብቡ

በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ...
ተጨማሪ ያንብቡ

የፈረንሳይ የባህር ላይ ጥበቃ ሀይሎች የእንግሊዝ ቻናል አልፈው ለመሄድ የሞከሩ ዘጠኝ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

መይ እሁድ 19 ቀን 2019 ዘጠኝ ስደተኞች በመያዝ በእንግሊዝ ቻናል በኩል ወደ እንግሊዝ በመሄድ ላይ የነበረ ትንሽ ጀልባ...
ተጨማሪ ያንብቡ