በፓሪስ አየር መንገድ ተርሚናል በሀይል ወደ ሀገር ቤት አንመልስም ያሉ በመተዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ሰለማዊ ሰልፍ አደረጉ

በመተዎች የሚቆጠሩ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ መዲናዋ ፓሪስ ከተማ አየር መንገድ ተርሚናል ውስጥ በመሰባሰብ ተቃዉሞአቸው አሰትመተዋል።

እነዚህ በሀይል እየተመለሱ ያሉ ስደተኞች የአሳይለም ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያላገኘ አልያም በዱብሊን ሬጉሌሽን መሰረት መጀመርያ የአውሮፓ ምድር ወደ ረገጡበት የአውሮፓ ሀገር እንዲመለሱ እየተደረጉ ያሉ ናቸው። የዱብሊን ሬግሌሽን በአውሮፓ ሀብረት አባል ሀገራት ስምምነት የተደረሰበት አንድ ስደተኛ መጀመርያ እግሩ በረገጠበት ሀገር አሳይለም መጠየቅ አለበት የሚል ህግ ነው።

ሰልፈኞቹ የፈረንሳይ መንግስት ህጋዊ ፈቃድ እንዲሰጣቸው እና ቤተሰቦቻቸው ወደ ፈረንሳይ ሀገር እንድያመጡ ጠይቀዋል። ትዊተር ላይ ፖስት የሆነ   አንድ ቪድዮ እንደሚያሳየው በግርድፉ ወደ 500 የሚጠጉ ስደተኞች በተርሚናል 2 ተገኝተው ተቃውሞው ላይ የተሳተፉ ሲሆን በርከት ያሉ የፖሊስ አባላት የቻርለስ ጉሌ አየር ማረፍያ ጣብያ የሰልፈኞቹ እንቅስቃሴ በቅርበት ሲከታተሉ ታይተዋል።  ሰልፈኞቹየፈቃድ ወረቀት ለእያንዳንዱ!” ሲሉ ተሰምተዋል። ሰልፉ የተዘጋጀው ስደተኞች በሚደግፍ ቻፕሌ ደቡት በተባለ ተቋም ነው።

2018 እና 2017 ጀምሮ ወደ ሀገር በሀይል የመመለስ ስራ (deportation) 20% ጨምረዋል። የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ክሪስቶፍ ካስትነር እንደገለፁት በተገለፀው አመት 14,859 ስደተኞች በሀይል ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ሰልፈኞቹ የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር አድዋርድ ፍሊፕ በአካል እንድያነጋግርዋቸው በይፋዊ መግለጫ ጠይቀው እንደነበር ገልፀዋል። በተጨማሪምፋይናንሻል፣ ሎጂስቲካል ድጋፍ እንድያገኙ አልያም ማባረር ላይ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ይኑረንየሚል ጥያቄ ይዘው የፈረንሳይ የአየር ፍራንስ ተወካዮች እንድያገኙዋቸው ጠይቀዋል። 

ፓሪሲን እንደዘገበው ስደተኞቹ በኋላ የአየር ፍራንስ ተወካይ አግኝተው ያነጋገሩ ሲሆን ተወካዩየስደተኞቹ ብሶት ለማነጅመንት አቀርባለሁብለዋል።

አንድ የሰልፉ አባል የሆነው ስደተኛ ይህ የመጀመርያ እንጂ የመጨረሻ እንዳልሆነ በመግለፅ አስጠንቅቀዋል።አሁን ዋና ትኩረታችን ያደረግነው አየር ፍራንስ ላይ ነው። ሌሎች ተግባራትም ይቀጥላሉ።ብለዋል።

ሰልፈኞቹ የአየር መንገዱ ተርሚናል እንዲዘጋ ቢያደርጉም የኤርፖርት ፓሪስ የበረራ ባለሙያዎች ግን በዚሁ ምክንያት የተስተጓጎለ በረራ እንደሌለ ገልፀዋል።

TMP – 10/06/2019

Photo credit: ኮለክቲፍ ቻፐሌ ደቡት/ፌስቡክ

ስደተኞች በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ቻርለስ ጉሌ አየር ማረፍያ ሰለማዊ ሰልፊ አደረጉ