ብሪታንያ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ማስታወቅያ አገልግሎትን ሊታደግ ነው

የኢንግሊዝ መንግስት ህገ-ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ለስደተኞች የሚጠቀሙት የፌስቡክ ማስታወቅያን እንደምታሳድድ ኣስታወቀች፡፡

እንደ ተለያዩ የኢንግሊዝ መንግስት ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ የኢንግሊዝ መንግስት 500 የሚጠጉ  የማህበራዊ ሚድያ ገፆች አብዛኛዎቹ የፌስቡክ ማስታወቂያዎችን ስደተኞችን ወደ አውሮጳ እንዲሄዱ ለማማለል እንደሚሚጠቀሙ ታውቋል፡፡

ሳልዝበርግ፡ ኦስትርያ ከመስከረም 19-20 2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ በተካሄደው ጉባኤ የኢንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ወ/ሮ ቴሬዛ ማይ እንዳሉት የህገ-ወጥ ሰው አዘዋዋሪዎችና ደላሎችን ቁጥጥር ማጠናከር እንዳለብንና ከስራቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ  እርምጃ መውሰድ አለብን ይህም የህገ-ወጥ ስደት ወንጀልን ለመከላከል ሲባል ነው፡፡ ይህንን ለማሳካት ምቹ ሁኔታን እንዳይፈጠር ለመከላከል ሲባል ነው፡፡

ይህንን ለማሳካት ምቹ ሁኔታን እንዳይፈጠር መከላከልና እነዚህን የስደተኞችን ህይወት አደጋ ላይ እንዲወድቅ እንዲያንሰራራና ቀላል እንዲሆኑ የሚያደርጉትን ሁኔታዎችና ትስስሮችን መበጣጠስ አለብን ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተርዋ ጨምረው ሲገልፁ የኢንግሊዝ መንግስት የሳይበር ፖሊሲንግ /ጥበቃ/ ችሎታዋና ልምድዋ ከሌሎች የአውሮጳ ሃገሮች እንደምታጋራና የኦንላይን መድረኮች ለድንበር ህጎች መከበር እንደማይሰሩ ገልፀዋል፡፡

ህገ-ወጥ የሰው ዝውውርና አዘዋዋሪዎች ትልቅ የገንዘብ /ገቢ/ ምንጭ ነው፡፡ በ2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ በተባሩት መንግስታት ድርጅት የመድሃኒትና የወንጀል ጉዳዮች ፅ/ቤት ጥናት እንደሚያመለክተው ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና ደላሎች ወደ 7 ቢልዮን ዶላር ትርፍ እንዳገቡና በ2016 እ.ኤ.አ 2.5 ሚልዮን ስደተኞችን በማዘዋወር እንዳገኙ ታውቋል፡፡

ለዚህም የማህበራዊ ሚድያ መድረኮች ለወንጀሎኞች የላቀ እርዳታ /እገዛ/ እንዳደረገና ታውቋል፡፡ በማህበራዊ ሚድያ እንዲጠቀሙ ካስገደዳቸው ዋናው ምክንያት አንዱ ጠንካራና የአከባቢ ሁኔታና ሃይልና የሃገሮች የስደተኞች ፖሊሲዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ 1.5 ቢልዮን የሚጠጉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ከነዚህም 900 ሚልዮን የሚሆኑት የቀጥታ /ኦንላይን/ ተጠቃሚዎች ወደ ብዙ ደንበኞች እንዲደርሱ እድል ተፈጥሯል፡፡ አንዳንዶቹ በህፃናትም ታላቅ ቅናሽ እንደሚያደርጉ ይገልፃሉ፡፡

የእርዳታ ኤጄንሲዎች ቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችን ከህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች እንዲታደጉ ተማፅነዋል፡፡ ከ2017 ዓ/ም እ.ኤ.አ ጀምሮ የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የማህበራዊ ሚድያ ካምፓኒዎች ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ማህበራዊ ሚድያን ለማባበያ እንዳይጠቀሙ የሚታደርግ እርምጃ /አስቸጋሪ/ እንዲያደርጉትና ስደተኞች ለማማለል እንዳይጠቀሙበት እንዲያደርጉ ይማፀናሉ፡፡

ጥቅምት ወር 2018 ላይ ከኒውሰልስ ጋር በተደረገው ቃለ ምልልስ የፌስቡክ ቃል አቃባይ እንደገለፀው ካምፓኒው  የማህበራዊ ሚድያው መድረክ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ በቀጣይነት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ቃል አቀባዩ እንዳለው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ህገ-ወጥ መሆኑና ማንኛውም ማስታወቅያ ፣ ገፅ  ድህረ ገፅን መጠቀም አይፈቅድም ለዚህም ከህግ አስከባሪዎች ጋር በብቅ እንሰራለን ከኢንተርፖልንም ጨምሮ

ፍቶ ክረዲት፡- Europa.eu