ያለ ረዳት የቀሩ 63 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ድጋፍ ተደረገላቸው

ካለፈው ሓምሌ ጀምሮ በሶማሊያ ያለ ረዳት የቀሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡

ዕድሜአቸው ከ15 እስከ 48 የሆኑት 63 ስደተኞች በየመን በኩል ቀይ ባህርን ተሻግረው ሳውዲ አረቢያ ለመድረስ ነበር፡፡ አንድ የንግድ መርከብ ከአደጋ እስኪያድናቸው ድረስ ለ6 ቀናት ካለ ረዳት የቀሩበት ምክንያት የተሳፈሩበት ጀልባ የሞተር ብልሽት ስላጋጠመው ነበር፡፡ ከአደጋ ያዳንዋቸው በሰጡት ሪፖርት መሠረት እጅግ በጣም ከደከሙት ስደተኞች መካከል ሁለቱ በውሃና ምግብ አቅርቦት እጥረት ምክንያት መሞታቸው ገልጿል፡፡

በሃርጌሳ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ፅ/ቤት ተመላሾቹ በሶማሊላንድ በቆዩባቸው ወቅት በሕክምና አገልግሎት፣ በመጠለያ፣ በምግብ በልብስና በምክር አገልግሎት እንደረዷቸው ተናግሮኣል፡፡

በሃርጌሳ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ፅ/ቤት ኃላፊ የሚከተለው ብሏል፡ እነዚህ ስደተኞች በማእበል እየተንሳፈፉ ስንቅ ለሌለባት ትንሽ ጀልባ ተስፋ ለምታስቆርጥ የኤደን ባህረ ሰላጤ ደረሱ፡፡ ከአደጋ መዳናቸው በጣም  ተደስተናል፣ እና በኛው አሲስትድ ቮልንታሪ ሪተርን ሰርቪስ/አገልግሎት በኩል ድጋፍ አድርገንላቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙት የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ፅ/ቤት የሥራ ባልደረቦቻችን በአዲስ አበባ በቦሌ የአይሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚመለሱ እርግጠኞች ነን፡፡  

ከተመላሾቹ አንዷ ዕድሜዋ 22 ዓመት የሆነች ሰምሃር የተባለች ገጠመኙ በጣም እንዳስደነገጣት የሚከተለው ተናግራለች፡እኔ ሞትን ነበር የምጠብቀው፡፡ አሁን በሕይወት መኖሬ ደስተኛ ነኝ፣ ቤተሰቦቼም በሕይወት በመኖሬ ደስተኞች ናቸው፡፡ አሁን የምፈልገው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ብቻ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ለሕገ – ወጥ ስደትና መሸጋገርያ መሆን ዋና መሠረት ናት፡፡ በሕገ-ወጥ መንገድ ለመሰደድ የሚፈልጉ በርካታ ኢትዮጵያውያን አመቺ የኤኮኖሚ ጥቅም ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ነው የሚያመሩት፡፡ በዳኒሽ ሬፉጂ ካውንስል ሚክስድ ማይግሬሽን ፕላትፎርም ሪፖርት መሠረት በ2015 የመን ከደረሱት ሕገ-ወጥ ስደተኞች ኣብዛኛዎቹ 90% የሚሆኑት ከኢትዮጵያ የሄዱት ነበር፡፡

ወደ ቤታቸው በፈቃደኝነት የተመለሱት በአውሮፓ ኅብረት ትረስት ፈንድ ለአፍሪቃ በኩል ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የሚሰጠው ድጋፍ ብቁ ናቸው፡፡ ድጋፉ የሚያጠቃልለው በማሕበረሰብ ውስጥ ለመዋሃሃድና መተዳደሪያን በማቋቋም ረገድ ነው፡፡ ከተመላሾቹ አብዛኛዎቹ 1200 የሚሆኑ ተመላሾች ኢትዮጵያውያን ከ2017 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ የዚሁ ዓይነት ድጋፍ እየተደረገላቸው ቆይተዋል፡፡   

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) በኩል ከአውሮፓ ኅብረት ጋር አብረው ከሚሠሩት ጋር በተነሳሽነት ለተመላሽ ስደተኞች ልማት ተኮር ፖሊሲዎችን በመመሥረት ደህንነቱ የተጠበቀ ሰድት ለማስተዳደር በማመቻቸት ከ26 የአፍረቃ አገሮች ጋር በመሆን የኣውሮፓ ኅብረት ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የጋራ EU-IOM joint initiative ተነሳሽነት አንድ ክፍል ናት፡፡

TMP – 14/09/2018

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከሃርጌሳ ሶማሊላንድ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ፡፡ ፎቶ፡ ኣለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት/ IOM