በሊብያ የስደተኞች ማቆያ ማእከላት ያለ የምግብ ችግር አሁንም እየጨመረ ነው

መድስንስ ሳንስ ፍሮንቴሪስ (MSF) የተባለ የህክምና እርዳታ የሚሰጥ ተቋም ማርች 21ቀን 2019   በትሪፖሊ ሳቢ በተባለ የማቆያ ማእከል ያሉ ስደተኞች ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረትና የክብደት መቀነስ ችግሮች ተጋርጦባቸው እንዳለ ገልፀዋል። ተቋሙ እንደገለፀው አብዛኛዎቹ በዚሁ የማቆያ ማእከል ያሉ ስደተኞች ኤርትራውያን ናቸው። ሌሎች ከሱዳን፣ ናይጄርያ፣ ካሜሮን እና ጋና የመጡ ስደተኞቹም እንዳሉ ተነግረዋል።  

ይህ ከ300 በላይ ስደተኞች የታጨቁበት ማእከል ከዚሁ ቁጥር አንድ ሶስተኛ ህፃናቶች ናቸው። ከግማሽ በላይ ደግሞ ከስድስት ወር በላይ እዚሁ ታጭቀው የቆዩ ናቸው።  

MSF የምግብና ስነ መዓዛ ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ በሁለት እና በሶስት ቀናት ውስጥ አንድ ምግብ ብቻ ነው እያገኙ ያሉት። አዳዲስ መጪዎች ድግሞ እስከ አራት ቀን ምንም ምግብ ሳያገኙ የሚቆዩበት አጋጣሚ አለ።  በዚህ ምክንያት ወደ ሩብ የሚጠጋ የስደተኛው ቁጥር በምግብ እጥረት የተጠቃ አልያም የክብደት መቀነስ ችግር የሚታይበት ነው።  

ሁኔታው በከፍተኛ ደረጃ አሳሳቢ ነው።” ብለዋል ኪስ ኩስ የተባሉት በሊብያ  የ MSF የጤና አማካሪ።   የእኛ የጤና ቡድን አንድ ታማሚ የሚወስደው መድሀኒት አቋርጦ ሲሰቃይ አይተዋል። ምክንያቱም የሚበሉት ነገር ስሌለ ነው። የምግብ እጥረት የሌሎች ተያያዥ ችግሮች ምንጭም እየሆነ መጥተዋል።” ብለዋል ተቋሙ። ይህ የመድሀኒት መቋረጥ ደግሞ እንደ ቲቢ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች ሁሉም ስደተኛ ጋር እንዲዛመቱ እያደረገ መሆኑ ገልፀዋል።

ሪፖርቱ እንድምያሳየው ከሆነ እያጋጠመ ያለ የምግብ እጥረት አዳዲስ በሚገቡት በሁለት እጥፍ የሚበልጥ ነው። ይህ የምያሳየው ማቆያ ማእከላት ውስጥ ካሉት ሰዎች በበለጠ በህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች ስር የወደቁት ክፉኛ አደጋ ውስጥ እንዳሉ የምያሳይ ነው።   

በዚህ አንድ ማቆያ ማእከል ውስጥ እያየነው ያለ ነገር ከቁጥጥር ውጭ በሆነ፣ ምክንያት ሊሰጥበት የማይችል እና በተበላሸ ሲስተም ውስጥ ስደተኞች ማሰቃየት ያለው አደጋ ነው።” ብለዋል ካርሊለን ከልጅር የMSF የአደጋዎች ቁጥጥር ሀላፊ።

“እኛ እያወራን ያለነው ስለ መሰረታዊ ህይወትን ማቆየት የሚችሉ የሰው ልጅ ፍላጎቶች ነው። ምግብ፣ መጠልያና ሌሎች አስፈላጊ አቅርቦቶች የማይሟላላቸው ከሆነ የሊብያ ባለስልጣናት በቀጥታ እነዚህ ስደተኞች መልቀቅ ነው ያለባቸው።” ብለዋል።

በግምት ወደ 670,000 የሚጠጉ ስደተኞች ሊብያ ውስጥ እንዳሉ ይነገራል። MSF  እንደሚለው እነዚህ ስደተኞች በሙሉ በሚባል ደረጃ ልክ እንደ ዕቃ ይሸጣሉ። የፆታ ጥቃት ይደርስባቸዋል። የሚዘገንን ስቃይ ውስጥ ይወድቃሉ ወዘተ።  የሊብያ መንግስት በአሁን ሰዓት ከ 5,700 በላይ ስደተኞችን እንደ ሳቢ በመሳሰሉ መንግስት የሚቆጣጠራቸው የስደተኞች ማቆያ ማእከላት   ዉስጥ እንደሚገኙ ይነገራል።

ሊብያ በመሬትዋ አድርገው ወደ አውሮፓ የሚጓዙ ስደተኞችን በየጊዜው እየያዘች  የመመለስ ስራዋ ቀጥላበታለች።  በመጀመርያዎቹ የ2019 ሁለት ሳምንታት ውስጥ  ቢያንስ  1,000 ስደተኞችን ወደ ሊብያ እንዲመለሱ አድርጋለ።    

TMP – 28/03/2019

ፎቶ: ጉልሜ ቢኔት/ሚዮፕ/MSF. በሊብያ ትሪፖሊ ከተማ አቡ ሳሊም በሚባል የስደተኞች ማእከል ውስጥ የፀጥታ ሀይሉ ስደተኞች በታጨቁበት ስፍራ አከባቢ ይታያል፤ 2017