በ2018 ብቻ 15 ሺ ስደተኞች ከሞት እንዳዳነ የሊብያ የባህር ጠረፍ ሰዎች ገለፁ።

የሊብያ የባህር ላይ ጠባቂዎች ቃል አቀባይ ዴሰምበር  20 ላይ እንደገለፀው ባለፈው ዓመት ብቻ ከ15 ሺ በላይ ስደተኞች ወደ አውሮፓ በሚሄዱበት ሰዓት ከሚያጋጥማቸው ፈተና እንዳደንዋቸው ገልፀዋል። እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች የሊብያ ፅህፈት ቤት ገለፃ ከሆነ ከዚህ አደጋ ከዳኑ ስደተኞች በብዛት ሶስት ሃገራት ማለትም ከሱዳን፣ ናይጄርያ እና ኤርትራ የመጡ ናቸው። ከእነዚህ ስደተኞች ከ10ሩ 7ቱ ወንዶች ሲሆኑ ከ10 ስደተኞች 1 ደግሞ ህፃን ይገኙበታል።    

የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች  በባህር ላይ ስደተኞችን የመያዝ ስራ  አጠናክረው የቀጠሉበት ሲሆን ይህ የሆነበት ምክንያትም     ጣልያን እና ሊብያ ዴሰምበር 2017 ላይ   ባደረጉት ስምምነት መሰረት ነው። ይህ ስምምነት በኋላ ላይም በማነኛውም መንገድ የተገኙ ስደተኞችን ወደ ሊብያ የመመለስ ተልእኮም ወስደዋል።   የሊብያ የባህር ላይ ጠባቂዎች ስደተኞችን የማደን እና የመመለስ ስራዎቻቸው 94 ኑቲካል ማይልስ በማስፋት በማነኛውም የውሃ አካል የተገኙ ስደተኞች  ይመልሳሉ። ሊብያ ላይ ለከተመው የተባበሩት መንግስታት እንደሚገልፁት ከሆነ እነዚህ የሚታገቱ ስደተኞች ከሊብያ በኩል የወጡ ናቸው።   

በጃንዋሪ 2017 እና ሴፕተምበር 2018 ባሉት ግዝያት ውስጥ ብቻ 29 ሺ ስደተኞች በሊብያ የባህር ጠባቂዎች እጅ ወድቀዋል።  ዩኤንኤስኤምኣይኤል በቅርቡ ባሳተመው የህትመት ውጤቱ ሁኔታው ሲገልፀው ,   Dአስጊ እና አስፈሪ፡ በሊብያ ባሉ ስደተኞች መብት እና የህይወት ሁናቴ የወጣ ሪፖርት  ይለዋል፤ ዴሰምበር 18/2018 ባወጣት ህትመት።   

በሪፖርቱ እንተገለፀው በሜዲትራንያን በኩል ወደ አውሮፓ የሚሄዱ ስደተኞች ብዙ ችግር ይገጥመዋቸዋል።  የህትመት ውጤቱ የሊብያ መሬት ከረገጡባት  ግዜ ጀምሮ ለግድያ፣ ቶርቼር፣ አስከፊ ችግሮች፣ ባርነት፣ መደፈር እና ሌሎች ፆታዊ የሆኑ ጥቃቶች ይዳረጋሉ፤ ይሄም በመንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የሚፈፀም ነው።” ብለዋል።   አንዳንድ ጥገኝነት ጠያቂ ስደተኞች በሃገሪቱ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር አማካኝነት ይድናሉ፤ ብዙ ደግሞ በታጣቂ ቡድኖች ታግተው እዛው ይገኛሉ።   

የተባበሩት መንግስታት የሊብያ ማእከሉ እንደሚለው ከሆነ እስከ 2018 መስከረም ወር ባለ ጊዜ ውስጥ ብቻ በምዕራባዊ የሊብያ ክፍል  6800 የሚገመቱ ስደተኞች ተይዘዋል። ሌሎች ብዙ ስደተኞች ደግሞ ከስደት ጋር ተያያዥነት በሌላቸው ማለትም በስርቆት፣ የተከለከለ ዕፅ በማዘዋወር ወንጀል፣ በወሲብ፣ በአልኮል ተጠቃሚነት፣ ሽብር ወዘተ ተከሰው ግዜው በማይታወቅ እስር ውስጥ ይገኛሉ።   

በስደተኛ ማቆያ ማእከላት ያለ ሁኔታም የከፋ መሆኑ ነው የሚነገረው።    በአጠቃላይ ሰብአዊነት የጠፋበት፣  ቬንቲሌተር የሌለው እና የታፈነ ቤት የሚኖሩበት፣ ብርሃን አልባ ማቆያ፣ የውሃ ችግር የሞላበት፣ ከሌላ አለም እንዳትገናኝ የምያደርግ ህግ እንድሁም የምግብ እጥረት የሚታይበት ነው።” በማለት ፅሁፉ አስፍሮታል።  ሁኔታው በደንብ ለመግለፅ የምያስችል አንድ   አጋጣሚ  28 ዕድሜው ሶማልያዊ ወጣት ራሱን በእሳት ያጋየበት  በሊብያ ትሪፖሊ ያጋጠመ ክስተት ነው።

በተጨማሪም የተቋሙ ዘገባ  “ብዙ ግዜ ሴት ስደተኞች በወንድ ጋርዶች ስር ሆነው እንድያገለግሉ ይደረጋሉ።” ይላል።  አንድ የስደት ማቆያው ላይ ያለች ሴት እንደገለፀችው በየምሽቱ  እስከ ስድትስ ግዜ ትደፈራለች።   

ይህ በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለ ጥቃት እንዳለሆኖ የሊብያ ባለስልጣናት ግን ይሄንን የመብት ጥሰት መቋጫ የምያገኝበት አቅጣጫ ሳያስቀምጡ አሁንም እንደነበሩ አሉ።” ይላል ዘገባው።

ይህ በሊብያ ማቆያ ማእከላት ላይ እየተፈፀመ ያለ የመብት ጥሰት እና ጉዳት በአለማችን ዙርያ መሰማት ከተጀመረ ወዲህ  ቡድኖች   ህገ ወደተኞች ላይ ድህንነታቸው የሚጠበቅላቸው መንገድ እንዲፈለግ እና ነፃ እንዲወጡ  እንቅስቃሴ ጀምረዋል።   እንደ ዡንዋ ገለፃ ከሆነ አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም፤ አይኦኤም በ2018 ብቻ 16 ሺ ስደተኘች ወደየሃገራቸው እንዲመለሱ ድጋፍ አድርገዋል። ከዚህ ቁጥር ከፍተኛ ሬሾ የሚይዘው የናይጄርያ ስደተኞች ሲሆን ማሊ እና ኒጀር ይከተላሉ።    

TMP – 20/01/2019

የፎቶ ካፕሽን: ስደተኞች በምንጣፍ ላይ ወድቀው ይታያሉ፤ በሊብያ ትሪፖሊ  

ፎቶ ክሬዲት: ዩኒሴፍ/አለስዮ ሮማንዚ