ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ ስደተኞች በባህር ጠባቂዎች አመካኝነት ወደ ሊብያ ተመለሱ!

ጁን 24 ላይ ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ ስደተኞች የያዘ ጀልባ በሊብያ የባሀር ጠረፍ ሰራተኞች ከአደጋ ድነዋል። ኤኤፍፒ እንደዘገበው የአስር ሰዎች ሬሳም በባህሩ ተገኝተዋል።

948 አፍሪካውያን ስደተኞች ከትሪፖሊ በስተ ምስራቅ በምትገኝ በጋራቡሊ የባህር ወደብ አድርገው በሶስት ጀልባዎች እና በሶስት ኦፕሬሽኖች ባህሩን ለማቋረጥ ሲንቀሳቀሱ ነበር በሊብያ ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ጉዳዩ በማስመልከት የጣልያን የሀገር ውስጥ ፀረ ስደተኞች ሚኒስትር ማቲዮ ሳሊቪኒ ስደተኞቹ በማዳናቸው ለሊብያ ባለ ስልጣናት ምስጋና አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው “እንደ ሚኒስትር እና እንደ ወላጅ ለሊብያ ባለስልጣናት እና ባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ያለኝን ልባዊ ምስጋና ለመግለፅ እፈልጋለሁ።” ብለዋል።

“ዛሬ 820 ስደተኞች ታድጋቹኋል። ወደ ሊብያ እንዲመለሱም አድጋቹኋል። ይህ ተግባር ህጋዊ ባልሆነ የሰዎች ዝውውር ስራ ለተሰማሩ እና አላስፈላጊ የምግባረ ሰናይ ተቋማት ጣልቃ ገብነት መልካም እርምጃ ነው” ሲሉም ገልፀዋል ሚኒስትሩ።

ሚኒስተሩ ይሄንን ቃል የተናገሩት ተመላሾቹን ለማናጋገር ወደ ሊብያ ባመሩበት ወቅት ነው።

በመግለጫቸው “የሊብያ ባለ ስልጣናት ስደተኞች የማዳንን፣ ወደ ሀገራቸው የመመለስን የተለመደ የቤት ስራቸው ያለ ማንም የምግባረ ሰናይ ተቋማትጣልቃ ገብነት እንዲሰሩ እንትዋቸው።” ብለዋል።

በጁን ወር ላይ ሳልቪን 630 ሰዎች የጫነች ጀልባ በጣልያን ወደቦች አመካኝነት ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ልታስገባ ስትል መከልከላቸው ይታወቃል። ማልታም ተመሳሳይ እርምጃ የወሰደችባት ይህች መርከብ እዛ የነበሩ ስደተኞች በስፔን የባሀር ላይ ጠባቂዎች እርዳታ እስኪድኑ ድረስ ባህር ላይ እንዲቆዩ ሆነዋል።

ጣልያን እና ማልታ ሌላ 234 ስደተኞች የጫነች ጀልባ የከለከሉ ሲሆን በብዙዎች ዘንድ አሳሳቢ ሆኖዋል። በመሆኑም ጀርመን ማእከሉ ያደረገ ሚሽን ላይፍላይን የተባለ ምግባረ ሰናይ ድርጅት የሁለቱም ሀገራት ስደተኞችን የመከልከል ተግባር በስደተኞች ላይ ለሚደርስ ጉዳት ሀላፊነት የሚወስድ አካል የሌለ መሆኑ የምያሳይ በመሆኑ ላይፍላይን ከፍተኛ ስራ እንደሚጠብቀው ይገልፃል።

ሳሊቪኒ እንደሚሉት ደግሞ ሀገራቸው ማየት ለሚፈልግ ማንኛውም ስደተኛ “ፖስት ካርድ ላይ ብቻ” ማየት እንደሚችል ይገልፃሉ። የጣልያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደሚለውም በሊብያ ባህር ላይ ያለ የስደተኞች ብዛት እና ለማቋረጥ የሚደረግ ጥረት ጣልያን ያወጣችውን ህግና ደንቦች የሚፃረር ነው።

ጁላይ 26 ላይ ብራስለስ ጀርመን በተካሄደው የምክክር መድረክ ማልታ ልክ ሌሎች የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት እንደተስማሙት ስደተኞችን በተመለከተ በአደጋ ጊዜ ለመምከር በምያስችል የስምምንት ሰነድ ላይ መፈረምዋ ይታወቃል።

ሳሊቪኒ ታድያ ከዚህ ስምምነት በኋላ ነበር ስደተኞች የያዘች ጀልባን ወደ ስፔን በማለፍ ላይ እያለች እንድትመለስ ያደረጉት። የዛኔ ማልታ ፈቃድ ሰጥታ ስታሳልፋቸው ሳሊቪኒ በትዊተር ገፃቸው “ከጦርነት ያላቸው አከባቢ የመጣችሁ ሴቶች እና ህፃናት መግባት ትችላላችሁ። ሌሎቻችሁ ግን አልተፈቀደላችሁም።” ብለዋል።

TMP – 28/07/2018

ፎቶ: ሚሽን ላይፍላይን/ ትዊተር. ጀርመን መሰረቱ ያደረገ የላይፍላይን ህይወት መድን ጀልባ