በኒጀር በአይኦኤም ጥረት ስደተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ወደ ሀገር ቤት መመለስ ጀምረዋል

የተባበሩት መንግስታት የስደት ኤጀንሲ ባደረገው ድጋፍ መሰረት በገዛ ፈቃድ የሚደረግ ስደተኞች የመመለስ ፕሮግራም ከባለፈው ዐመት በተሻለ መንገድ በኒጀር ስኬታማ ስራ መሰራቱ ተገለፀ።

እንደ አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (IOM) ገለፃ ከሆነ በዚሁ ዐመት በጁላይ ወር መጨረሻ አከባቢ10 ሺ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል። ይህም 2017 ከነበረው 7 ሺ ተመላሽ የበለጠ መሆኑ ነው ተቋሙ የገለፀው።    

በመይ ወር ብቻ 3400 ስደተኞች ይህ በፈቃደኝነት መመለስ የተሰኘውን ፕሮግራም የመረጡ ሲሆን ይሄም ከዚህ ወር በፊት ተመዝግቦ የማያቅ ቁጥር ነው ተብለዋል።   የዘንድሮ የተመላሾች ቁጥር ከሌላ ጊዜ በተነፃፃሪ የተሻለ መሆኑን ማሳያ የሚሆነን በ2015  ዓ.ም እንዲመለሱ ድጋፍ የተደረገላቸው 1,721 ሲሆን በ2016 ደግሞ 5 ሺ ለምያህሉ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤት መመለስ የምያስችላቸው ድጋፍ ተሰጥተዋቸዋል።

ከ12 ሺ በአይኦኤም የመተላለፍያ ማእከላት የተገኙ ከስደት ተመላሽ ዜጎች ግማሽ የምያህሉ የማንነት መለያ ፎርም የላቸውም። ከ5 ሺ በላይ የጉዞ ሰነዶች ኒጀርን ጨምሮ ከተለያዩ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ኤምባሲዎች የተገኘ ነው።    

ከ8,000 መዳን የቻሉ ስደተኞች ወደ 90 በመቶ የሚጠጉትን በ84 የፍለጋ ኦፕሬሽኖች ላይ የተገኙ መሆናቸው የአይኦኤም ዘገባዎች ያሳያሉ።   

የአይኦኤም ቡድን በገዛ ፈቃደቸው ወደየሀገራቸው ለሚመለሱ ሁሉም የምዕራብ አፍሪካ ስደተኞች  ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ድጋፍ እየሰተጠ ነው ያለው። ድጋፉ እየተሰጠ ያለው ከበረሀ ያመለጡም እንዲሁም  ከእኛ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሁሉም ነው” ብለዋል የኒጀሩ የአይኦኤም ኮምሽነር ጉስፒ ሎፕሬቴ።    

እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ከሆነ አልጀርያ ከመይ 2017 እስካሁን ከ13, 000 በላይ ስደተኞች ከ 40 ድግሪ ሴልስ የሙቀት መጠን በላይ በሆኑት የኒጀር እና ማሊ በረሀዎእች ላይ እየተሰቃዩ ድጋፍ ሳትሰጣቸው ቀርታለች።  

የአይኦኤም ጀነራል ዳይሬክተሩ ዊልያም ላሲ ባወጡት መግለጫ እርጉዝ ሴቶች እና ሌሎች አቅም የሌላቸው አካላትን ጨምሮ ህጋዊ ያልሆኑ ስደተኞች ያለ ምግብና ውሃ መተው፣ ረጅም ጉዞ እንዲጓዙ ማድረግ እና ከ30 ድግሪ ሴልስ በላይ ሙቀት ባለበት አከባቢ መተው ተገቢ አይደለም።” ብለዋል።

ሓሰን ካሲሚ በአልጀርያ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ባለስልጣን ሲሆን አልጀርያ እንደዚህ አይነት ኢ ሰብአዊ ድርጊት ለምን እንደፈፀመች ለማብራራት ሞክረዋል። “ አይኦኤም ያልተናገረው አንድ ሀቅ አለ። ስደተኞቹ  እኮ (አልጀርያ ውስጥ እያሉ) ምግብ እና ውሃ ያቀረበችላቸው አልጀርያ ናት!” በማለት አስተባብለዋል።

የቅርቡ ጊዜ የመመለስ  ስራ የተከናወነው በጁላይ 15 ሲሆን የአልጀርያው ባለስልጣን እነዚህ የመለስዋቸው 600 አፍሪካውያን ስደተኞች አልጀርያን በማቋረጥ ለመሄድ ሲሉ የተያዙ ናቸው። እንደ አባባላቸው “ይህ የመመለስ ስራ የነበረውን ከመከራ የማውጣት ስራ ነው” ብለዋል ኤኤፍፒ በዘገባው።

 ባለስልጣኑ እንደገለፁት ስደተኞቹ እንደሚሉት ከሆነ ወደ ጠረፋችን ታፍነው መጥተው እዛ እንዲቆዩ ተደርገዋል።” አክለውም “እዛው የምግብ እና የውሃ እጥረት ባለበት እንዲቆዩ ተደርገዋል።  የማዳን ዘመቻው ከመካሄዱ በፊት 50 ኪሎሜትር በእግር የመጓዝ ግዴታ ነበረባቸው።” ብለዋል።

TMP – 07/09/2018

ፎቶ ክሬዲት: አይኦኤም.  ስደተኞች በአይኦኤም የመተላለፍያ ማእከል ውስጥ ለሴት ስደተኞች እየተሰጠ ያለ ድጋፍ የምያሳይ