የአፍሪቃ ህብረት መደበኛና ህጋዊ ከሃገር የማውጣት ዕድል ሊከፍት ነው
ከአውሮፓ ህብረት ጋር በመተባበር የአፍሪቃ ህብረት ወደ አውሮፓ በሚያደርጉት የአፍሪካ ወጣቶችን ህይወት አደጋና ከህገ–ወጥ ስደት ለመታደግና ለመከላከል አዲስ ስራ መጀመሩ አስታውቋል።
በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽን ምክትል ሓላፊ ተወካይ የሆኑት ናይጄርያዊ ብርጊቴ ሙካንጋ ኢኖ ህዳር 29/2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ በተካሄደው የባለድርሻ አካላት ስብሰባ እንደተናገሩት የአፍሪቃ ህብረትና የአውሮጳ ህብረት ህጋዊ ከሃገር የመውጣት እድል ለመክፈል ለማመቻቸት እየተነጋገሩበት መሆኑ ገልፀዋል።
ተወካዩ ብርጊቴ እንደገለፁት የውጭ ሃገራት ኩባንያዎች የሰው ሃይል (ሰራተኞች) ያስፈልጋቸዋል፡፡ ከሃገር በህጋዊ መንገድ የመውጣት እድል ለምን አናመቻችም የቪዛ ማመልካቻዎችን ወድቅ ከማድረግና ወጣቶችን ወደ አደገኛና ህገ–ወጥ ጉዞ ከመጋበዝ ሲሉም ይጠይቃሉ።
የአውሮጳ ህብረት ለአፍሪቃ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር በአፍሪካ መዋእለ ንዋይ እያፈሰሰ መሆኑ ይታወቃል። በነሃሴ 2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ የታላቋ ብሪታንያ መንግስት የ11 ሚልዮን ፓውንድ ስምምነት በኢትዮጵያ ለ 100,000 (አንድ መቶ ሺ) የስራ እድል ለመፍጠርና የታክስ (ግብር) አሰባሰብ ዘዴን ለማሻሻል መፈራረሙ ይታወቃል። በህዳር 2018 እ.ኤ.አ የአውሮፓ ህብረት የልኡካን ቡዱን በጋምቢያ እንደገለፁት የስራ የክህሎትና የገንዘብ ድጋፍ ለሴቶችና ወጣቶች መርሃ ግብር ለ 3000 (ሶስት ሺ) ሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል በጋምቢያ እንደሚቋቋም አስታውቋል።
ሙካንጋ ኢጎ በተጨማሪም የምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኤኮአሰ) ለወጣቶች ህጋዊ ከአገር የመውጣት እድል የሚያስችል አዲስ ፖሊሲ እያዘጋጀ መሆኑ አመልክተዋል።
የአፍሪቃ ህብረትና ሌሎችም የአህጉሩ አደረጃጀቶች እንደነ ኢጋድና ኮሜሳ (የምስራቅና ደቡብ አፍሪቃ የጋራ ገበያ ማህበር) ፣ የምስራቅ አፍሪቃ ማህበረሰብ ለኢኮኖሚያዊ ትስስርና በአህጉሪቱ ውስጥ ነፃ የዜጎች እንቅስቃሴ እንዲኖር እየሰሩ መሆናቸው ታውቋል።
ይሁን እንጂ የዚህ ዓይነቱ ሂደት ዘገምተኛ ነው ምክንያቱም አባል ሃገራትይ የሚነሱትን ሃሳቦች ላይ ለመስማማት እየጣሩ ስለሆነ ነው ። ለምሳሌ በቅርቡ የህብረቱ ነፃ የዜጎች እንቅስቃሴ ፕሮቶኮል ሊጠቀስ ይችላል። ይህንን ስምምነት በኪጋሊ ሩዋንዳ መጋቢት ወር 2018 ዓ/ም የፈረሙት 27 ሃገሮች ብቻ ናቸው።
የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) በ2018 ዓ/ም እ.ኤ.አ በ2150 በላይ ህገ–ወጥ ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ወይም የሜዲተራንያን ባህር ሲያቋርጡ በጉዞ ላይ ሳሉ ደብዛቸው መጥፋቱ ዘግቧል። የአፍሪቃ ህብረት አባል ሃገራት ይህንን አስከፊ ክስተት ለመቋቋምና ዋና ዋና ምክንያቶች በሃገርና በአህጉር ደረጃ ለመቅረፍ ሃላፊነት እንዲወስዱ አጥብቆ እየተማፀ ነው።
TMP – 12/12/2018
ፎቶ:- ኣሌክሳንድሮስ ሚካይሊዲስ/ ሻተርስቶክ። የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሃላፊ ፍሪዳሪካ ሞገሂሪኒ እና የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በብራስለስ ቤልጅየም
ፅሑፉን ያካፍሉ