በፈረንሳይ አልፕስ አከባቢ አንድ ስደተኛ በብርድ ህይወቱ አልፎ ተገኘ

ዘለካል  እንደዘገበው ከሆነ በፈረንሳይ አልፕስ አንድ ስደተኛ በቅዝቃዜ ምክንያት መንገዶች ላይ ወድቆ በልብ በሽታ ህይወቱ አልፎ ተገኘ።   

ይህ ስደተኛ ጣልያንን ለመሻገር አስቦ በአልፕስ አከባቢ እንደደረሰ ነው ፌቡራሪ 7 ላይ ከጥዋቱ 3፡00   በሀትስ አልፕስ እና የጣልያንዋ ፒዳሞት አከባቢ አንድ የከባድ ጭነት መኪና ሹፌር ወድቆ ያገኘው።   

የፈረንሳይ የአከባቢው ፖሊስ ስደተኛው ለማዳን አምቡላስ የጠራ ሲሆን የ29 ዓመቱ የቶጎ ዜግነት ያለው ስደተኛ ደርማን ታሚሙ ግን በሃይፖተሪማ በሽታ ምክንያት ክፉኛ ተጎድቶ ስለነበር ማዳን አልተቻለም። እንደ ዘሎካል ዘገባ ከሆነ በጠረፍ ከተማ በሪያንኮን በምትገኘው ሆስፒታል ውስጥ መሞቱን በሀኪሞች ተነግረዋል።  

የቻሪቲ ሬንቦው ፎር አፍሪካ የተባለው ተቋም ፕረዚደንት የሆኑት ፓሎ ናርቺሲ ለዘጋርድያን   “ይህ ሰው በቀይ መስቀል እና በኛ በኩል የመንገዱን አደገኛነት በጥብቅ ከነገርናቸው ማታ ላይ ያለፉ 21 ሰዎች አንዱ ሊሆን ይችላል” ብለዋል።    

በጃንዋሪ የመጀመርያ ሰሞን በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት መንገዱ አደገኛ እና ለመሄድ አስቸጋሪ ያደረገው ሲሆን ይህ ቶጎአዊ ስደተኛም ግማሽ አካሉ በበረዶ ተሸፍኖ ነው የተገኘው።    

አፕሪል 2018 ላይ በዚሁ ቦታ ሶስት ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ይታወቃል። ከሶስቱ አንደኛው ናይጄርያዊ ማቲው ብለሲንግ ሲሆን ከብርያንኮን ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው ዱራንሴ ወንዝ ነው የተገኘው። ሁለት ሌሎች ስደተኞች ደግሞ ስደተኞች በሚሄዱበት መንገድ ሙተው ተገኝተዋል።  በዚሁ በያዝነው የፈረንጆች አመትም ይህ የቶጎ ስደተኛ የመጀመርያው ይህ በረዳማ መንገድ ስያቋርጥ ህይወቱ ያለፈ ስደተኞ ለመሆን ችለዋል።  

በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በፈረንሳይ  የተሻለ ህይወት ፍለጋ ይሄንን የአልፕስ ተራሮች አቋርጠው ለመሄድ ከጣልያን ይነሳሉ። ይሁንና መጨረሻቸው በፈረንሳይ ጎደናዎች መያዝ እያ ወደ መጡበት መመለስ ይሆናል።  ብዙ ስደተኞችም በመቶዎች የሚቆጠር ዩሮ እየከፈሉ በመኪና አደገኛ በሆነው የአልፕስ መንገድ ማቋረጥ ወደ ፈረንሳይ ያቀናሉ።   

የጣልያኑ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ማቲው ሳሊቪኒ ፈረንሳይ ባለፉት ሁለት አመታት “ከ60 ሺ በላይ ስደተኞች፡ ኣብዛኛዎችም ሴቶች እና ህጻናት በጨለማም ሳይቀር በበረሃዎች ወደ ጣልያን መመለስዋ” ይከሳሉ። በዱብሊን ረጉሌሽን ስምምነት መሰረት አቅም የሌላቸው ሴት እና ህጻናት ወደመጡበት መመለስ አይቻልም። ፈረንሳይም ይህ ህግ እንዳልጣሰች ይታወቃል።    

TMP – 21/02/2019

ፎቶ: ሞንተግንቨር ስኪ ሪሶርት፡ በፈረንሳስይ ሀውት-አልፕስ በዊንተር ጊዜ  

ክሬዲት: ማይክ ዶታ/ ሸተርስባክ