ጣልያን ከአደጋ የዳኑ ስደተኞች ይዘው ወደ ሀገርዋ የሚመጡትን ጀልቦች እንደምታስከፍል አስታወቀች
ጣልያን ወደ ሀገርዋ በሚመጡት ህይወት አዳኝ ጀልባዎች ላይ ክፍያ እንዲጣል የምያደርግ ማለትዋን ተከትሎ ከተላለዩ የመብት ተሟጓች ተቋማት ክስ እየቀረበባት። በሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ማቲው ሳሊቪኒ የቀረበ አዲስ ፕሮፖዛል ከፀደቀ የምግባረ ሰናይ ተቋም መርከቦች ቅጣት ይጣልባቸዋል። ቅጣቱ የምያመጥዋቸው ስደተኞች እያንዳንዳቸው እስከ 5,500 ዩሮ ታስቦ እንዲከፍሉ የሚደነግግ ነው።
የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች ባወጡት መግለጫ እንደገለፁት ይህ አሁን ጣልያን እያወጣችው ያለ ህግ የስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂ ሰዎች መብት ክፉኛ የሚጎዳ ነው ብለዋል።
“ይህ አዲስ ህግ አጠቃላይ የናቪጌሽን ኮዱ በስህተት የሚተረጉም እና ዓለም አቀፍ የስደተኞች ህግን የሚጥስ ነው።” ብለዋል የሲ ወቹ ጂዮርጅያ ሊንዳርድ። አክለውም “የሰዎች ህይወት ወደ ክፍያ የወረደበት ሁኔታ ነው ያለው። ይህ ክፍያ ሞራላዊ እና ህጋዊ የሰዎች መብት ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው።” ብለዋል።
የሳሊቪኒ አዲስ ፕሮፖዛል እንዲወጣ ያነሳሳው የተባለው“ትልቅ እምርታ ያለው እና አንገብጋቢ” ሆኖ የተገኘው “ደስ የማይል ተግበር” ለመዋጋት መሆኑ ገልፀዋል። ህጉ ከየባህሩ የሚመጡትን ስደተኞች የት ማረፍ እንዳለባቸው ውሳኔ ለመስጠት እንድያስችል መሆኑ ተገልፀዋል።
ስደተኞችን ከሞት የምያድኑ የንግድ ጀልባዎች ደግሞ የንግድ ፈቃዳቸው ለአንድ አመት እንዲታገድ ይሆናል፤ በህጉ መሰረት።
ይህ ህግ የሊብያ የፀጥታ ሀይሎች “ለስደተኞች በቂ የሚባል የሎጂስትክስ እና የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ” ብለዋል። ይሁን እንጂ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ባለሙያዎች የሊብያ የወሰን የፀጥታ ሀይሎች በየቀኑ ከፍተኛ የሰበአዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፅሙ ይገልፃሉ። የሊብያ የወሰን ጠባቂ ሀይሎች ስደተኞች ለማዳን የሚደረጉ ኦፕሬሽኖች እንዲቆሙ መደረጉን ገልፀዋል ባለሙያዎቹ።
የተባበሩት መንግስታት ባለሙያዎች በመግለጫቸው የጣልያን ባለስልጣናት በርከት ያሉ አለምአቀፋዊ ህጎች እየጣሱ እንሚገኙ ይገልፃሉ። ለምሳሌ አንቀፅ 98 የተባበሩት መንግስታት የባህር ላይ ህግ ተጥሰዋል። በአንቀፁ ማነኛውም በባህር በሞት አፋፍ ላይ የተቸገረ ሰው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማገዝ ያስፈልጋል የሚል ይገኝበታል። የምግባረ ሰናይ ተቋማት በበኩላቸው ይህ አይነቱ ህግ ከአብዛኛው የባህር ላይ ህጎች እና አሰራሮች ውጪ ነው።
“አዲሱ እየወጣ ያለ ህግ ህጋዊ አሰራሮች የሚጥስ እንዲሁም የሰዎች ህይወት ለማዳን የማያስችል ነው።” ያሉት ደግሞ የኤምኤስፍኤፍ (MSF) ፕረዚደንት ካሉድያ ሎደሳኒ ናቸው። እሳቸው “በሽተኛ ይዞ ወደ ሆስፒታል የሚሄድ አምቡላስን እንደማስከፈል ይቆጠራል” ብለውታል።
TMP – 29/05/2019
Photo credit: ሲ ወች
Photo caption: ዘ ሲ ዎች 3 ብቸኛው በሜዲትራንያን ባህር አገልግሎት እየሰጠ ያለ የህይወት አዳኝ ተቋም ነው።
ፅሑፉን ያካፍሉ