በሊብያ ምስራቃዊ ክፍል 290 ስደተኞች ባህር ላይ ከሞት ድነዋል

በሶስት አነስተኛ ጀልባዎች ላይ ሜዲትራንያን ባህር ተሻግረው ለማለፍ ሲሞክሩ የነበሩ 290 ስደተኞች ከሞት መዳናቸው የሊብያው የባህር ሀይል አስታውቀዋል።

መይ 23 ቀን 2019 ጥዋት ላይ ከትሪፖሊ 160 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው ከዚልታን ከተማ ሁለት ጀልባዎች  የአድኑኝ  ምልክት አግኝተዋል። በመሆኑም የፍለጋ እና ህይወት አድን ፓትረሎች ባደረጉት ጥረት 203 ስደተኞች በአነስተኛ ጀልባ ተሳፍረው በመሄድ ላይ እያሉ ባጋጣመቸው አደጋ ከሞት አድኖዋቸዋል።

በተመሳሳይ ቀን ከሰዓት በኋላ ከትሪፖሊ 50 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሌላ የህይወት አድን ምልክት የተገኘ ሲሆን ጀልባዋ ተሰባብራ ባህር ላይ እየተንሳፈፈች ስደተኞቹ ደግሞ በጀልባዋ ስባሪ እና ውሃ እና ነዳጅ ይዘው በነበሩ ኮንታይነሮች ላይ እየተንጠላጠሉ በሞት አፋፍ ላይ ተገኝተዋል። በመሆኑም በዚህ ጀልባ ስድስት ሴቶች እና አንድ ህፃን የሚገኙባቸው 87 ስደተኞች በህይወት ተርፈዋል።

ህገወጥ ስደተኞቹ በተንሳፋፊ እና በተሰባበሩ ጀልባዎች ሲሆዱ ነው ያገኘናቸው። በህይወት አድን ግብረ ሀይል ናቸው በሁለት ጀልባዎች ሆነው ሲሄዱ ከአደጋ ሊድኑ የቻሉት።ብለዋል የወሰን ጥበቃ ቃል አቀባዩ ጀነራል አዩብ ቃሲም። የጀርመኑ የግብረ ሰናይ ተቋም ወች በበኩሉ ለህይወት አድን ስራ የሚጠቀምበት አየርክራፍት በሶስት ጀልባዎች ሆነው ሲሄዱ መያዛቸው ገልፀዋል።

እነዚህ ስደተኞች ከሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማልያ፣ ግብፅ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ሴኔጋል እና ባንግላድሽ መሆናቸው ታውቀዋል። ስደተኞቹ በሊብያ የሊብያ ህገ ወጥ ስደት መከላከል ክፍል ተይዘው በትሪፖሊ ማቆያ ማእከላት ተጠልለው የነበሩ ናቸውም ተብለዋል።

የጀነራል ሃፍታር ጦር ውግያ ከማስነሳቱ ጊዜ ጀምሮ በሊብያ ዋና ከተማ ውስጥ በተለያዩ የስደተኛ ማቆያ ማእከላት   የሚገኙ ስደተኞች   እየተካሄደ ባለው ከፍተኛ ውግያ ውስጥ ታግተው  መቆያታቸው ይታወሳል። ጦርነቱ የተጀመረው በትሪፖሊ ከተማ አፕሪል 4 ቀን 2019 ላይ  ነው።

የሊብያ ባለስልጣናት ስደተኞኞችን የተጋጋለ ጦርነት ባለው አከባቢ እንዲቆዩ ማድረጋቸው በእጃቸው ያሉ ንፁሃን ዜጎች ላይ ከፍተኛ የህይወት ፈተና እንዲገጥማቸው እያደረጉ ነው።ብለዋል በአሚኒሲቲ ኢንተርናሽናል የመካከለኛ ምስራቅ እና የሰሜናዊ አፍሪካ ተጠሪ የሆኑት ማግደሊና ሙጋርቢ።  

ከጦርነት ቀጠናው እንዲወጡ የምያስችል ማነኛውም አይነት መፍትሄ እና እርምጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል። አንዳንድ በጦርነት ስራ ውስጥ በግዴታ እየተሳተፉ ያሉ ስደተኞችም ዓለም አቀፍ ህግ የሚጥስ ስለሆነ መቆም አለበት።ሲሉም አክለዋል።

TMP – 31/05/2019

Photo credit: ወች   / ትዊተር

Photo caption: የሲወች አየርክራፍት መይ 23 ቀን 2019 ላይ የሊብያ የህይወት አድን አካል ስደተኞችን ከሞት ማዳኑአስታውቀዋል