ስደተኞችን ጭና ስትጓዝ የነበረች በሊቢያ ጠረፍ ጠባቂዎች ችላ በመባልዋ በጭንቅ ላይ ነች
ከፕላስቲክ የተሰራችውና 100 ስደተኞችን አከባቢ ይዛ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ የድረሱልኝ ጥሪ ብታቀርብም በሊቢያ ጠረፍ ጠባቂ ባለስልጣኖች ችላ መባልዋን ተከትሎ በሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ ለሰዓታት በጭንቀት ላይ መሆንዋ ከዮሮነውስ የተገኘው ዘገባ አመለከተ::
ፓይሎት ቮለንታሪስ (የበጎ ፍቃደ ፓይሎቶች) በመባል በሚታወቁት በአየር ላይ በመሆን ለእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ በመስጠት የሚታወቁት አባላት ከመስከረም 16 ቀን የነፍስ አድን ዘመቻ በባህር ላይ አሰሳ ሲያደርጉ ጀልባዋን ለማየት እንደቻሉ ታውቋል::
“ በዛሬው እለት የኛ የአየር አሳሽ ቡዱን አንዲት የፕላስቲክ ጀልባ 100 ሰዎችን ጭና ባህር ውስጥ በተስፋ መቁረጥ ላይ ያለች መሆንዋን ሮም በሚገኘው ማሪታይም የባህር ጠፈር የነፍስ አድን ዘመቻ ቡዱን አባላት ብናሳውቅም ለሊቢያ ባለስልጣናት ከመንገር ከሊቢያ ባለስልጣናትም ምንም ዓይነት መልስ ባለመሰጣታቸው እነዚህ ስደተኞች መቼ እንደሚድኑ ኣናውቅም “ ሲሉ እንዲደረግ በመጠባበቅ ላይ ናቸው::
በባህር ላይ የሚገኙት ስደተኞች ለነፍስ አድን በዱኖች ከተነገራቸው ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ ለ8 ሰዓታት እንዲቆዩና ከዛም እንደዳኑ ታውቋል:: በመጨረሻም ሁለቱም ፓይሎቶች ጀልባዋ በሊኒያ ጠፈር ጠባቂዎች ከመስጠም እንደ ዳነች መልእክት ደርሷቸዋል::
ከሰኔ ወር ጀምሮ; ሊቢያ የአከባቢውን ሰፊ የባህር ጠረፍ ቦታ አሰሳና ነፍስ ለማዳን ሃላፊነት መውሰድዋና አብዛኛው ከሰሜን አፍሪቃ እሰከ አውሮፓ ያለው ቦታ ይህችን ጀልባ የተገኘችበት አከባቢም ጭምር እንደሚሸፍን ታውቋል::
እንደ ነፍስ አድን ቡዱኑ ዘገባ ከሆነ ሰዎች ከመዳናቸው በፊት በደርዘን የሚቆጠሩ የመልእክቶች መለዋወጥ እንዳደረጉና ታውቋል::
TMP – 24/10/2018
ፎቶ; ፓይለትስ ፖለንታሪስ/ ትዌተር። ፓይሎቶቹ አውሮፕላን የባህሩን አድማስ ስትቃኝና በጭንቀት ላይ ያሉት ስደተኞች ሲመለከቱ።
ፅሑፉን ያካፍሉ