ለሦስተኛ ጊዜ ለዓለም አቀፋዊ ሕገ-ወጥ ማዟዟር ጥቃት ምክንያት የሆኑት ሕፃናት

ከ18 ዓመት በታች የሆኑት ሕፃናትች ስደተኞቸ የሜዲቴራንያን ባህርን በአስተላላፊዎች ጀልባ ላይ፡፡ ፎቶ፡ ጊደዮን ኢማድኖ/ሪፖርተር

በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ፈንድና (UNICEF) ኢንተር – ኤጀንሲ ኮኦርዲናሽን ግሩፕ ኤገይንስት ትራፊኪንግ (ICAT) ሪፖርት መሠረት ሕፃናት ስደተኞች በሰው አዘዋዋሪዎች እጅግ በጣም ተጎጂዎች ሆነው እየቀጠሉ ናቸው፡፡

30 July/ሓምሌ በሚከበርበት የዓለም የሰዎች ማስተላለፍ ቀን ሁለቱ ድርጅቶች ማለት (UNICEF) ዩኒሴፍና (ICAT) ኢካት የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የሕፃናትን ደህንነት በሚጠብቅ መልኩ የመንግሥት ፖሊሲዎችንና የጠረፍ ተሻግሮ መሄድ መፍትሄ መተግበር እንዳለበት አጥብቆ አስገነዘበ፡፡ በሁለቱ ድርጅቶች አባባል 28% ለዓለም አቀፋዊ ሕገ-ወጥ ማዟዟር ጥቃት ምክንያት የሆኑት ሕፃናት ናቸው ብለዋል፡፡ ሁኔታው ለሕገ-ወጥ ማዟዟር ጥቃት ምክንያት የሆኑት ሕፃናት እስከ 64 እና 62 መቶኛ የሚደርሰው በሰሃራ በታች አፍሪካ፣ መካከለኛው አሜሪካና ካሪቢያን እጅግ በከፋ መልኩ ነው፡፡

የዩኒሴፍ ዳይሬክተር፣ ሄንሬታ ፎረ፣ የሰዎች ሕገ-ወጥ ዝውውር በዓለም ላሉት በሚልዮን ለሚቆጠሩት ሕፃናት ተጨባጭ ስጋት ነው፣ በተለይም ያለአንዳች ጥበቃና ቤቶቻቸውን ለቅቀው በሚሄዱት ሕፃናትብለዋል፡፡   

በመላው ዓለም ያሉት መንግሥታት ለችግሩ መፍትሔ ለመስጠት ባለመተባበራቸው በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ማህበራት እየተስፋፉ መምጣታቸውና በመቶ ሺዎች ስደተኞችን በመበዝበዝ ትርፍ በማግኘት ላይ መሆናቸው የተባበሩት መንግሥታት ገለፀ፡፡

የሰዎችን ማዘዋወር ተግባር ባልተስተካከለ፣ አለመረጋጋትና ግጭት ባለበት የሚመገብ እጅግ መጥፎ ወንጀል ነው፡፡ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሚያገኙት ትርፍ ከሰዎች አጉል ተስፋዎችና ተስፋ መቍረጥ ነው፡፡ እነርሱ ተጎጂዎችቸውን በማደን መሠረታዊ መብቶቻቸውን ይዘርፏቸዋልብሎ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሓፊ፣ አንቶንዮ ጉቴረዝ ገለፁ፡፡

የሰዎችን የማዘዋወር ሥራ ብዙ መልክ ያለውና ወሰን ወይም ጠረፍ የሌለው ነው፡፡ ሰዎች አዘዋዋሪዎች ብዙ ጊዜ ቅጣት ሳይቀጡ ነው የሚሠሩት፣ የሚሠሩት ወንጀልም በቂ ትኩረት አይደረግበትም፣ ይህ አሠራር መቀየር አለበትዋናው ፀሓፊው በንግግራቸው ላይ ስጨምሩ የተናገሩት፡፡ ዓለም አቀፉ አካል አዘዋዋሪዎቹ ወደ ሕግ ለማቅረብና ለተጠቂዎቹም የመከላከልና የማገዝ ሥራ እንደሚሠራገልፀዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ክፍል መግለጫ መሠረት በ2017 በመላው ዓለም ያሉት ስደተኞች ሕፃናት ቍጥር በግምት 36 ሚልዮን መድረሱንና ከዚሁም 29 መቶኛው አፍሪካ የምታስተናግደው ነው፡፡

TMP – 27/08/2018