ሀንጋሪ ለስደተኞች ደጋፍ በሚሰጡት ሰዎች ላይ ቅጣት ልትጥል ነው።

የ ሀንጋሪ መንግስት ለስደተኞች ሰብአዊ ድጋፍ በሚሰጡት ሰዎች ወይም አካላት ላይ ቅጣት የሚጥል አዲስ አነጋጋሪ ህግ ለመቅረፅ እየተዘጋጀ መሆኑን እየተነገረ ነው።

ቢቢሲ እንደገለፀው ይህ ለመፅደቅ በዝግጅት ላይ ያለ አዲስ ህግ “ ስቶፕ ሶሮስ አክት (Stop Soros Act)” በመባል የሚታወቅ ሲሆን ጥገኝነት ለሚጠይቁ ስደተኞች መንገድ የሚነግሩ፣ ምግብና ውሃ የሚያቀብሉ፣ የህግ ድጋፍ የሚሰጡ ባጠቃላይ የተለያዩ ሰብአዊ ድጋፍ የሚሰጡ አካላትን የሚወነጅል ህግ ነው።

የኦርባን ፓርቲ መንግስትን በተደጋጋሚ የሚወቅሰው ሀንጋሪ ሀገው ውስጥ መሰረቱ ያደረገ ጆርጅ ሶሮስ የተባለ የሰብአዊ ድጋፍ እንቅስቃሴ ለተጨማሪ ችግር እየዳረገነ ነው በሚል ነው። ምክንያትም ወደ አውሮፓ ሀገር በሚሄዱ ሙስሊም ስደተኞች ላይ ያለው አቋም መሆኑም ይገልፃል። ለህጉ መፅደቅ አንድ ምክንያትም ይሄንን እንቅስቃሴ ሆነዋል።

ረቂቅ ህጉ ባለፈው ጁን 5 ላይ በሀገሪቱ ፓርላማ ክርክር የተደረገበት ሲሆን የኦርባን ፓርቲ በሁለት ሶስተኛ አብላጫ ድምፅ ህጉ መፅደቅ እንዳለበት በስምምነት ተደርሰዋል። በዚህ ሁነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የእሳቸው ደጋፊዎች የስደተኞች አቋም ሊቀየር ነው ማለት ነው።

በዚህ ሳምንት በአዲሱ ህግ ላይ ተጨማሪ ውይይት በማድረግ የህጉ መፅደቅ እውን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። እውን የሚሆንበት ምክንያትም ቀደም ብሎ የኦርባን ፓርቲ አብላጫ ድምፅ ማግኘቱ ተከትሎ አሁንም ይሄንን ድምፅ ሚዛን ሊደፋ ስለሚችል ነው። እናም “ስቶፕ ሶሮስ አክት” ህግ ሊሆን ነው።

ሀንጋሪ ከአሁን በፊት በጣልያን እና ስፓይን መጠልያዎች ያሉ 160, 000 ሶርያውያን እና ኤርትራውያን ስደተኞችን፤ የ አውሮፓ ህብረት ወደ አውሮፓ ሀገራት ለማከፋፈል ያወጣውን እቅድ ስትቃወም የቆየች መሆኗ ይታወቃል።

እንደ አልጀዚራ ዘገባ ከሆነ የኦርባን ፓርቲ የአውሮፓ ህብረት እንደዚህ አይነቱ ስደተኞችን የማከፋፈል ስርዐት እንደገና ሊያየው ይገባል ባይ ነው።

ቲኣርቲ በዘገባው ሂሊሲንኪ ኮሚቴ እና አመኒስቲ አንተርናሽናልን ጨምሮ ዋነኛዎቹ የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት ረቂቅ ህጉ የሀገሪቱ ህግ ሆኖ እንዳይፀድቅ ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ነው። ምክንያቱም ረቂቁ ህግ የሀገሪቱ ህግ ሆኖ ከቀጠለ እነዚህ ተቋማት ወንጀለኞች ያደርጋልና።

ማርታ ፓራዳቪ ከዘሂሊሲንኪ ኮሚቴ እንዳአለችው “እንደዚህ አይነት ህግ የበለፀጉ በሚባሉ ሀገራት፣ በአውሮፓ ህብረት እናም የህግ ሉአላዊነት በተከበረበት ምድር ቦታ የሌለው ነው።”

ረቂቅ ህጉ እንደሚለው በስደተኞች ድጋፍ ላይ የተገኘ ማነኛውም ሰው እስከ አንድ አመት ፅኑ እስራት የሚደርስ ቅጣት የሚጥል ነው።

TMP – 29/06/2018