በሊብያ ወደ ሌላ ቦታ መዛወር እንፈልጋለን በሚል ስደተኞች ዐመፅ አስነሱ
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በአብዛኛው የሚገኙባቸው ስደተኞች ሊብያ የሚገኙ ስደተኞች ማእከል ላይ የአመፅ ሰልፍ አስነሱ።
እነዚህ ስደተኞች እንደሚሉት ከሆነ ወደ አውሮፓ ለመሻገር በማሰብ ሊብያ ላይ የተያዙት በ2015 ነው። ይሁንና እነዚህ 120 የሚሆኑ ስደተኞች በሊብያ ተይዘው ወደ ህገ ወጥ ደላሎች ሊሸጡ መሆናቸው ነው የሚናገሩት። በሊብያ የፀጥታ አካላት ከመሸጥ የዳኑ ቢሆንም እንዳይዘረፉ፣ ቶርች እንዳይደረጉ እና በበሽታ እንዳያዙ ባላቸው ከፍተኛ ስጋት ምክንያት በተቻለ ፍጥነት ሊብያን መልቀቅ ይሻሉ።
የታጎሩበት የስደተኞች ጣብያ በር በመበርገድ ይሄንን ፍላጎታቸው እንዲፈፀም ለየተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) በሰለማዊ ሰልፍ መልክ ጥያቄአቸው አቅርበዋል።
ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ በሩን ሰብረው የወጡት ስደተኞች ተሰልፈው በ120 ኪሎሜትር ርቀት ወደ የምትገኘው የትሪፖሊ ከተማ ተጉዘዋል። አብዛኞቹ ስደተኞች ወደ አውሮፓ በሚደረግ ጉዞ በሊብያ ሀገር ውስጥ ሚኒስትር የህገ ወጥ ስደት መከላከል መምርያ ሰራተኞች ወይም ደግሞ በሊብያ ባህር ላይ በተለያዩ የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት ተይዘው ወደ ማእከሉ የመጡ ናቸው። እነዚህ ማእከላት ታድያ ብዙ ጊዜ ለህይወት የማይመቹ ፣ በጣም የተጨናነቁ እና በቂ የምግብ፣ የውሃ እና የህክምና አቅርቦት ያልተሟላላቸው ናቸው።
አለም አቀፉ የስደት ተቋም (IOM) እንደዘገበው ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በስደተኛ ማቆያ ማእከላት ያለ የስደተኞች ቁጥር በእጥፍ ጨምረዋል ። የፀጥታ አካላት ከተለያዩ በሰው ልጅ ንግድ ጋር የተሰማሩ አካላት ጋር በመተባበር፤ በሊብያ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል እየተፈፀመ በመሆኑ በተቻለ ፍጥነት ሊብያን ለቀው ለመውጣት ይፈልጋሉ።
ይህ ሁነት ብዙ ሰዎች እንድያዩት በመፈለግ በማቆያ ማእከላቱ ያሉ ስደተኞች እሁድ ኦገስት 12 ላይ ሁኔታው የምያሳይ የተለያየ የፎቶ እና ቪድዮ መረጃዎች ሲለጥፉ ተስተውለዋል።
ስሙ አማን እንደሆነ ለፍራንስ24 የገለፀው የሀያ ሁለት ዕድሜው ኢትዮጵያዊ ሰልፈኛ እንደገለፀው “ላለፉት ሶስት ወራት ሙሉ ቃሳር ቤን ጋሽር በተባለችው ቀበሌ (ከትሪፖሊ ወደ ደቡብ በ25 ኪሎሜትር ገደማ ርቀት የምትገኝ) ታሰረን ቆይተናል።” አማን አክሎ እንደገለፀው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ሄዶ ጎብኝተዋቸዋል። ስማቸው እና መይ ወር ላይ ወደ ቦታው የገቡበት ቀን ሁሉ መዝግቦዋቸዋል። “ይሁንና ከዛ ቀን ጀምሮ እስከ አሁን የሰማነው ነገር የለም” ብለዋል።
“ዓማፅያኑ ለሰው ልጅ ነጋዴዎች ሲሸጡን ነበር። እነዚህ ሰዎች በኤሌክትሪክ እየታገዙ ቶርቸው እያደረጉን በፊልም ቀርፀው ወደ ጓደኞቻችን እና ቤተሰቦቻችን እየላኩ ገንዘብ ይወስዱ ነበር። ለማነኛውም ነገር ከ1ሺ እስከደ 6 ሺ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ይጠይቃሉ።” ብለዋል አማን። “የባሰውን ነገር ደግሞ ያ ሁሉ ነገር ፈፅመው እና ገንዘብ ተቀብለውም ቢሆን አይለቁንም።”
“አሁን ይሄንን ሲኦል ተሎ መልቀቅ እንፈልጋለን። ወዴት እንሂድ የሚለውን ነገር ጉዳያችን አይደለም። ግን መውጣት አለብን። ለዩኤንኤችሲአር የምንለምነው ያለነውም ይሄን ነው። መልቀቃችን እንድያፋጥንልን እና ከመጥፋት እንድያድነን!”
በአሁን ሰዐት ያለ የስደተኞች ቁጥር ስደተኞች ሊያርፉባቸው ከተቋቋሙት የስደተኛች ማእከላት ቁጥር በላይ ነው። ዩኤንኤችሲአር እንደሚለው ከሆነ ቦታ የሚፈልጉ የስደተኞች ቁጥር በ2009 ብቻ 1.4 ሚልዮን ደርሰዋል።
TMP – 09/09/2018
ፎቶ: ኦገስት 12 ላይ የተካሄደውን የዐመፅ ሰልፍ ከምያሳይ በፌስቡክ ከተለቀቀ ቪድዮ ስክሪንሽት ተደርጎ የተወሰደ
ፅሑፉን ያካፍሉ