በሊብያ ያለ ጦርነት ወደ ትሪፖሊ እየተቃረበ በመምጣቱ ምክንያት የታገቱትን ስደተኞች አደጋ እያንዣበባቸው ነው ተባለ

በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በሊብያ በተቃራኒ ቡድኖች እየተካሄደ ባለ ውግያ ምክንያት አጣብቂኝ ውስጥ እንዳሉ ተገልፀዋል። ውግያው ወደ ከተማው እየተቃረበ ነው ተብለዋል።

በጀነራል ካሊፋ ሃፍታር የሚመራው የሊብያ ብሄራዊ ሰራዊት እና የተባበሩት መንግስታት እውቅና የሰጠው ሊብያ ላይ ማእከሉ ባደረገ የመንግስት ሰራዊት መካከል እየተደረገ ባለ ውግያ ምክንያት በርካቶች የሞቱ ሲሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል።  በውግያው ቢያንስ 75 ሰዎች መሞታቸው እና ሰለማዊ ዜጎችን ጨምሮ 323 ደግሞ መቁሰላቸው የተባበሩት መንግስታት ለሮይተርስ ገልፆለታል። 

እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፃ ከሆነ ሊብያ ውስጥ 6,000 በላይ በስደተኛ ማእከላት ያሉ ሰዎች   ከኤርትራ፣ ሶማልያ እና ሱዳን የመጡ ሲሆን 600 በላይ ህፃናት ይገኙባቸዋል።  እነዚህ ስደተኞች በጣም በተጨናነቁ ማእከላት፣ ረሀብ እና እስር በተደራረበበት ሁኔታ ውስጥ በተላለዩ አካላት የሚያዙዋቸው የጦር ሰዎች ተከበው እየኖሩ ነው።

አልጀዚራ እንደዘገበው የታገቱት ስደተኞች ያለ እህል ውሃ ተዘግተው ይኖራሉ። አብዛኛዎቹ ደግሞ የጋለ የተኩስ ልውውጥ ባለበት አከባቢ ነው ያሉት።  ሰራዊቱ እያየነው ነው።ብለዋል ቃሲር ቢን ሃሸር በተባለ የስደተኞች ማቆያ ውስጥ ያለ አንድ ስደተኛ ለዜና አውታሩ በሰጠው ሀሳብ።     የምግብ ስቶሩ ባዶ ነው።ሲልም አክለዋል። ጨምሮምጦርነቱ አሁንም እየቀጠለ ነው። ውሃ እና ኤሌክትሪክ ሲቲ ተቋርጠዋል። ብለዋል።

ሌላ ለአልጄዚራ ሀሳቡ የሰጠ ስደተኛ ከዚህ ወስደው ሊሸጡን ይችላሉ።ሲል ስጋቱ ገልፀዋል። ሁሉም ዕብዶች ናቸው። በጣም አስጊ ሁኔታ ውስጥ ነን ያለነው። ወዴት መሄድ እንዳለብን አናውቅም። ሁሉም እዚህ ያለ ስደተኛ ሮጦ መሸሽ ይፈልጋል። ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነው ያለነው። አእምሮአችን  በተስፋ እጦት ተይዘዋል። ብለዋል።

በትሪፖሊ ከተማ ደቡባዊ ምስራቅ ክፍል በሚገኝ አይን ዛራ በተባለ የስደተኞች ማቆያ ማእከል ታስሮ የተገኘ አንድ ስደተኛ ደግሞ አብሮአቸው የነበሩ የጥበቃ ሰዎች ትተዋቸው ሄደዋል፤ ምግብ የሚባል ነገርም እንደሌለ  ገልፀዋል።

የዩኤንኤችሲአር ቃል አቀባይ ባባር ባሎችየጥይት ድምፅ ይሰማሉ። ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ ናቸው።ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ አፕሪል 9 ቀን 2019 ላይ 150 ስደተኞች አቅራብያው ወደሚገኝ አገልግሎት መስጫ ማእከል ወስደዋቸዋል።

የአገልግሎት ማእከሉ ስራ አስከያጅ ለሮይተርስ እንደገለፁት ኤፕሪል 10 ቀን 2019 ላይ ለስደተኞቹ ዋስትና እና ድህንነተ ሲባል በራቸው ክፍት አድርገዋል።

በሊብያ እስከ 700,000 የሚገመቱ ስደተኞች ሜዲትራንያን ባህር ለመሻገር አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተይዘው በማቆያ ማእከላት እንዳሉ ይነገራል። የህይወት አድን መርከቦች በሌሉበት የሚደረግ ያለ ጉዞ ስለሆነ ብዙ ስደተኞች በሊብያ የፀጥታ ሀይሎች እየተያዙ ይታሰራሉ።   ባለፈው የፈረንጆች አመት የሊብያ የፀጥታ አካላት   ወደ 15,000 የሚጠጉ ስደተኞች ተይዘው እንዲመለሱ ተደርገዋል። 2019 የፈረንጆች አመት ከገባ ወዲህ ባሉ አራት ወር ውስጥ  1,073 ስደተኞችን ተይዘው እንዲመለሱ አድርጋለች፤ ሊብያ። .

TMP – 19/04/2019

ፎቶ ከሬዲት: ሳራ ክሬታ/ኤምኤስኤፍ

የፎቶ መግለጫ: አንድ ህይወቱ የተረፈ ስደተማ በካሆም የማቆያ ማእከል በተዘጋ በር አሸልኮ ሲያይ፤ ሴፕተምበር 2018