ስደተኞች ጀልባ በመጥለፍ ወንጀል ተያዙ

ሶስት በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ለመሄድ ሲሞክሩ የተያዙ ስደተኞች የቱርክ ጀልባ ለመጥለፍ በሞመከራቸው ምክንያት በማልታ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

የጀልባው ቡድን፤ ወንዶች፣ ሴቶች እና  ህፃናት የሚገኙባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ከባህር እያዳኑ ወደ ሊብያ ይመልሳሉ። ይሁን እንጂ ኢል ሂብሉ የተባለው አነስ ያለ የዘይት ታንከር ያለው ጀልባ ይዞዋቸው ሲመለስ በቶርቸር እና የማቆያ ማእከላት ስቃይ ወደተጋለጡባት ወደ ሊብያ እየመለሳቸው መሆኑ ባወቁ ጊዜ ጀልባውን ለመጥለፍ ሞክረዋል። በመጨረሻም ጀልባው በሀይል ማልታ ላይ እንዲቆም ሆነዋል።

ካፕቴኑ እንዳለው ከመገልበጥ አደጋ የታደጋቸው አንድ የአውሮፓ የሚሊተሪ አየር ሲሆን ብዙ ስደተኞች ከአደጋ እንዲድኑ ምክንያት ሆነዋል። አፋጣኝ ድጋፍ ለማግኘትም የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርገዋል። 

ሰዎቹ ከጀልባዋ ማውረድ ጀመርኩኝ። ይሁንና ስድስት ሰዎች አንዘልም ብለው እምቢ አሉ። ፍራቻቸው ወደ ሊብያ እንዳይመለሱ ነው።ብለዋል።

ካፕቴኑ እንዳለው እነዚህ ስደተኞች ትሪፖሊን በዓይናቸው እስክያይዋት ድረስ ጀልባዋ ወደ ሊብያ አቅጣጫ እንዳዞረች እንኳን አላስተዋሉም ነበር። እሱ እንዳለውስደተኞቹ ወደ ሊብያ የመመለስ ጉዳይ በጣም ጠልተውት ነበር። 

እዛ የነበረ ብረት እያነሱ የጀልባዋ አካላት በመምታት ተቃዉሞአቸው አሰሙ። ወደ ሊብያ መሄዱ ከቀጠልን  ጀልበዋ እንደሚሰባብርዋት ማስፋራራት ጀመሩ። አስፈሪ ነበር። ስለጀልባዋ አደለም የጨነቀኝ። እዛ ስለነበሩ የጉዞው ቡድን እንጂ።ብለዋል ካፕቴኑ።

ካፕቴኑ እንዳለው ወደ ሊብያ የባህር ሀይል በመደወል ጉዞው እንደቀየረ ነግሮዋቸዋል። እሱ እንዳለውሊገድሉን ነው።  ወደ ሊብያ ከቀጠልን ይገድሉናል። እናም የሊብያ ጉዞው ትነዋል።እንዳላቸው ተናግረዋል።

ጣልያንም ማልታም የጀልባዋ ወደቦቻቸው ላይ ማረፍ አልፈቀዱም ነበር። ይሁንና ልዩ ሀይል ተልኮ ጀልባዋ በመክበብ እና ሰራተኞቹ በመጠበቅ በማልታ ወደብ ላይ እንድትቆም ተደርጋለች።

ዜግነታቸው ከጋና እና አይቬሪኮስት የሆኑት በዚህ ጠለፋ ላይ የተሳተፉ ሶስት ስደተኞች ወንጀሎች ሆነው ከተገኙ ከባድ የእስር ቅጣት እንደሚጠበቅባቸው ተነግረዋል።   እነዚህ ተጠርጣሪዎች የሚከፍሉት ነገር ስሌለ እና በማልታ የምያዉቁት ሰው ባለመኖሩ ምክንያ ግኑኝነት እንዳይኖራቸው ሆነዋል።

የጣልያኑ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ማቲው ሳሊቪኒ ጀልባዋ በማልታ ወደብ እንድታርፍ በማድረጉ ለማልታ የመከለካያ ሀይል አማኳሽተዋል።እነዚህ ሰዎች ሲሰደዱ የተያዙ የተቸገሩ አካላት ሳይሆኑ ሀገር የምያጠፉ ምስጦች ናቸው። ጣልያንን ማየት የሚችሉት በቴሌስኮፕ ብቻ ነው።ብለዋል ሳሊቪኒ፤ ስደተኞቹ በማስመልከት በሰጡት ሀሳብ። 

እሳቸው እንዳሉትየስደት ጉዳይ በወንጀሎች እጅ ወድቀዋል። እናም አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ይህ ጉዳይ ማስቆም ያስፈልጋል።ብለዋል። ያጋጠመውን ሁነት ደግሞበባህር ስራዎቻችን ላይ ካጋጠሙት ልዩ የስደተኞች የባህር ላይ ውንብድና አንዱሲሉ ገልፀውታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ እንደ ወች ያሉ በጎ አድራጊ ድርጅቶች የማቲው ቃል ይቃወማሉ። ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ማልታ ልያገኙት የቻሉት በኋይል ተወስደው ነው እንጂ ለዝርፍያ አይደሉም በማለት ይሞጉታሉ። የተቃወሙትም ቶርችር እና ስቃይ ወደአሳለፉበት አንሄድም ነው ያሉት ተብለዋል። 

በሊብያ ያለ የስደተኞች ማእከል ያለበት ከፍተኛ ችግር በየጊዜው እየተሰነደ መጥተዋል። ይሄንን ስራ የምያከናውኑ የሰብአዊ መብት ተማጓቾች፣ የተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ኤጀንሲዎች መሆናቸው ለማወቅ ተችለዋል።   ስደተኞች በተለይ ደግሞ ለተቀነባበረ የእስር፣ ቶርቸር፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ ጠለፋ፣ የሀይል ጥቃት፣ ባርነት እና ግድያ ጥቃቶች እንደሚጋለጡ ተነግረዋል።በባህር ላይ በሞት አፋፍ ያሉትን ስደተኞች ወደ ሊብያ መመለስ ጨካኝነት ነው።ብለዋል ወች በመግለጫው።    

2018 ብቻ የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች  ወደ 15,000 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ማዋል ችለዋል።

TMP – 10/04/2019

Photo: ስቴቭ ኢስትቫኒክ /ሻተርስቶክ. ትንሽ ታንከር በማልታ ቫሌታ ወደብ ላይ