ወደ እንግሊዝ ለመግባት የሞከሩ ኤርትራውያን ስደተኞች በቁጥጥር ስር መዋለቸው ተሰማ

ይህ 18 ሰዎች የያዘ የኤርትራውያን ስደተኞች ቡድን ማርች 13 ቀን 2019 በትልቅ ተሳቢ መኪና አመካኝነት ወደ እንግሊዝ  ሀገር ለመግባት ሲሞክር በቁጥጥር ስር ሊውል ችለዋል። ስደተኞቹ የተያዙት በተለመደው የተሽከርካሪ ፍተሻ ግዜ የጀርመን ባለቤትነት ባለው ተሳቢ መኪና ውስጥ ነው።   

የኬንት የተባለች ከተማ ፖሊስ እንደገለፀው “ሎንደን M26 በተባለው መኪና ብዙ ሰዎች ተጭነው ነበር።”

ኤርትራውያን መሆናቸው የገለፁ 18 ሰዎች፣ 11 ወንዶች፣ ስድስት ሴቶችና አቅም የሌላቸው ሰዎች ናቸው። በዚሁ ሙከራ የተያዙ አቅም የሌላቸው የህክምናና ሌሎች አቅርቦቶች ወደ ሚገኝበት ቦታ ተወስደዋል።” ብለዋል የሀገሪቱ የጠረፍ ሀይል ቃል አቀባይ።  አክለውም “ሁሉም ውሳኔዎች በእንግሊዝ የስደተኞች ህግ ስር ይከናወናሉ።” ብለዋል።  

በዚህ አመት ሌላ ተመሳሳይ ኬዝም በኤርትራውያን ስደተኞች ተመዝገብዋል።   

በጥር ወር 27 ኤርትራውያን፣ ሱዳናውያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚገኙበት አንድ ቡድን በጭነት መኪና ተደብቀው ወደ እንግሊዝ ለመግባት ሞክረው ነበር። ፖሊስ እንዳስታወቀው “ህይወት አደጋ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል” የሚል መረጃ ከደረሰው በኋላ መኪናዋ እንድትቆም በማድረግ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።    

የሚደርሱንን መረጃዎች ጉዳዩ ትኩረት እንድንሰጠው አድርገዉናል። እናም ቀልጣፋና ትክክለኛ እርምጃ ለመውሰድ ተገድደናል።” ብለዋል ምክትል ኮንስታብል ኒክ ባከር። በመጨመርም   “የ42 ዓመቱ መኪናዋ ስያሽከረክር የነበረ አድራሻው እስካሁን ያልታወቀ አሽከርካሪ በህገ ወጥ መንገድ ሰዎች ወደ እንግሊዝ እያስገባ ነው በሚል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል።  

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የሚሰማሩ ሰዎች በእንግሊዝ ሀገር ከፍተኛ ቅጣትና እስር ይበየንላቸዋል።  ለምሳሌ ማርች 2019 የጭነት መኪና የያዘ አንድ ግለሰብ 20 ስደተኞችን ደብቆ በመጫን ወደ እንግሊዝ ለማስገባት ሲሞክር በመያዙ 12 ሺ ፓውንድ ሊቀጣ ችለዋል።  ፌቡራሪ 2019 ደግሞ በተቀናጀ ወንጀል ስራ ውስጥ መግባታቸው የተረጋገጠ ስድስት ሰዎች  የ27 ዓመት እስር ሊፈረድባቸው ችለዋል።  የተያዙት አራት ቬትናማውያን ወደ እንግሊዝ በጀልባ ለማስገባት ስለተያዙ ነው። በ2018 መሰከረም ደግሞ በእንግሊዝ ቻናል ሰዎችን በማሳለፍ የተጠረጠሩ ሰባት ሰዎች የ48 አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።     

በድቡሊን ሬጉሌሽን መሰረት እያንዳንዱ ስደተኛ አሳይለም መጠየቅ ያለበት መጀመርያ እግሩ በረገጠበት የአውሮፓ ሀገር መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም አብዛኛዎቹ ወደ እንግሊዝ የሚገቡ ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ የመመለስ ዕድል አላቸው።

ፈረንሳይ በአውሮፓ ህብረት ሀገራት ባዮሜትሪክ መረጃውን የሞላ ስደተኛ ለመቀበል ዝግጁ ነች። ይህ ዩሮዳክ በመባል የሚታወቅ ባዮሜትሪክ ዳታ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የአንድ ስደተኛ አጠቃላይ መረጃ፣ በምን ምክንያት እንደገባ ወዘተ የሚገልፅ ዝርዝር ሀሳብ ማለት ነው።

በ2018 ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ በትናንሽ መርከቦች በእንግሊዝ ቻናል አድርገው   ለማለፍ የሞከሩ ስደተኞች እስከ ጃንዋሪ 2019 ወደ ፈረንሳይ እንዲመለሱ ተደርጓል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው በእንግሊዝ ቻናል የሚደረግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ነው።

TMP – 28/03/2019

ፎቶ: ፖወል ማርቲን/ ሻተርስቶክ. የጭነት መኪኖች በዶቨር ወደብ አከባቢ