ወደ ስፔን ከሚገባ ስደተኛ ግማሹ ቀጥታዊ ግፍና በደል እንደሚደርስበት ይነገራል

ግማሽ ቁጥር ወደ ስፔን ምድር የሚደርሱ ከአፍሪካ በሜዲትራንያን በኩል የሚጓዙ ስደተኞች ቀጥታዊ የሆነ ግፍና በደል እንደሚደርስባቸው ይናገራሉ።  

ከ1, 300 በላይ ስደተኞች እና አሳይለም ጠያቂዎችን ኢንተርቪው በማድረግ   በአለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም (አይኦኤም) የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው  በአምስቱ የግፍና በደል መለክያዎች ተመዝኖ ነው ይህ ድምዳሜ የተደረሰው። አምስቱ መመዘኛዎች አንዱ   የስደተኛው ካለፈቃዱ መያዝና ማቆየት፣ ሳይፈቅድ ማሰራት እና የተስማሙት ክፍያ አለመክፈል፣ አስገድዶ ማሰራት፣ ያለ ፈቃድ ጋብቻ እንዲመሰርቱ ማድረግና አካላዊ ጥቃቶችን ናቸው።    

የዚህ ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው በስደተኞች ላይ የሚደርስ ግፍና በደል በመጨመር ላይ ነው። ይህ የምያመለክተው የስደተኞቹ ፍላጎትና የስደት ተነሳሽነት ምን ያህል ልዩነት እንዳለ ነው።” ብለዋል የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት የስፔን ሚሽን ችፍ የሆኑት ማርያ ጀሱስ ሄረራ።   

ይህ ጥናት ቀጥታዊ  ያልሆኑት የግፍና በደል ዓይነቶችና መጠንም ለማየት ሞክረዋል። እነዚህ ቀጥታዊ ያልሆኑ በደል እና ግፎች ገንዘብ ሰጥቶ ደም መቀበልን፣ ወይም የተለያዩ የአካላት ክፍል መውሰድን፣ ደም በሀይል መውሰድ፣ የተለያዩ የአካላት ክፍል በሀይል መውሰድና አስገድዶ መድፈርን ያጠቃልላል። ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ሴቶች   ሩብ የምያክሉ አስገድዶ የመድፈር አደጋዎችን እንዳሉ ምስክርነታቸው ሰጥተዋል።   

ከፍተኛ የሆነ የስደት ፍሰት ሲታይባቸው የነበሩ ሞሮኮና አልጀርያ ከፍተኛ የሆነ የግፍና በደል ወንጀሎች ሲታይባቸው የነበሩ ሀገራት ናቸው። ሊብያና ማሊም እንዲሁ በእንደዚህ አይነት ወንጀል ከፍተኛ መጠን ያላቸው መሆናቸውን ጥናቱ አመላክተዋል።

በዚህ ጥናት ከተካተቱት ስደተኞች 38% ስፔን ለመድረስ አንድ አመት እንደፈጀባቸው የገለፁ ሲሆን ከሩብ በታች ደግሞ ለሶስት ወራት እና ከዛ በታች ለሆነ ጊዜ በመንገድ እንዳሳለፉ ይናገራሉ።  ጥናቱ ያለውን የዲሞክራፊክ ባህሪ እንዲወክል 90% ወንድ ተሳታፊዎች የተካተቱበት ነው።  

አንድ ሶስተኛ በዚህ ጥናት ውስጥ ከተካተቱ ሰዎች የህገ ወጥ ስደት መንገድ ከየት ወዴት እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ ከማሊ ወደ አልጀርያ ከዛ ወደ ሞሮኮ ከዛ በኋላ በባህር ወይም በመሬት አድርጎ ወደ ስፔን የሚደረግ ጉዞ ትልቁ ድርሻ እንደሚይዝ ተናግረዋል።  

TMP – 24/03/2019

ፎቶ: ጆቫኒ ካንሰሚ/ሻተርስቶክ. ጀልባና ህገ ወጥ ስደተኞች