አፍሪቃውያን ስደተኞች በአልጀርያ ስቃይና ባርነት እንዳጋጠማቸው ገለፁ
በአልጀርያ የነበሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች እንደ ባርያ ለአስገዳጅ ሥራ እንደተዳረጉ ሪፖርት ማድረጋቸው ከቶምሶን ሮይተር ፋውንዴሽን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሊብያ ይደረግ የነበረው መውጫ እጅግ አደገኛና አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱ፣ አልጀርያ ወደ ሜዲቴራንያን ዋና ማስተላለፍያ ሆናለች፡፡ በስደተኞቹ ላይ የግዴታና የባርነት ሥራ ይፈፀምባቸው የነበረው ቶምሶን ሮይተር ፋውንዴሽን ከአንዳንድ የበጎ አድራጊ ድርጅቶችና በአጋደዝ (ዋና ማስተላፍያ በር) ከሚገኙት የአገሩ ማሕበራት፣ በስልክና ከሁለት ተጠቂዎች ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ ባገኘው ማስረጃ ነው፡፡
ከጊኒ የሄደው ዕድሜው 21 ዓመት የሆነው ኦስማን ባህ በአልጀርያ በማያውቃቸው ጠላፊዎች ሁለት ጊዜ እንደተሸጠና በሕንፃ ሥራ ተገድዶ እንደሠራ ይናገራል፡፡ “ፓስፖርታችን ወሰዱብን፣ ደበደቡን፣ ምንም አልበላንም አልጠጣንም” “ለስድስት ወር ባርያ ነበርኩኝ” ብሎ ለቶምሶን ሮይተር ፋውንዴሽን ነገራቸው፡፡
ከቶጎ የሄደው ኦጉንጄ ታንገ ማዙ በበጎች ማደርያ እንደተኛና እንስሶቹ ከታመሙ ወይም ከቆሸሹ ይደበደብ እንደነበር ተናገሮኣል፡፡ “አንድ ትልቅ ሰይፍ ይዘው ይመጡና ሊመቱኝ ሲሉ ተምበርክኬ ይቅርታ እጠይቃለሁ ከዛ ይተዉኛል” አለ፡፡
ካለፈው ዓመት መስከረም ጀምሮ በአልጀርያ በፀረ ስደተኞች ስሜት ከፍተኛ ተቃውሞ ተንቀሳቅሶ እንደነበር የሚገልፅ ሪፖርት ወጥቶ ነበር፤ በዚያም ወቅት ከአልጀርያ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ወደ ደቡባዊ ኒጀር ወደሚገኘው ምድረበዳ ተባርረው ተጥለው ነበር፡፡
በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞችን በዘፈቀደ በመክበብና በግድ በማባረር ረገድ አገሪቱ ተከስሳ እንደነበር አንድ የRFI የየካቲት ወር ሪፖርት ያሳያል፡፡
የአልጀርያ ባለሥልጣኖች ስደተኞቹ በአገራቸው ለመቆየት መብት እንዳላቸው ለማረጋጥ ባለመፈለጋቸው በዘር አመካኝተው ሰዎችን ያስሩ እንደነበር፣ ባለፈው ዓመት የወጣው በአለም አቀፉ አምኔስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ያሳያል፡፡ ከታሰሩት ወይም ከተባረሩት ውስጥ ጥቂቶቹ ያለተመዘገቡ ስደተኞች ነበሩ፣ ሌሎቹ ግን ህጋዊ ቪዛ የነበራቸው ናቸው፡፡
እንደስደተኞቹ አባባል የአልጄርያ ባለሥልጣኖች ስደተኞችን ከጠረፉ 30 ኪ.ሜትር ራቅ ብሎ በ45 ዲግሪ ሴንት ግሬድ እና ውሃ በሌለበት ይጥሏቸው ነበር፡፡
በግንቦት ወር የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ፅ/ት ቤት አልጄርያ በመጋቢትና በሚያዝያ ስደተኞችን ቢያንስ ስድስት ጊዜ ሰፊ የማባረር ሥራ እንዳከናወነች አውግዘዋታል፡፡ ነገር ግን የአልጄርያ መንግሥት ውግዘቱን ጭራሽ ባለመቀበል እንዲያውም አልጀርያ እንደዛ ያደረገችው የዜጎቿን ደኅንነት ለማረጋገጥ ስለሆነ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶችና የአፍሪቃ አገሮች ችግሩን በመፍታት ሊረዱኝ ይገባል ብሏል፡፡
ሃሰን ካሲሚ የተባለው የአልጄርያ ከፍተኛ የአገር ውስጥ ሚኒስቴር ባለፈው ግንቦት ወር እንዲህ ብሏል፡፡ “ደቡባዊ አልጀርያ በከፍተኛ የስደት ማእበል እየተወረረች ናት”
በተጨማሪም ሃሰን ካሲሚ “አልጀርያ የሌሎች መንግሥታት ሕዝብ ላይ ኃላፍነት የለኝም” ብሏል፡፡
በ2016 በፈ.አቆ. IOM በኒጀር 6,300 የሚያህሉ ስደተኞች አብዛኛዎቹ ከአልጀርያና ሊቢያ የተመለሱ መሆናቸው ባደረገው ጥናት አረጋግጧል፡፡ በአልጀርያ ከነበሩት 65% በሊቢያ ከነበሩት 61% የሆኑት ሁከትና ስድብ ይፈፀምባቸው እንደነበር ከቶምሶን ሮይተር ፋውንዴሽን አረጋግጧል፡፡
ኒጀር ዜጎቿ በአልጀርያ ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ እንደተሰቃዩ በተደጋጋሚ ስትቃወም ብትቆይም፣ በጊኒ፣ በጋቦንና በኒጀር ያሉት የመንግሥት ሥራተኞች ማህበራት ይህንኑ ጉዳይ በአጀንዳ እንዲዝላቸው አፍሪቃ አንድነትን ሲገፋፉ ቆይተዋል፡፡
TMP – 17/07/2018
Photo credit: IOM 2016/ Amanda NERO. የፎቶው ማስረጃ፡ IOM 2016/ አማንዳ ኔሮ፡፡ ከአልጀርያ የተመለሱት ስደተኞች አጋደዝ IOM ከተባለችው የማስተላለፍያ ማእከል በመውጣት ላይ እያሉ
ፅሑፉን ያካፍሉ