መሮኮና ስፔን በሕገ ወጥ የሰው ልጅ ኣዛዋዋሪዎች ላይ ባደረጉት ትግል የስደተኞች ቁጥር እንዲቀንስ ኣድርገዋል

በዚህ አመት በሞሮኮ በኩል ወደ ስፔይን የሚገቡት የሕገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር በግማሽ ቀንሰዋል፡፡  የዚህ ምክንያትም ሁለቱ አገሮች ባደረጉት ጥረት የሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ቡዱን እንዲበታተን እንዲፈርስ በማድረጋቸው ነው፡፡

ከአለም አቐፍ የስደተኞች ድርጅት  በተገኘው ዘገባ  መሰረት በሚያዝያ ወር 820 ስደተኞች ወደ ስፔይን የገቡ ሲሆን፤ 2018 በተመሳሳይ ግዜ የገቡት ግን 1700 በላይ ናቸው፡፡ 

የሞሮኮ ባለስልጣኖች የስደተኞችን ህይወት አደጋ ውስጥ የሚከቱ የሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች የተቀናጀ አውታር ለመበታተን በትጋት እየሰሩ ናቸው፡፡  በግንቦት 2/ 2019 እኤአ የሞሮኮ ባለስለጣኖች በሰሜናዊው የሞሮኮ የባህር ጠረፍ ይንቀሳቀሳሉ ተብለው የተጠረጠሩቱን አምስት የሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች የተቀናጀ ቡዱን አባሎች በቁጥጥር ስር

እንዲውሉ አድርጓል፡፡ ባለስልጣኖቹ በብዙ የሚቆጠር ገንዘብና ለሕገ ወጥ ስደት የሚያገለግሉ ዕቃዎች እንዲሁም ስደተኞችን ወደ ስፔይን  ለማጓጓዝ የሚጠቀምባቸው ቁጥራቸው በዛ ያሉ ተሸከርካሪዎችና የፕላስቲክ ጃልባዎች ይገኙባቸዋል፡፡

ከተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ ሽፌር ሲሆን ሕገ ወጥ ስደትን  የማስተባበር የማማቻቸት  ሚና የነበረውና ከሰሃራ በታች ካሉት አገሮች የመጡት አምስት ስደተኞችን ወደ ሰሜናዊው የሞሮኮ የባህር ጠረፍ  በማጋጋዝ ላይ ነበር፡፡

በተጨማሪም ስፔይን ለአመታት እጅግ በጣም  የተቀናጀ አለም አቀፍ ሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዘዋዋሪዎች ቡዱን  እንዲበታተን ወይም እንዲፈርስ አድርጋለች፡፡ ይህ ቡዱን 350 ስደተኞች በሞሮኮ በኩል ወደ አውሮጳ እንዲገቡ አድርገዋል፡፡ ስደተኞች ዋስትና ለሌለውና አደገኛ ጉዛአቸው 20000 ዩሮ ለሕገ ወጥ የሰው ልጅ አዛዋዋሪዎች  መክፈላቸውን የስፔይን ባለስልጣኖች አስታውቀዋል፡፡

የወንጀለኞቹ ቡዱን ለመበታተን ወይም ለማፍረስ የተቻለው በዩሮ ፓል የአውሮፓ ሕብረት ሕግ ፀጥታ ማስከበር ትብብር ኤጀንስና በሞሮኮ የመርጃ አገልግሎት ትብብር መሆኑን  የስፔይን ፖሊስ ገልፀዋል በዚሁ ዘመቻ 18,000 ዩሮ በላይና በርካታ የተጭበረበሩ የሃሰት መጋጋዣ ተይዘዋለ፡፡

ጣልያን በማእከላዊው ሜድተሪያንያን የምታደርገውን የማዳን ዘመቻ በመተውዋን የሊብያን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ጥበቃ በማጠናከራቸው ከሞሮኮ እስከ ስፔይን ያለው መንገድ ከሕገ ወጥ ስደተኞች ዋናው ወደ አውሮጳ የመግብያ ቦታ ሆናል፡፡

2018 በሜድትሪያንያን በኩል ወደ አውሮጳ  ከገቡት 112,000 ስደተኞች መካካል  ግማሾቹ የሞሮኮ ስፔይን መንገድ  መተላለፍያ በመጠቀም ነው፡፡  ይህ የስደተኞች ማዕበል ማድሪድና ሞሮኮ  ሕገ ወጥ ስደት ለመግታትና የሕገ ወጥ የሰው ልጅ  አዘዋዋሪዎች ቡዱን ለማፋራረስ በጋራ በመሆን የተቀናጀ እርምጃ  እንዲወስዱ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም ሞሮኮ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸውና በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮጳ ለመግባት የሚፈልጉ አፍሪቃውያን  ስደተኞች ወደ አገሪቱ ደቡባዊ ክፍል እንዲሄዱ አድርጋለች፡፡

TMP – 09/05/2019

ፎቶ፡ Shutterstock /  Riccardo Nastasi

Photo caption: Abandoned migrant boat