ብዙ ህፃናት ስደተኞች ወደ ግሪክ ደሴቶች በመጥፎ ሁኔታ እየደረሱ ነው
የተባበሩት መንግስታት የህፃናት ጉዳይ የሚከታተል (ዩኒሴፍ) ባለፉት መጀመሪያ 8 ወራት 2018 (እ.ኤ.አ) ከ7 ሺህ በላይ የህፃናት ስደተኞች እንደደረሱና ባለፈው ዓመት 2017 ሲነፃፀር በ32% እድገት (ጭማሪ) እንዳሳየ ገልፀዋል፡፡ አስቸጋሪውን ጉዞ ጨርሰው እዛው ከደረሱ በኋላ አብዛኛዎቹ ህፃናት ንፅህናው ያላጠበቀና በደሴቶቹ ህዝብ የበዛበትና መገልገያ ቦታዎቹ ያልተመቹ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በግሪክ የዩኒሴፍ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ግብረ መልሱ መስጫ ጣብያ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት ሃላፊ ሉችዮ ሜሪላንድ እንደገለፀው “ጨበማእከሎቹ ህፃናትን ማስተናገድ እጅግ አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱና በጣም አስቸጋሪና በአደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ፣ ይህም አዳዲስ ስደተኞቹ ስለሚጨምሩ መሆኑን አስታውቋል፡፡
“ሁሉም ስደተኞችና በስደተኛ መቀበያና መለያ ማእከላት የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂዎች በተለይም ህፃናት ወደ ዋናው ቦታ ያለ ምንም መዘገየት መተላለፍ እንዳለባቸውና በዚህም ድህንነቱ የተጠበቀ መኖርያ ፣ ከለላ ፣ የህክምና አገልግሎትና ሌሎቹም መሰረታዊ አገልግሎት እንዲያገኙ“ ተብሎ መሆኑ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በግሪክ ደሴቶች ከሚገኘው 20500 ስደተኞች 80 ከመቶ የሚሆኑ 5000 (አምስት ሺ) ህፃናትን ጨምሮ ንፅህናው ባልተጠበቀ፣ ከአቅም በላይ የተሸከመና የመቀበያና መለያ ጣብያ መሆኑ ታውቋል፡፡ ከ70 የሚበልጡ ሰዎች በአንድ መፀዳጃ ይጠቀማሉ ፣ ይህም ከመፀዳጃው የሚወጣውን ፍሳሽ እንደሚያስቸግራቸው ነው የአከባቢው ባለስልጣናት ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ የህዝብ ብዛት ካልተቀረፈ ካምፖቹን ለመዝጋት መዛታቸው ታውቋል
በሌሰቦስ የሚገኘው በሞርያ የተባለው ካምፕ (ማእከል) 3100 ሰዎችን ይይዛል ተብሎ የተሰራ ሲሆን የስደተኞች መቀበያ ተብሎ የተሰራው ሳምሶ ደግሞ ለ650 ሰዎች ተብሎ የተሰራው በአሁኑ ሰዓት 13000 ሰዎች ገደማ እያስተናገደ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ 2400 ህፃናት ናቸው፡፡ የግሪክ መንግስት 2000 ስደተኞች ከሞርያ ደሴት ወደ ዋናው መሬት (ቦታ) ለማንቀሳቀስ (ለማዛወር) ተስማምቷል፡፡
ዩኒሴፍ (የህፃናት አድን ድርጅት) ህፃናት በደሴቶቹ የጤና ፣ የድህንነት ስጋትና ፣ የስነኣእምሮ ጫና እንደሚደርሳቸው ገልፀዋል፡፡ ሜሪላንድ እንደሚገለፀው ከሆነ አብዛኛዎቹ ያገኛሁአቸው ህፃናትና ወጣቶች የጦርነት ሰቆቃ አንዲሁም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀለው የተሰደዱ ናቸው፡፡ አሁን በጣም አስቸጋሪና ብሩህ ተስፋ የሌላቸው ናቸው፡፡ ኣብዛኛዎቹ ለከፍተኛ የአእምሮ ጭንቀት ተዳርጓል፡፡
የእርዳታ ኤጀንሲዎች አለም አቀፍ የነፍስ አድን ኮሚቴ እና ድንበር የለቫ ሃኪሞች (MSF) በቅርቡ በሞርያ ካምፕ ያሉት ወጣቶች ራስን የመግደል ሙከራ ወይም ራሳቸውን እንደጎዱ ማሰጠንቀቅያ ሰጥተዋል፡፡ የአለም አቀፍ የነፍስ አድን የቅርብ ጊዜ ዘገባ እንደሚያሳየው ከሆነ 60% (በመቶ) የሚሆኑት የሞርያ ካምፕ ስደተኞች ራሳቸው ለመግደል አቅደው እንደነበር ይገለፃል፡፡
በግሪክ መንግስት ህግ መሰረት ስደተኞች በማእከላት የሚኖሩ ተገን ጠያቂዎች ቢያንስ 25 ቀናት በማቆያ ማእከላት ማሰለፍ አለባቸው ፣ ይህም የመደረሻ ሂደት ለማሟላት ሲሆን ነገር ግን ህፃናት እስከ አንድ ዓመትና ከዛ በላይ እንደሚቆዩ ታውቋል
ግሪክ በአሁን ጊዜ እሰከ 60000 ስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች የምታስተናግድ ሲሆን በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽንና በህፃናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) የወጡ ዘገባ እንደሚያመለክተው 23500 ህፃናት ስደተኞችን 3448 ጠባቂ የሌላቸው ህፃናትን ጨምሮ በሃገሪቱ እንደሚኖሩ ታውቋል፡
TMP – 15/10/2018
ፎቶ ፡ Anjo Kan/Shutterstock
ፅሑፉን ያካፍሉ