በሊብያ እስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች በሳንባ ነቀርሳ በሽታ መያዛቸውን ተረጋገጠ

በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በሜድትራንያን በኩል ወደ አውሮፓ ለመጓዝ በሚያደርጉት ሙከራ ተይዘው ንጽህና በሌላቸው በታጨቁና የሳንባ ነቀርሳ በሽታ በተስፋፋባቸው የሊብያ እስር ቤቶች እንዲኖሩ ይደረጋሉ፡፡.

በአሁኑ ግዚ በሊብያ እስር ቤቶች ውስጥ ተይዘው ከሚገኙት በሺዎች ከሚቆጠሩት እስረኞች መካካል ሳም የተባለ የሳላሳ/30/ አመት ዕድሜ ያለው ኤርትራዊ ስደተኛ አንዱ ሲሆ፤ እነርሱ ያሉበትን ሁኔታ ኢሰብኣዊና በጣም አሰቀያሚ ለኑሮ የማይስማማ መሆኑን በበጎ አድራጊ ቡዱኖች ተገፀዋል፡፡   ሳም ያለበት ክፍል ከ100 በላይ ስደተኞች ይኖሩበታል፡፡  ከነዚህ መካካል በቅርቡ ወደ እስር ቤት የገቡና በሳንባ ነቀርሳ በሽታ የተያዙ ናቸው፡፡  ሳም በመጀመርያ ከበሽታ ነጻ መሆኑን  በሓኪሞች የተረጋገጠለትና በበሽታው ለተያዙት ሰዎች እርዳታ በማድረግ ላይ ነበር፡፡  ይሁን እንጂ ከጥቂት ወራት በሃላ የድካም ስሜት ይሰማው ጀመር ፡፡ ‹‹ ከጥቂት ወራት በሃላ ጤነኛ አልነበርኩም፡፡ ምርመራ ሳደርግ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ እንዳአለብኝ ሃኪሞች ነገሩኝ››  በማለት ተናግረዋል፡፡

በነዚህ እስር ቤቶች ውሰጥ የሚገኙት ሁሉም ስደተኞች በሳንባ ነቀርሳ በሽታ ከተጠቁት በሽተኞች ጋር አብረው እንዲኖሩና በጋራ ባልዲዎች ወይም የፕላስቲክ ጠርሙሶች ላይ እንዲጸዳዱ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም በቂ ምግብና መድሃኒት አይሰጣቸውም፡፡ አብዛኞዎቹ እስረኞች  በጣም ደካሞችና በቂ ምግብ የማያገኙ በምግብ እጥረት ህመም የሚሰቃዩ በመሆናቸው በሚሰጣቸው መድሃኒት ምክንያት የሚመጣውን የጎንሽ ጉዳት ለመቋቋም አልቻሉም፡፡

ዶክተር ፕሪንስ አልፋኒ በሊብያ የመዲስን ፎንትቲየር የድንበር የለሽ ሓኪሞች አስተባባሪ ሲሆኑ ‹‹  እሰረኞች የሚበላ ነገር  ወይ ምግብ ባለማግኘታቸው ምክንያት መድሃኒት ማቋረጣቸውን የሚገልጽ ዘገባ ደርሶናል፡፡  እኛም ለተራበ እስረኛ አንቲባየቲክ መስጠቱን ተገቢ አለመሆኑን እንገነዘባለን›› በማለት ተናግረዋል፡፡

ሌላው ኤርትራዊ ስደተኛ  በሊብያ እስር ቤት ውስጥ ለአንድ አመት ያህል የቆየ ሲሆን ‹‹  በሳንባ ነቀርሳ በሽታ የተጠቁ ብዙ ሰዎች ያሉ ሲሆን ሆኖም ግን ሓኪም የለም እያሉ በህይወታችን ላይ እየቀለዱ ናቸው። በየጥዋቱ ለግማሽ ሰዓት ያህል ብቻ ውሃ እናገኛለን፡፡ 650 የምንሆን እስረኞች በ8 መጻዳጃ ቤቶች ብቻ እንጠቀማለን››  በማለት አክሎ ተናግረዋል፡፡  በሊብያ በሌላኛው እስር ቤት  ውስጥ የሚገኝ ስደተኛ ከመስከረም እኩሌታ ጀምሮ ከጽዳት ጉድለትና በቂ ሕክምና ካለማግኘት የተነሳ ቢያንስ 10 እስረኞች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡

ብዙ እስረኞች በእስር ቤቶቹ ያለውን አስከፊ ሁኔታ ተቃውሞታል፡፡ በዚህም ሳብያ በሊብያ የእስር ቤት ዘበኞች ከፍተኛ ግፍ ደርስባቸዋል፡፡ በዚህ ዓመት በመጋቢት ወር መጀመርያ ላይ 150 የሚሆኑ ወንዶች በእስር ቤት ያለውን የእሰረኞች አያያዝ በመቃወም በትሪፖሊ ከተማ የሚገኘውን ትሪክ አል ሲካ ከተባለ እስር ቤት ማምለጥ ችለዋል፡፡ 30 የሚሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ከእስር ቤት በማምልጣቸውና ተቃውሞ በማድርጋቸው ምክንያት ስቃይ ደርስባቸዋል፡፡

በ2018 እ.ኢ.አ ከ15,000 በላይ ስደተኞች ሜዲትራንያን ባህርን ለማቋረጥ ሲሞክሩ መሃል ላይ በመያዝ ወይም  ከአደጋ በማዳን ወደ ሊብያ እንዲመለሱ  መደረጋቸውን የሊብያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች አስታውቀዋል፡፡

በሊብያ ከሚገኙ ከ600,000 በላይ ስደተኞች አብዛኛዎቹ አስከፊ መከራና ስቃይ እንደሚደርስባቸው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት /IOM /  አስገንዘባል፡፡ በአሁኑ  ጊዜ 20,000 የሚሆኑት ጥገኝነት ጠቂዎችና ስደተኞች በሊብያ እስር ቤቶች ውሰጥ ተይዘው ይገኛሉ፡፡

TMP 05/04/19

ፎቶ፥ ANSA/ ዙሀይር አቡስረዊል

Photo Caption:  በትሪፖሊ አቅራቢያ ዛውያ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች