የአውሮፓ ህብረት ጥገኝነት የሚሰጣቸው ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው
በ2018 እ.ኤ.አ በአውሮፓ ሀብረት አገሮች ጥገኝነት የተሰጣቸው ሰዎች ቁጥር በ40% መቀነሱን/መውረዱን በቅርቡ የወጣው የዩሮስታት የአውሮፓ ህብረት የስታስቲክስ ኤጀንሲ ዘግቧል።
በዚህ ዘገባ መሰረት በ2018 እ.ኤ.አ 330 ሺ ጥገኝነት ጠያቂዎች ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን በ2017 እ.ኤ.አ ከተመዘገበው 533 ሺ ግማሹን ያህል ይሆናል። ከአውሮፓ ህብረት አገሮች ጀርመን ፣ ጣልያንና ፈረንሳይ በብዛት ጥገኝነት የሰጡ አገሮች ናቸው።
በአውሮፓ ህብረት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ብቻቸውን ሆነው ጥገኝነት የሚጠይቁ ልጆች ቁጥር በ2018 እ.ኤ.አ ከአንድ ሶስተኛ በላይ መቀነሱን /መውረዱን ዘገባው አስታውቋል።
በአውሮፓ ህብረት በ2018 እ.ኤ.አ አለም አቀፋዊ ጥበቃ እንዲያገኙ ከተደረጉ አብዛኛዎቹ ሰዎች መካከል ሶሪያውያን ፣ አፍጋኒስታውያንና ኢራቃውያን ሲሆኑ ይህም ቁጥራቸው
ከመጀመሪያዎቹ አመልካቾች ከ50% በላይ ይይዛል። በተመሳሳይ ዓመት 4% ብቻ ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ተቀባይነት አግኝተዋል። በቅርብ ዓመታት አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ህብረት አገሮች ጥብቅ የሆኑ የስደት ፖሊሲዎች በተግባር ላይ እንዲውሉ አድርገዋል። ለምሳሌ ጀርመን “መልህቅ የስደተኞች ማእከል” (Anker Migrant centres) የሚል በማቋቋም የጥገኝነት ጠያቂዎች ጉዳይ በመያዝና በሂደት በማየት በዚሁም በአውሮፓ ህብረትና ቱርክ መካከል በተደረገው ስምምነት መሰረት ሰደተኞቹ ወደ ግሪክ እንዲመለሱ ያደርጋል። የዚህም ውጤት ጥገኝነት የተሰጣቸው ሰዎች ቁጥር በብዙ እንዲቀንስ አድርጓል። በ2018 እ.ኤ.አ በአውሮፓ ህብረት ከ580 ሺ አለም አቀፍ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ካመለከቱት ጥገኝነት ጠያቂዎች መካከል ከ250 ሺ በላይ ተቀባይነት አላገኘም።
ጀርመን ብዛት ያላቸውና በመጠባበቅ ላይ የሚገኙትን የጥገኝነት ማመልከቻዎች ወሳኔ ለመሰጠትና የጥገኝነት ሂደት ጊዜ ከአንድ ዓመት ወደ ስድስት ወር ለመቀነስና በአጭር ጊዜ ተቀባይነት ያላገኙትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ነበሩበት ለመመለስ ውሳኔ አድርጋለች። ባለፉት ጥቂት ዓመታት አብዛኛዎቹ የአውሮፓ ህብረት አገሮች ሃንጋሪ ፣ ኦትስሪያና ፖላንድን ጨምሮ ለጥገኝነት ጠያቂዎች ይሰጡት የነበረውን መሰረታዊ ማህበራዊ ድጋፍና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንዲቋረጥ አድርገዋል።
በአውሮፓ ሀብረት አገሮች ያሉት ብዙ ጥገኝነት ጠያቂዎች ባለው ጥብቅ ህግና ቁጥጥር አንዳንዴም በሚታየው ሰደተኞችን የፀረ ስደተኛ ስሜት ምክንያት ለመኖር እየታገሉ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት ብዙ ጥገኝነት ጠያቂዎች ሌላ አማራጭ ስለ ሌላቸው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ።
TMP – 29/04/2019
ፎቶ ፦ ሹተር ስቶክ ኮም
በአውሮፓ ህብረት ጥገኝነት ያገኙ ሰዎች ቁጥር በብዛት ቀንሷል።
ፅሑፉን ያካፍሉ