ቱንዝያ ከሁለት ሳምንታት ቆይታ በኋላ የስደተኞችን መርከብ በወደብዋ እንድያርፍ ፈቃድ ሰጠች!
በጁላይ 28 የወጣው ዘገባ እንደምያመላክተው 40 ስደተኞችን ይዞ ባህር ላይ ለ2 ሰማንታት የቆየው እና በኮመርሻል ቨስል የዳነው መርከብ በወደብዋ እንድያርፍ ቱንዝያ ፈቅዳለች።
ቱንዝያ እንዚህ ስደተኞች የተቀበለችበት ምክንያት “ለሰብአዊ ስራ ሲባል ነው” ብለዋል የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዮሴፍ ችሃድ።
የማልተስ፣ ፈረንሳይ እና Italian እንዲሁም የቱንዝያ ባለ ስልጣናት መርከብዋን ፊት በመንሰታቸው ለሁለት ሳምንታት የምያክል ጊዜ ታንከር ሳሮስት 5 የተባለውን የዛርዚስ የቱኒዝያ ደቡባዊ ክፍል የሆነውን ወደብ አቅራብያ ከባህር ላይ እንድትቆይ ተገዳለች። ይሁን እንጅ እነዚህ 40 ስደተኞች ከሞት የዳኑት በጁላይ 15 ከሌላ “ካርሎኒ ቲድ III” የተባለ መርከብ በደረሰ የስልክ የድረሱልን ጥሪ መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።
እንደ አሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ከሆነ የቱኒዝያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቻሃድ ሀገራቸው እነዚህ ስደተኞች መቀበል መቻልዋ በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሌላ እንዳይተረጎምባት አስጠነቅቃለች፤ ማለትም እነዚህ ስደተኞች ስትቀበል በሀገርዋ የስደተኞች የስክሪን ስርዐት ለማቋቋም ፈቃደኛ ነች ማለት አለመሆኑ ገልፀዋል።
የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ስደተኞች የአውሮፓ ምድር ሳይረግጡ ባሉበት እንዲመለሱ እና አደገኛው የባህር ላይ ጉዞ ለመቀነስ በማሰብ በሰሜናዊ የአፍሪካ ክፍል የስክሪን ማእከላት ለመክፈት ( screening centres in North Africa ) አልመው እየተንቀሳቀሱ መሆናቸው ይታወቃል።
“የመጀመርያው ስራችን የነበረው በማልታ ባህር ላይ ሲሆን የዛኔ የነበረ ጭቅጭቅ ስደተኞቹ ወደየትኛው ሀገር እንውሰዳቸው የሚል ነበር።” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ቱኒዝያ ስደተኞቹን ለመቀበል መወሰንዋ ባስታወቀችበት ጊዜ “ውሳኔውን ለመዉሰድ መዘግየታችን እንዳለ ሆኖ እንደዚህ አይነት ቁርጠኝነት በመውሰዳች ግን ደስተኞች ነን።” ብለዋል የሳርሶት 5 ካፕቴኑ ዓሊ ሓጂ ለኤኤፍፒ በሰጠው ቃለ መጠይቅ።
ስደተኞቹ 246 ስደተኞች ወደ ተቀመጡበት በሀገሪትዋ ታላቁ ከተማ መደኒን ወደ ሚገኘው የስደተኞች ማቆያ ማእከል ይወሰዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የቱኒዝያ ቀይ ማህበር እንዳለው እነዚህ 40 ስደተኞች ከግብፅ፣ ባንግላድሽ፣ ካሜሮን፣ ሰኔጋል፣ ጋና፣ ኮትዴቫር እና ሴራልዮን የመጡ መሆናቸው ገልፀዋል።
TMP – 03/09/2018
ፎቶ ክሬዲት: አይኦኤም
ፅሑፉን ያካፍሉ