ከስደት ተመላሾች ወደ ስራ የማስተሳሰር ስራ፡ በሱዳን
አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦ ኤም) እና የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ እንደገለፁት ከጁን 2017 እስከ ማርች 2018 ባሉት ግዝያት ውስጥ 615 ሱዳናውያን ስደተኞች በገዛ ፈቃዳቸው ከሊብያ ተመልሰዋል።
ስደተኞቹ IOM’s voluntary humanitarian return assistance programme, ከሊብያ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኋላ መጀመርያ የስነ ልቦና ትምህርት እና ድጋፍ እንድያገኙ ተደርገዋል። ስደተኞቹ መጪው ህይወታቸው በሀገራቸው ሰርተው የሚኖሩበት እቅድ እንድያወጡ የምያስችል ድጋፍም ተሰጥተዋቸዋል።
ወደ ሊብያ የሚሄዱ ስደተኞች ብዙ ጊዜ እስርን፣ ከፍተኛ የመብት ጥሰትን፣ ስቃይን (ቶርቸር) እንዲሁም የባርያ ንግድን ጨምሮ ከፍተኛ የሆኑ አስጊ የህይወት ፈተናዎች ይደርስባቸዋል።
ሊብያ ላይ ከሚያጋጥሙ የስደተኞች መከራ አንዱ በማርች ወር ላይ ሶሻል ሚድያ ወጥቶ የታየ አንድ ቪድዮ ነበር። ቪድዮው አንድ ሱዳናዊ ሰውነቱ ሲቃጠል የምያሳይ ነው። ይህ አስደንጋጭ ቪድዮ ወደ ሶሻል ሚድያ ያስገቡት ወንበዴዎቹ ከስደተኞች እና ቤተሰቦቻቸው በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ለማግኘት በመፈለግ ነው። የሱዳን መንግስት በግዜው ይህ አስነዋሪ ተግባር በማውገዝ የሊብያ መንግስት ዜጎቹን እንዲከላከልለት መልእክት አስተላልፎ እንደነበር ይታወሳል።
ሱዳናውያን ስደተኞች ልክ የኤርትራ፣ ሶማልያ እና ኢትዮጵያ ስደተኞች እንደምያደርጉት ሜዲትራንያን ባህር አቋርጦ የአውሮፓን መሬት ለመድረስ በተስፋ ይሰደዳሉ። የሱዳን የውጭ ጉዳዮች ዋና ፀሀፊ አምባሳደር ዶክተር ካራር ኣል ቱሃሚ “እየጨመረ ያለ የስደት መጠን እና የምያስከትለው ያለ የዐለማችን ትልቁ ችግር የሚፈታው በጋራ በመስራት እና በማሳተፍ ብቻ ነው” ብለዋል።
“እኛ ስደተኞችን በሀገር ቤት መልሶ ለማቋቋም በሚደረግ ጥረት በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነቱ አለን። ማሕበረሰቡ በማሳተፍ ጭምር ለመስራት ዝግጁ ነን። ይህ ተግባር ከስደት የሚመለሱ ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ ስራ ለማስተሳሰር ያግዛል የሚል ተስፋ አለን። በተለይ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ለወደፊቱም ወደ ስደት መሄድ ለመምረጥም ላለመምረጥትም ትክክለኛ ምርጫ ይሰጣል።” ብለዋል አምባሳደሩ።
የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አባላት እነዚህ ከስደት ተመላሽ ሱዳናውያን ዜጎች በሀገር ቤት ሰርተው የሚለወጡበት ዕድል ለማመቻቸት ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን አበርትተው እንደሚሰሩ ይገልፃሉ። ይህ ፕሮግራም የማሕበረሰብ ልማት ከማረጋገጡ በተጨማሪ አንዳንድ ለስደት የምያነሳሱ ምክንያቶች በመዝጋትም ተጨማሪ ፋይዳ ይኖረዋል።
የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ከሚሰጣቸው አስፈላጊ አገልግሎቶች አንዱ የስነ ልቦና ማማከር አገልግሎት ነው። ይህ የማማከር ስራ ከስደት ተመላሾቹ የስነ ልቦና ብርታት እና ተስፋ እንዲታጠቁ የምያደርግ ነው። ከዛም በተጨማሪ ስራ ለመጀመር የምያስችል የስራ እቅድ በማውጣት ዙርያ የምክር አገልግሎት ይሰጣል።
እስከ አፕሪል 17/2018 ባለ ጊዜ ውስጥ 109 ስደተኞ በቅርብ ጊዜ ደግሞ በአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አመካኝነት የሚሰጥ የክህሎት እና ቢዝነስ ለመጀመር የምያስችል መሰረታዊ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል።
በሱዳን የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የካልቹራል ኦሬንቴሽን ኤንድ ሳይኮሎጂካል ሳፖርት አስተባባሪ የሆኑት ራዋን ሃሚድ “ከስደት ተመላሾች አብሬ ስሰራ ያየሁት አንድ ነገር ቢኖር እነዚህ ስደተኞች በስደት መንገዳቸው ላይ ያጋጠማቸው ፈተና ከፍተኛ የሆነ የአእምሮ ችግር አስከትሎባቸዋል።” ብለዋል።
“ወደ መከራ መጋለጣቸው፣ አካላዊ ጥቃት ሊደርስባቸው መቻሉ እንዲሁም ታስረው ተገርፈው ወደ ቤት ባዶ እጃቸው እና የተበተነ ተስፋ ይዘው መመለስ መቻላቸው ስነ ልቦናዊ ድጋፍ የምያስፈልጋቸው መሆኑ ገብቶናል።” ሲልም አክሎ ገልፀዋል፤ ሃሚድ።
በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የሱዳን የትስስር ማእከል ሃላፊ የሆኑት ሊንዳ ኦናይስ በበኩላቸው “ከስደት ተመላሽ ሱዳናውያን ባግዝን ቁጥር በሀገሪቱ ጠንካራ የመደጋገፍ ባህል እንዲጎለብት እና ከማህበረሰቡ የማስተሳሰር ስራ ቀልጣፋ እንዲሆን እያገዘ ነው።”
TMP – 26/07/2018
ፎቶ: በአይኦኤም. ሱዳናውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ
ፅሑፉን ያካፍሉ