ጣልያን ለህገ-ወጥ ስደት ዋና መንስኤዎችን ለመግታት እንድታግዝ ኬንያ ጥሪ አቀረበች

ህገወጥ ስደትን ለመግታት በሚደረገው ጥረት የጣልያን መንግስት ለህገወጥ ስደት ዋና ዋና መንስኤዎች የሆኑትን ልዩ ትኩረት እንዲያደርግ ኬንያ ሓሳብ አቅረባለች:: ጥቅምት 25/2018 / .. በተካሄደው የጣልያን አፍሪቃ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ተገኝተው የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃላፊ አባቡ ንዋምባ እንደተናገሩትየጣልያን መንግስት የአፍሪቃ ሃገሮች ጋር በመሆን ለህገወጥ ስደት መንስኤ የሆኑትንና በሜዲትራንያን ባህር ለአደገኛ ጉዞ የሚገፋፉትን ምክንያቶች እንዲቀርፉ ገልፀዋል::”

ሓላፊው46 የአፍሪቃ ሃገሮች   13 ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የአፍሪቃ ሕብረት ጨምሮ ለተወጣጡ 350 የሚደርሱ ተወካዮች ባደረጉት ንግግር ከአፍሪቃ ሃገሮች ብዙ ምርቶች ወደ ጣልያን በማስገባትና በአህጉሪቱ ለሚካሄዱት የሰላም ሂደቶች በመደገፍ የጣልያን መንግስት ከአፍሪቃ ህገወጥ ስደተኞችን እንዲበዙ የሚገፋፉትን ለማቃለል ማገዝ እንደሚችል ሓሳብ አቅርበዋል::”

በአህጉሪቱ ያለውን የኢኮኖሚ ዕድገት እድልና በአፍሪቃውያን ወጣቶች ብዛት እውቅና በመስጠት ዋና ፀሓፊው የአውሮፓና የአፍሪቃ ትብብር እንደሚያስፈልግና ይህም በጋራ ትብብር የሚደረገው ሓላፊነትን በመወጣት የዓለምን መረጋጋትና ብልፅግና ማምጣት ይቻላልሲሉም ሞግተዋል::  

ከስፔይንና ግሪክ ጋር ጣልያን ወደ አውሮፓ የሚሄዱትን የአፍሪቃ ስደተኞችን በመቀበል ከቀዳሚዎቹ ተርታ ትሰለፋለች:: 2018 / ብቻ 22 በላይ ስደተኞች ወደ ጣልያን የባህር ዳርቻዎች እንደ ደረሱ ይታወቃል:: ይህንን የስደተኞች መጉረፍ ተከትሎ የጣልያን መንግስት የድንበር ጥበቃና ቁጥጥር ፖሊሲዎች ማውጣቱና ይህም ለነፍስ አድን ስራዎች ሲባል ወደቦችን መዝጋት ሊብያ የድንበር ጠባቂዎች አቅም መገንባትና ህገወጥ ስደተኞችን ማስቆም የመሳሰሉትን ያጠቃልላል::

የጣልያን የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የዓለም አቀፍ ትብብር ሓላፊ ኢንዞ ሞኦቬሮ ሚላኔሲ ጉባኤው  ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር መልክ ያለው የምክክር እድል እንደሚከፍት ተናግረዋል:: ጨምረውም ሲናገሩእኛ ይህንን ጉዳይ የተገኘውን ጥሩ አጋጣሚ የባህላዊና እድሜ ጠገብ ዝምድናችንና የጂኦፖለቲካዊ ትብብራችን በመጠቀም ችግሩን ለመቅረፍ ፅኑ እምነት አለንብለዋል::

ከምኣቬሮ ሚላኔሲ ቁርጠኝነት በተጨማሪ በሃቀኛና ፍሬያማ የሆነ ውይይት መሰረት በማድረግ በአፍሪቃ አገሮችና በጣልያን መካከል የአንድ ቢልዮን ዩሮ የአንድነት ፈንድ ለማቋቋም እንዳዘጋጆችና ይህም እርሻ የዓሳ ምርት ማሳደግና የንግድ በሰሜን አፍሪቃ እንዳጎለብት ነው:: በተጨማሪም ሃገሪቱ ተጨማሪም መዋእለ ንዋይ ለአፍሪቃ ፈንድ እንደመደበችና ይህም

ህገወጥ ስደትን ለማስቆምና የኢኮኖሚ ኢንቨስትመንት ከፍተኛ የህገወጥ ስደት የሚታይባቸው ሀገሮች ውስጥ መሆኑ ነው::

TMP – 23/11/2018

ፎቶ: ጀን ዋትሶን/ ሻተርስቶክ። ሴቶች የሻይ ቅጠል ሲለቅሙ በምዕራባዊ ኬንያ የሻይ ቅጠል በኬንያ ከፍተታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ምርት ነው::