የጣልያን ባለስልጣናት የ1500 የስደተኞች ካምፕ አፈረሰ
በደቡባዊ የጣልያን ክፍል ከ1,500 በላይ ስደተኞች መኖርያ አልባ ሆነው ቆይተዋል። በመሆኑም እነዚህ ስደተኞች የመሰብሰብ ስራ የተሰራ ሲሆን በሳን ፈርዲናንዶ ተሰርቶ ነበረውን ቀኝ ዘመም ፓርቲ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ታላቁ የስደተኞች ካምፕ በማፍረስ መጀመሩን ተገልፀዋል።
ወደ 1,000 የሚጠጉ የፖሊስ ኦፊሰሮች ቦታው በመክበብ የምያፈርሱ ማሽኖች አስገብተው ወደ 400 የሚጠጉ ሼዶች አፈራርሰዋል።
“ቃል በተገባው መሰረት … ከወሬ ወደ ተግባር ተሸጋግረናል።” ብለዋል የጣልያኑ የሀገር ውስጥ ሚኒስትርና የቀኝ ዘመሙ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ማቲው ሳልቪኒ።
የሳን ፈርዲናንዶ ከንቲባ የሆኑት አንድራ ትሪፖዲ በበኩላቸው ቀድመው ካምፑ የእሳት አደጋ ሊያስከትል በምችል ሁኔታ እንደ ነበር ገልፀዋል። መንግስት እነዚህ ስደተኞች ወደ ስደተኛ ማእከላት እንደሚወሰዱ ገልፀዋል።
ይሁንና ይህ የማፈራረስ እና ስደተኞቹን የመውሰድ ስራ ራሳቸው ስደተኞቹ ተቃውመውታል። ምክንያቱም በአከባቢው ሳይፈቀድላቸው በብርቱኳን እና የዘይት ልማት ውስጥ ተሰማርተው ስለነበር ነው። ለጣልያን መገናኛ ብዙኋን ሀሳባቸው የሰጡ አስያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ስደተኞቹ ስራ ላለመፍታት ወደ ልማቱ ቦታ የተጠጋ ሌላ መኖርያ ይፈልጋሉ።
ዘጋርድያን ያወጣው ዘገባ እንደምያሳየው እነዚህ በህገ ወጥ መንገድ ስራ ላይ የተሳመሩ ስደተኞች ከሚገባቸው በታች ይከፈላቸዋል። በሰዓት እስከ ሁለት ዩሮ እንደሚከፈላቸው ተነግሬል። በሰዓት እስከ ሁለት ዩሮ እንደሚከፈላቸው ሲሆን ሶስት አራተኛ የሚሆኑ ደግሞ የስራ ውል ሳይኖራቸው ነው የሚሰሩት። ሰብል በሚሰበሰብበት ጊዜ እሰከ 3000 የሚደርሱ ያልተዘገቡ ስደተኞች ስራ ፍለጋ በአከባቢው ካምፕ ሰርተው ያለ ኤሌክትሪክሲቲና የውሃ አቅርቦት ይኖራሉ።
ይህ ካምፕ ከአሁን በፊት ፈራርሶ የነበረ ሲሆን ስደተኞቹ እና አሳይለም ጠያቂዎቹ ወደ ቦታው ተመልሰዋል። በመሆኑም የአከባቢው ባለስልጣናት ስደተኞቹ ካምፕ እንዳይሰሩ “አስፈላጊውን እርምጃ” እንደሚወስዱ ተናግረዋል።
TMP – 27/03/2019
ፎቶ: አንተንዮ አሪኮ/ሻተርስቶክ. የጣልያን መከላከያ ሀይል የስደተኞቹ ካምፕ ካፈረሰው በኋላ የቀረ ፍርሽራሽ፤ በሳን ፈርዲናንዶ ከተማ
ፅሑፉን ያካፍሉ