ፖሊስ በየሳምንቱ 20 የማስወጣት ስራ ስለሚሰራ በካሌ ሁኔታዎች እየተባባሱ ሄደዋል
ሄልቢ የተባለው ኤርትራዊ ስደተኛ እንደሚገልፀው እሱና ጓደኞቹ በረንዳ ላይ እንደሆነ ገልፆ፤ ይህም ፖሊሶች ቴንዳዎቻቸውን ሰራዎቻቸው ስለሚወስድባቸው መሆኑ ይናገራል:: የፈረንሳይ ፖሊሶች አስመልክቶ ሲናገር ፖሊሶችን ሰናይ እንሮጣለን ምክንያቱም ከዚህ በፊት ደብድበውናል ይላል::
ከኤርትራውያን ጎደኞቹ አንዱ ኢፌ የተባለው የ27 ዓመት ወጣት ሲናገር ወደ እንግሊዝ አገር ለመሻገር በመሞከር ከአንድ ዓመት በላይ መቆየቱ ይገልፃል:: እሱ እንደሚለው አብዛኛዎቹ ቀናት (ለሊቶች) ፖሊሶች ስለሚያሳድዱን መተኛት አደገኛ ነው ሲል ምሬቱን ይገልፃል::
ፓውል ሌስለር የተባለ በስደተኞች ላይ የሚሰራ ዘጋርድያን ጋዜጣ እንደገለፀው ካሌ የስደተኞች መጠልያ ያለው ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰ መምጣቱ ይህም ጀንግል የተባለውን ዋናው የስደተኞች መጠልያ በ2016 ከፈራረሰ ወዲህ መሆኑ ገልፀዋል:: አብዛኞቹ ስደተኞች ለ4 ሰዓታትም አይተኙም፤ ይህም የስነ–ልቦና ጫና እንደሚያስከትልም ጭምር ይገልፃል::
የክረምቱ ጊዜም የራሱ የሆነ ተፅእኖ ይፈጥራል:: የብድር በሽታዎች እየተከሰቱ ናቸው ፤ የእንግሊዝ አገር የእርዳታ ድረጅት ተወካይ የሆነችው ማዲ አለን እንደምትገልፀው እሰካሁን ሶስት የሳምባ ነቀርሳ ታማሚዎች እንደተገኙ ትናገራለች:: በቅርቡ በየሳምንቱ ካሌ ውስጥ በሚደረገው ያማስወጣትና የማባረር ስራ ትልቅ የስነ–ልቦና ጫና በስደተኞች ላይ እየፈጠረ መሆኑ ትገልፃለች::
አለን ጨምራ ስታስረዳም ሰዎች ሁሌም በእንቅስቃሴና መፈናቀል ላይ ናቸው ፣ አንድ ድንኳን (ቴንዳ) ለ6 ወራት ነበር የሚያገለግለው አሁን ግን ለ6 ቀናት ብቻ ነው የሚያገለግለው:: ሁኔታዎች በማይታመን ሁኔታ ከነበሩበት እጅግ በጣም የከፉ መሆናቸውም ትገልፃለች::
የፈረንሳይ ፖሊሶች በስደተኞች ላይ የሚያደርሱትን በደል በማጋለጥ ዘገባው እስካሁን በ12 ወራት ውስጥ ከ1000 በላይ ክሶች በፖሊሶች ላይ እንደተደረጉና ከነዚህም 244 ድብደባዎችና ግርፋቶች እንደሁም አስለቃሽ ጋዝ መጠቀማቸውም ይገለፃል::
በካሌ ያለው ሁኔታ ስደተኞችን በጀልባ ወደ ኢንግሊዝ አገር እንዲሻገሩ እየገፋፋቸው መሆኑና ዘ ቴሌግራፍ በቅርቡ እንደዘገበው 28 ጀልባዎች ወደ ኢንግሊዝ ሲሻገሩ በፈረንሳይ ባለስልጣናት መያዛቸው ገልፀዋል::
TMP – 7/12/2018
ፎቶ:- ኤድዋርድ ክሮፎርድ/ ሻተርስቶክ። የፈረንሳይ ፖሊሶች ከካሌ የስደተኞች ማእከል ሲወጡ
ፅሑፉን ያካፍሉ