የሱዳን ፖሊሶች በህገ-ወጥ ሰደተኞች ላይ የማሰር ሰራ ቀጥለውበታል

የሱዳን የፀጥታ ሃይል ሰራተኞች ሊቢያን ለማቋረጥ በተዘጋጁት አራት ህገወጥ አዘዋዋሪዎችና 57 ህገወጥ ስደተኞችን ጉዞ አሰናክለዋል። ይህ ስራ የህወጥ ሰደተኞችንና ህገወጥ አዘዋዋሪዎችን ቀጣይ ስራ ለማዳናቀፍ  (ለማስቆም) የሚደረገውን ጥረት ኣካል መሆኑ ታውቋል።

ካርቱም ውስጥ ማእከሉ ያደረገው አንድ የሱዳን ሚድያ ማእከል ዘገባ ከሆነ ይህ ህገወጥ ስደተኞችና ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ሰዎችን ደብቀውበት በነበረው ስፍራ ይሆናል ምስራቃዊ ክፍል መሆኑ ነው። የሱዳን ሚድያ ማእከል ጨምሮ እንዳስታወቀው በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ ላይ ሌላ ሶስት ህገወጥ አዘዋዋሪዎችን ጨምሮ የማዳን ስራ እየተካሄደ መሆኑ አስታውቋል።

በየዓመቱ ከኤርትራና ከኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው ስደተኞች ወደ ሱዳን እንደሚሰደዱና ከሱዳንም ወደ ሌላ አገር (ወደ አውሮፓ) ለመጓዝ እንደሚጎርፉና ይህም በሊብያ በኩል ወደ አውሮፓ የሚደረግ የጀልባ ላይ ጉዞ በሜዲትራንያን በኩል አድርገው መሆኑ ታውቋል።

የተ.. የሰደተኞች ኤጀንሲ እንደዘገበው ከሆነ 10 በላይ ኤርትራዊያን ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የሁለቱም አገሮች ድንበር ባለፈው መስመከረም ወር ከተከፈተ ወዲህ እንደ ሸሹ ዘገባው ያመለክታል።

ህገወጥ አዘዋዋሪዎቹ ቡዱኖች በዚህ የሰደት ጉዞ ቀጠና የሚሰሩት የስደተኞችን ተጋላጭት በመጠቀም እንደሚሰሩ ታውቋል። አስቸጋሪው ጉዞ ሰደተኞቹን ጠቀም ያለ ገንዘብ እንደሚያስከፍሉዋቸው ታውቋል። በአብዛኛው ስደተኞቹ በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ቡዱኖችና ሌሎች ወረበሎች የተለያዩ ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸው ታውቋል።

ነገር ግን የሱዳን መንግስት እነዚህ ህገወጥ አዘዋዋሪዎችንና ህገወጥ ሰደተኞችን እያከለከለ መሆነየ ታውቋል። የሱዳን መንግስት ከጎረቤት አገር ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ጥብቅ የሆነ ህግ በማውጣትና አስፈላጊ ያልሆነ ወደ አውሮፓ አገሮች ጉዞ ለማስቀረት የድንበር የደህንነት ስራዎች ላይ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

የነዚህ ህገወጥ አዘዋዋሪዎችን ስራ ለማኮላሸት የሱዳን የደህንነት ሰራተኞች (ሃይሎች) በፖርት ሱዳን ካርቱም አምዱርማንና ከሰላ ከተሞች ላይ እየሰሩ መሆናቸው ታውቋል።

በዚህ የአሰራር ስራ በህዳር 18/2018 / .. በህገወጥ አዘዋዋሪዎች እጅ ተይዘው የነበሩትን 84 የኤርትራ ሰደተኞችን እንዳዳነ አሰታውቋል።

TMP – 24/12/2018

ፎቶ: የሱዳን ትሪቡን . የአፍሪቃ ህገወጥ ስደተኞችን የሱዳንና የሊብያ ድንበር ሲሻገሩ

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ