ኢትዮጵያ በሰው ሀይል ስደት ዙርያ ከፍሊፕኒስ ትምህርት እየወሰደች ነው

የኢትዮጵያ ከፍተኛ የባለስልጣናት ልኡካን ቡድን ወደ ፊልፕንስ በመጓዝ የሀገሪቱ የሰው ሀይል ስደት ምን እንደሚመስል ትምህርት ወስደዋል።  

ልኡካን ቡድኑ የፊሊፕንስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የጎበኘው ፌቡራሪ 27 ላይ ነው።   ስድስት ቀን በፈጀው የፊሊፕንስ ቆይታ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልኡካን ቡድን የፊሊፕኒስን የሰው ሀይል አሰራር እና የስደት  ጉዳይ አያያዝ ዙርያ ትምህርት ቀስመዋል። ተመኩሮም ወስደዋል።    

የፊፕኒስ የስደተኞች ጉዳይ የሚጠቀምበት አሰራር የስደተኞች መብት በመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። ይህ አሰራር ከኢትዮጵያ ለሄደ የልኡካን ቡድን   ቀርቦላቸዋል። ይህ ብቻ ሳይሆን በስራ እና ሰራተኞች ኤጀንሲዎች የሚደረግ መልካም የሚባል የስራ ማገናኘት አሰራር እንዲሁም ስርዓተ ፆታን በተሻለ መንገድ እንዲሰራበት ታሳቢ ያደረገ አሰራር ለልኡካን ቡድኑ  ቀርቦላቸዋል።

የሁለቱም ሀገራት ተወካዮች በስደት ስላሉ ሰዎችና ስራዎቻቸው ዙርያ ውይይት አድርጓል። የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በስደት ስላሉ ሰዎችና የሚሰሩዋቸው ሰራዎች ዙርያ ከፊልፕኒስ በቀጣይነት ልምድ ለመውሰድ ያለው ፍላጎት ገልፀዋል። ሁለቱም ሀገራት እያንዳንዳቸው ወደ 105 ሚልዮን የሚጠጋ የህዝብ ብዛት ያላቸው ሲሆን በሚልዮኖች የሚቆጠር ህዝብ በስደት ይኖራሉ።     

ፊልፕኒስ ዜጎችዋ በሌላ ሀገር ልካ በማሰራት ከአለማችን መሪ የምያደርጋት ደረጃ ያላት ሀገር ነች። እንደ ሀገሪቱ መንግስት ገለፃ ከሆነ ከ2.3 ሚልዮን በላይ ፊልፕኒሳውያን በውጭ ሀገራት ይሰራሉ።  አብዛኛው ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ የሚሰራ ፊሊፕኒሳዊ ህጋዊ በሆነና የሀገሪቱ መንግስት ባቋቋማቸው ኤጀንሲዎች በኩል የሚሄድ ነው። ህገ ወጥ ስደት በፊሊፕኒስ ሀገር ውስጥ እምብዛም አይደለም።  

ስደት በኢትዮጵያ በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ትልቅ አጀንዳ እየሆነ መጥተዋል።  በሰዎች ላይ እየደረሰ ባለ የሰው ልጅ ንግድ፣ የመብት ጥሰት፣ ሞት እና እንግልት ምክንያት ሀገሪቱ በ2013 ላይ ፀረ ህገ ወጥ ስደት አሰራር አውጥታ አውጃለች።

በመካከለኛ ምብራቅ ሀገራት ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሁሉም ህጋዊ አይደሉም። አብዛኛዎቹ ፓስፖርትና የመኖርያ ቪዛ የላቸውም። በህገወጥ መንገድ ቀይባህር በማቋረጥ በሰውዲ አረብያ በመሳሰሉ ሀገራት ውስጥ ስራ ፍለጋ   በጁቡቲ አድርገው ወደ  የመን  የሚሄዱ ናቸው።  

በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የነዳጅ ሀብት በተቸራቸው የአረብ ሀገራት ሳይደርሱ በመንገድ ይሞታሉ፤ የመን ላይ ባለ የእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ሰለባ ይሆናሉ። የቅርቡ መጥፎ ታሪክ እንኳን ካየን በምስራቃዊ የጅቡቲ ወደብ አከባቢ ባጋጠመ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ምክንያት የ52 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉ ይታወሳል።   

የፈለጉት ሀገር የደረሱ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስፈላጊውን የሰነድ ግብአት ስለሌላቸው   እንግልትና የመብት ጥሰት ይደርስባቸዋል። ወደ ሀገራቸው በፈቃዳቸው ሲመለሱ ወይም ተይዘው እንዲሄዱ ሲደረጉም ባዶ እጃቸው ስለሆነ የሚመጡት ወደ ጭንቀት እና ስራ አልቦነት ይዳረጋሉ።

ኢትዮጵያ በ2018 አዲስ ህግ አውጥታ ነበር። ህጉ የስራና አሰሪ ኤጀንሲዎችን አሰራራቸው የሚያይና የሚገመግም ነው። አዳዲስ የስልጠና ማእከላት በመክፈት ሰዎች ወደ ስደት ከመሄዳቸው በፊት አስፈላጊውን ስልጠናና ክህሎት እንድይዙ የምያደርግ ነው። በተጨማሪም ስለ መሰረታዊ መብቶች እውቀት እንዲኖራቸው፣ የባህልና ስነ ምግባር እውቀት እንዲጨብጡ፣ የአረብኛ ቋንቋ ክህሎት እንዲኖራቸው የምያደርጉ ማእከላት ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ሀገሪቱ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ደረጃ የሚሰሩባቸው አምስት የአረብ ሀገራት ጋር ማለትም ከክዌት፣ ዮርዳኖስ፣ ኳታር፣ ከአዩናይት አረብ ኢመሬትስና ስዑዲ አረብያ ጋር በጋራ መስራት የምያስችል ስምምነት መፈረም ችላለች።  

TMP – 25/03/2019

ፎቶ: ስታንስሊቭ71/ሻተርስቶክ. ስደተኞች በዱባይ የኮንስትራክሽን ሳይት ውስጥ ሲሰሩ