የዩኒሴፍ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር በኢትዮጵያ ለሚገኙ ስደተኞች የትምህርት ዕድል እንድያገኙ ሁኔታዎች እንደተመቻቸላቸው ተናገሩ
የዩኒሴፍ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር የሆኑት የህንድ ፊልም ሴት ተዋናይ ፕሪያንካ ቾፕራ ጆናስ በኢትዮጵያ ባደረጉት የአንድ ሳምንት ጉቡኝት በህፃፅና አዲ ሓርሽ የስደተኛ ካምፖች ከሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ጋር ተገናኙ፡፡ የግብኙቱ ዓላማም ስደተኞች የሆኑትን ህፃናት/ ልጆች የትምህርት ዕድል ለማግኘት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመርዳት ነው፡፡
የበጎ ፍቃድ አምባሳደርዋ በካምፕ ውስጥና ውጭ የሚገኙትን ትምህርት ቤቶችና የጤና ማእከሎች እንዲሁም በኤርትራውያን ስደተኞችና የአከባቢው ማህበረሰብ የሚጠቀሙባቸው በመንግስት ስር በሚተዳደረው የአመጋገብ ሁኔታ ማጣርያ ማእከል ጉብኙት አካሄደዋል፡፡ “ኢትዮጵያ በስደተኞች ላይ ያላትን ግልፅ ፖሊሲ ሌሎች አገሮች ሊከተሉት የሚገባ ምሳሌ ነው” ሲሉ ቾፕራ ጆናስ ገልፀዋል፡፡
“ እኛ እንደግለሰብ ማህበረሰብና መንግስታት በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉትና ሰብአዊ ቀውሶችን ባጋጠሙ ግዜ በራችንን ክፍት በማድረግ በስደተኞች ላይ ያለንን ፖሊሲ ክፍት በማድረግ በአገራችን ጥገኝነት ለሚጠይቁ ሰዎች አስፈላጊውን ጥበቃ ማድረግ ያለብን መሆናችንን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወይም አንፀባራቂ ምሳሌአችን ናት” ሲሉ ቾፕራ ጆናስ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በቅርብ አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩትን ኤርትራውያን ስደተኞች ህይወታቸውን እንዲሻሻል ለማድረግ በአገር ውስጥ አማራጮች በመፍጠር በሕገ ወጥ መንገድ የሚደረጉቱን አደገኛ የስደት ጉዞዎች ለማስቀረት አስፈላጊውን እገዛ አድርጋለች፡፡
አገሪቱ በዚህ አመት ጥር ወር ስደተኞች የበለጡ መብቶች እንዲያገኙና የትምህርትና ከካምፖች ውጭ የመስራት ዕድል እንዲኖራቸው የሚያስችል ሕግ አፅደቃለች፡፡ በአሁኑ ግዜ 196,350 የሚሆኑ ስደተኞች ከ60,000 በላይ ህፃናትን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች መመዝገባቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅፈት ቤት በቅርቡ ባወጣው ዘገባ አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ስደተኞችን ለመቀላቀልና ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ለህብረተሰቡና ለአከባቢው ኢኮኖሚ አስፈላጊውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ አጠቃላይ የስደተኞች እቅድ ተግባር በሕዳር 2017 እ.ኤ.አ ተግባራዊ አድርጋለች፡፡
ለ55,000 ኤርትራውያን መኖርያ የሆነውን በሕፃፅና አዲ ሓርሽ ካምፖች ላይ ስለተደረገው የማቀላቀል አስፈላጊነት ያላቸውን አስተያየት ቾፕራ ጆናስ ገልፀዋል፡፡
“እነዚህ ካምፖች የሚገኙበት ቦታ ከጎረቤቶቻቸው ከኢትዮጵያ ማህበረሰብ በጣም ቅርብ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እንደ ስደተኞቹ ከድህነትና ከዉሱን የገቢ ምንጮች ጋር በመታገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ለሁለቱም ማህበረሰቦች እኩል ፕሮግራሞች በመኖራቸው ለእያንዳንዱ ህጻን ለመኖርና ለማደግ አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉም ልጆች እኩል የትምህርት ፣የምግብና የጤና አገልግሎት እንዲኖራቸው ያደርጋል” በማለት ቾፕራ ጆናሰ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ አብዛኛዎቹ ከኤርትራ፣ሶማልያና ደቡብ ሱዳን የሆኑትን ከ900,000 ስደተኞች በላይ ይገኙባታል፡፡ እንደተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ፅፈት ቤት ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በ2ኛ ደረጃ ስደተኞች በብዛት የሚገኙባት አገር ናት፡፡ በመስከረም 2018 እ.ኤ.አ በወጣው ዘገባ 175,000 ኤርትራውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡
TMP – 31/05/2019
ፎቶ፥ ፍሬዘር
ህጻጽ የስተኞች ካምፕ፡ ኢትዮጵያ
ፅሑፉን ያካፍሉ