የፈረንሳይ ፍርድቤት የህፃን ስደተኞች ዕድሜ የምያሳይ የአጥንት ምርመራ ተግባራዊ ማድረግን ፈቀደ

በፈረንሳይ ሀገር ያሉ ህፃን ስደተኞች ለህፃናት የሚሰጠውን የተለየ እንክብካቤ  እንድያገኙ አልያም እንዲነፈጉ የምያስችል የተለየ የአጥንት ዕድሜ ምርመራ በመምጣቱ ምክንያት ለሀገሪቱ ባለስልጣናት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል። ይህ ፈቃድ የተላለፈው ማርች 21 ቀን 2019 የሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ጉባኤ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው። 

የግራ እጅ ኤክስረይ ማሽኑ ለመጀመርያ ግዜ 1930ዎቹ እንደተፈለሰፈ የሚነገር ሲሆን አንድ ህፃን አጥንቱን በመመርመር ከዕድመ በታች መሆኑ እና አለመሆኑ ለመለየት የምያስችል ነው። 

ይሁን እንጂ ይሄንን አዲስ የምርመራ መሳርያ በተለይ በዕድሜ ላቅ ባሉ ልጆች ላይ ትክክለኛውን ዕድሜ በማሳየት ረገድ ክፍተቶች እንዳሉት እየተነገረ ነው። በእንደዚህ አይነት የዕድሜ ክልል ያሉ ህፃናት በመካከለኛ 18 ወራት እስከ ሶስተ አመት የዕድሜ መዛባት የምያሳይ ነው ተብለዋል። ይህ ማለት አንድ ዕድሜው 15 እንደሆነ የሚናገር ህፃን 18 ዕድሜውም  ሊሆን ይችላል፤ 12 ዕድሜውም ሊሆን ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም የስነ መአዛ እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ለአጥንት ዕድገት ወሳኝነት ስላላቸው ትክክለኛውን መረጃ ለማግኝት አደጋች ነው።

ይህ ጉዳይ ያጋጠመው አንድ ጋናዊ መሆኑ የሚገልፅ አዳማ  የሚባል ስደተኛ 2016 በፈረንሳይ በዚሁ መሳርያ ታይቶ ዕድሜው 15 መሆኑን ይነገረዋል። እሱ ግን  አልቀበልም ይላል። በስተመጨረሻም ልጆች ወደሚቆዩበት የእንክብካቤ ቦታ መወሰዱን ይታወሳል።  

ይሁንና ከአንድ አመት በኋላ  በደቡባዊ ምዕራብ የፈረንሳይ ክፍል የሚገኘው  የጂቪሊ ፍርድቤት ትልቅ ነው በሚል ከልዩ የእንክብካቤ ማእከል አባርሮታል። አዳማ ወደ ልዮን ፍርድቤት ይግባኝ ጠይቆ ክስ በማቅረቡ ምክንያት ፍርድቤት ጉዳዩን እንደገና አይቶታል። በመሆኑም ልጁ 20 እና 30 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወጣት መሆኑ ለማረጋገጥ ችለዋል።

በስደት ጉዞው ብዙ አስፈላጊ ሰነዶች ስለሚጠፉ ብዙ ስደተኞች የዕድሜአቸው ማረጋገጫ ሰነድ ይታጣል። በመሆኑም እንደዚህ አይነት ማሽን መጠቀም የግድ ይላል። ይሁንና የዚህ ማሽን የምርመራ ውጤት እንደ አንድ እና ዋና የዕድሜ ማሳወቅያ መንገድ መውሰድ ከባድ እየሆነ  መምጣቱ የህገ መንግስት ጉባኤው ገልፀዋል። የጉባኤው ባለስልጣናት ጨምረው እንደገለፁትተመርምሮ ዕድሜው ታውቆ ህፃን መሆኑን የተረጋገጠ ልጅ ሁሉም አይነት ጥቅሞች ያገኛል።ብለዋል። ጨምሮምየህፃናቱ ዕድሜ የሚለካው በማሽኑ አንለካም በማለታቸው ሊሆን አይችልም።

በፈረንሳይ ሀገር ውስጥ የሚገኙ ከዕድሜ በታች የሆኑ ህፃናት 2015 ከነበረ 6,000 ከሶስት አመት በኋላ 2018 ወደ 17,000 ማሻቀቡ ተነግረዋል። ከእነዚህ ልጆች አብዛኛዎቹ ያለ ምንም አይነት ሰነድ የሌላቸው ናቸው።   

ይህ አዲሱ የዕድሜ ማሳወቅያ ማሽን ሰነድ ሳይኖራቸው ለሚገቡት ስደተኞች መቆጣጠርያ ተብሎ በጥቅም ላይ እየዋለ ያለ  ቢሆንም አንዳንድ ልዩ እንክብካቤ የምያስፈልጋቸው ህፃናት በተለያዩ ምክንያቶች እንዲቀሩ እያደረገ በመሆኑ የሰብአዊ መብት ተሟጓቾች እየተቹት ነው።

TMP – 12/04/2019

ፎቶ: ገራርድ ቦቲኖ  /ሻተርስቶክ. የህፃን ስደተኞች መብት በማስመልከት የተካሄደ ሰለማዊ ሰልፍ፤ ማርሲሊፈረንሳይ፤ ሰፕተምበር 2018