ጣልያን ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል የምያስችል የተሽከርካሪ ድጋፍ ለቱንዝያ ሰጠች
የጣልያን መንግስት 50 የበረሀ ተሽከርካሪዎችን ለቱንዚያ ሰጠች። ይህ በሰሜናዊ የአፍሪካ ክፍል ለሚደረገው ህገ ወጥ ስደት ለመከላከል ታስቦ የተሰጠ ደጋፍ መሆኑ ተገልፀዋል።
እነዚህ 50 4×4 የበረሀ ተሽከርካሪዎች ከጣልያን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ለቱንዝያ ሀገራዊ ጥበቃ የተሰጠ ነው። ሀገራዊ ጥበቃ፡ በቱንዝያ ህገ ወጥ የሰው ልጅ ነጋዴዎች መያዝን ጨምሮ የሀገሪቱ አጠቃላይ የድንብር ፀጥታ የሚጠብቅ የመንግስት አካል ነው።
የጣልያን የሀገር ውስጥ ሚኒስትር “ድጋፉ እየተሰራ ላለው ስራ ለማመስገን ታስቦ ከአፍሪካ ፈንድ የተገኘ እና በፀጥታ እና ድህንነት ዙርያ ሁለቱም መንግስታት አብረው ለመስራት ባደረጉት ስምምነት መሰረት የተፈፀመ ነው።” ብለዋል።
የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ማቲው ሳሊቪኒ “በቅርቡም ሌሎች ተጨባጭ ድጋፎች ይኖራሉ። በአለም አቀፍ እቅድ ደረጃም ከቃላት ወደ ተግባር እየተሸጋገርን ነው።” ብለዋል። የጣልያን ኤምባሲ በቱንዝያ ነው ይህ ድጋፍ የሰጠው።
ባለፈው ኦክተበር ወር ላይ በሳሊቪኒ የተመራ የጣልያን ልኡካን ቡድን ወደ ቱንዝያ በመሄድ ሁለቱም ሀገራት ስደተኞች እንዳይገቡባቸው እና የባህር ላይ ጉዞ መቀነስ በሚቻልባቸው እቅዶች ላይ አብረው ለመስራት ተስማምተው ነበር። በጉብኝታቸው ጊዜ ቱንዝያ ህገ ወጥ ስደተኞች ላለማሳለፍ በምታደርገው ስራ ምትክ ጣልያን ኢኮኖምያዊ ድጋፍ ለመስጠት ተስማምተዋል።
በግዜው በተደረሰ ስምምነት መሰረት ጣልያን ሁለት ካተርስ የተባሉ ማሽኖች እና አራት ጀልባዎች በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ እንደምትሰጥ ገልፀው የነበረ ሲሆን ይህ የራዳር ሲስተም ስጦታ አንድ አካል እንደነበር ተገልፀዋል። በጊዜው ሳሊቪኒ ለቱንዝያ የፀጥታ አካላት ስልጠና ለመስጠት ያላት ፈቃደኝነት ገልፃ ነበር።
ጣልያን ተመሳሳይ ስምምነት በ2018 ከሊብያ ጋር ያደረገች ሲሆን በስምምነቱ መሰረት ጀልባዎች ሰጥታለች፤ ለፀጥታ ሀይልዋም ስልጠና እንድያገኙ አድርጋለች። በዚሁ ምትክ ደግሞ የሊብያ የፀጥታ አካላት ህገ ወጥ ስደተኞች በሀገርዋ መሬት አቋርጠው እንዳያልፉ አድርጋለች። በመሆኑም በ2018 ብቻ 15,000 ህገ ወጥ ስደተኞች መያዝ ችላለች።
TMP – 26/03/2019
ፎቶ: ስደተኞች በጣልያን ጎና አቅራብያ አከባቢ በድንኳኖች ተጠልለው ሲኖሩ ይታያል። ሻተርስቶክ)
ፅሑፉን ያካፍሉ