ሌሎች 42 ስደተኞችን በእንግሊዝ የጠረፍ ሀይሎች መያዛቸውን ተሰማ

መይ 11 ቀን የቅዳሜ እና እሁድ ቀናት ላይ በህገ ወጥ መንገድ ወደ እንግሊዝ ሃገር ለመግባት አስበው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 42 ስደተኞች የእንግልዝ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው አስታወቀ። ስደተኞቹ በወሰን ጠባቂ ፓትሮሎች ተይዘው ወደ የሚመለከታቸው የስደት ጉዳዮች ባለስልጣናት መወሰዳቸው ተገልፀዋል።  

እነዚህ ስደተኞች በድቡሊን ህጉ መሰረት ወደ ፈረንሳይ ወይም ደግሞ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ስደተኞቹ ኢራናውያን እና ኢራቃውያን ሊሆኑ እንደሚችሉ የተገመተ ሲሆን በሶስት ትናንሽ ጃልባዎች ወደ እንግሊዝ ሀገር በመግባት ላይ የነበሩ መሆናቸው ነው የተነገረው።

በድቡሊን ህግ መሰረት አንድ ወደ አውሮፓ ሀገር የገባ ስደተኛ አሳይለም መጠየቅ ያለበት መጀመርያ እግሩ በረገጠበት ሀገር መሆኑ ይደነግጋል።ድጋፍ የሚሹ ስደተኞች አሳይለም መጠየቅ ያለባቸው መጀመርያ እግራቸው በረገጡበት አውሮፓዊ ሀገር መሆኑ ተደንግጎ ያደረ ህግ ነው።ብለዋል የእንግልዝ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች /ቤት።

የድቡሊን ረጉሌሽን በአውሮፓ የሚኖር የህገ ወጥ ስደት ችግር ለመከላከል ታስቦ የወጣ እና የአሳይለም ጥየቃ ሂደት ወደ ስርዓት ለማስገባት ታስቦ የወጣ ህግ ነው።  በህጉ መሰረት አንድ ስደተኛ ወደ አውሮፓ ሲገባ አሳይለም የሚጠይቅበት ሀገር የመመረጥ መብት የለውም። መጀመርያ እግሩ የረገጠበት ሀገር ውስጥ ነው አሳይለም መጠየቅ ያለበት። ህጉ አዲስ ወደ አውሮፓ የሚገቡ ስደተኞችም መጀመርያ እግራቸው በረገጠበት ሀገር . የአሳይለም ጥያቄ ማቅረብ እንዳለባቸው ይገልፃል።

ዶቨር ኤምፒ ቻርሊ ኢልፊክ በፈረንሳይ እና እንግልዝ ሀገር አከባቢ አሁን ካለው ህግ ይበልጥ ጠበቅ ያለ ህግ እንደምያስፈልግ ይገልፃል። እሱ እንደሚለው የሙሉ ክብ ጥበቃ ያስፈልጋል። ይህ በማድረግስደተኞች በሰላም ወደ ፈረንሳይ ለመመለስ የምያስችል ዕድል ይፈጥራል።ብለዋል።

በህገ ወጥ የሰዎች ዙውውር ስራ ላይ የተሰማሩ ግለሰዎች  የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ ወሰን ከብሪክዝት በኋላ እንደሚዘጋ የሚገልፅ ሀሰተኛ ወሬ እየነዙ ያሉበት ሁኔታ ነው ያለው። የቢቢሲ ጋዜጠኛ ኢራናዊ መሰሎ ከህገ ወጥ ደላሎች ጋር በነበረው ግኑኙነት እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት በወጣችበት ቅፅበት ወደቡ በስርዓት ይዘጋልብለውኛል ብለዋል። ሁሉንም ወደ እስርቤት ይወስድዋቹኋልእንዳሉትም አክሎ ገልፀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እንግሊዝ ግን ከፈረንሳይ ጋር ያላትን የወሰን ትብብር ስራዎች ላይ እንደ ወትሮ በአቋማ ፀንታ እንደምትሰራ ገልፃለች።

በመካከላችን ያለ የመረጃ ልውውጥ በባሀር በኩል ከፈረንሳይ ወደ ባህር ጠረፎች የሚደረግ የስደተኞችን   ጉዞ በማገት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው። ይህ የጋራ ትብብር የባህር ላይ ስደት እና የተቀናጀ ወንጀል በማምከን ረገድ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ አብረን እንሰራለን።ብለዋል ሀላፊው።   

ከጃንዋሪ 2019 ጀምሮ እስካሁን 25 በላይ ህገ ወጥ ስደተኞች ከእንግሊዝ እና ሌላ የአውሮፓ አባል ሀገራት ወደ ፈረንሳይ ሊለመለሱ ችለዋል።

TMP – 25/05/2019

Photo credit: ዱንክለይ / ሻተርስቶክ

Photo caption: UK Border Force cutter HMC Valiant