የፈረንሳይ ፓርላማ የአሳይለም ጠያቂ ስደተኞች ጉዳይ የምያፋጥን ህግ አወጣ

ፎቶ: በሰሜናዊ ፓሪስ ወደ አንድ ሰብኣዊ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም ለመግባት በመጠባበቅ ላይ ያሉ የስደተኞች ቡድን

የፈረንሳይ ፓርላማ ኦገስት 1 ላይ ባካሄደው የፓርላማ ውሎ የአሳይለም ጠያቂ ስደተኞች ጉዳይ ለማፋጠን የምያስችል ህግ ማውጣቱ ተነግረዋል። ይህ ህግ አንድ ስደተኛ ፈረንሳይ ከገባ በኋላ በ120 ቀናት ውስጥ ጉዳዩ ይፈፀምለት የነበረው ወደ 90 ቀናት ዝቅ እንዲል የምያደርግ ነው።   

ፍራንስ24 እንደዘገበው ስደተኞች  በአሳይለም ጉዳይ ላይ ያላቸው አቤቱታ የምያቀርቡበት የነበረ 11 ወራት የሚፈጅ ጊዜ ወደ 6 ወር ዝቅ እንዲል የምያደርግ ህግ መሆኑ ገልፀዋል።  ይህ ህግ ተቀባይነት ያላገኙም ሆነ የተሰካላቸው ስደተኞች በጊዜ ወደየስራቸው እንዲገቡ የምያደርግ ነው ተብለዋል። በተጨማሪም መመለስ ያለባቸው ስደተኞች ከመመለሳቸው በፊት ይቆዩበት የነበረው 45 ቀናት በእጥፍ እንድያድግ በማድረግ 90 ቀናት እንዲቆዩ የምያዝዝ ነው።

አንዳንድ የፓርላማው አባላት ይሄንን ህግ ጠበቅ እንዲል ያላቸው አቋም የገለፁ ቢሆንም በተለይ ህፃናት ያሉዋቸው መመለስ ያለባቸው ስደተኞች ለአምስት ቀናት በስደተኛ መቆያ ማእከላት እንዲቆዩ ደንግገዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአውሮፓ የሰብአዊ መብት ኮርት ይሄንን ህፃናት ያሉዋቸው ስደተኞች ረጅም ጉዞ እየጠበቃቸው መሆኑ እና ወደ መጡበት እንዲመለሱ የማደረግ ስራ አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል።  

የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ገራርድ ኮሎምብ በፓርላማው ፊት እንደተናገሩትእኛ ለትክክለኛው የአሳይለም ሂደት ነው በራችን እየከፈትን ያለነው። ምንም የተደረገ ነገር የለም። ይህ የምያስፈልገው አንድ የአውሮፓ አባል ሀገር ፍራቻ ሲገጥመው ላይ ታች ከማለት አስቀድሞ ህግ ማስቀመጥ ይበጃል በሚል ነው።” ብለዋል።  

ቀድመውንም ስደተኞች በአውሮፓ ሀገራት የምያመጡት ቀውስ ለመቀነስ ፈረንሳይ እና ጣልያን የአሳይለም ሂደት የምያስፈፅም ማእከል   set up asylum processing) በአፍሪካ ለማቋቋም ሲመክሩ ቆይተዋል። ይህ የምያስፈልገውም “የሞት መንገዶች” ማለትም “voyages of death” በማለት የሚጠሩትን ሜዲትራንያን የማቋረጥ ጉዞ ለመግታት ነው።

የአሁኑ የአውሮፓ ህብረት የአሳይለም ህግ እንደሚለው ሀገራቱ ስደተኛ ሲመጣባቸው መጀመርያ ማድረግ ያለባቸው መቀበልን ነው። በዚህ ህግ ምክንያት ጣልያን እና ግሪክ በከፍተኛ ደረጃ የተጎዱ ሲሆን በስፔንም በቅርብ ወራት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስደተኞች ጭማሪ ( increased in Spain ) ታይተዋል።  

TMP – 14/08/2018