በሺዎች የሚቆጠሩ ጣልያናውያን ዘረኝነትን ለማውገዝ ሰለማዊ ሰልፍ ወጡ
ከ 200,000 በላይ ሰዎች የተሳተፉበት በሰሜናዊ የጣልያን ክፍል በሚላን ከተማ ማርች 2/2019 ዘረኝነትን ያወገዘ ሰለማዊ ሰልፍ ተደርጓል። ሰልፈኞቹ ራይት ዊንግ ፓርት እያወጣቸው ያለ ፖሊሲዎችን ፍራቻ የሚለቁ፣ ጥላቻ ያላቸውና ልዩነት የምያሰፉ ናቸው በሚል ነው የተካሄደው።
በመፎክሮቻቸው “ህዝብ ይቅደም” የሚሉ ሀሳቦች የተሰሙ ሲሆን ይሄም የብዙኋነት ድምፅ መከበር እንዳለበት የሚጠይቅ ሆኖ ተገኝተዋል። ሰልፉ የሚላን ጎደናዎችን በተለያዩ ከለሮች፣ ሙዚቃና ዳንሶች እንዲታጀቡ አድርጓል።
“እዚህ የተገኘነው የመቀበል መቻል መልካምነትና የብዙሀነት ውበት ምን ያህል ጥሩ ነገር እንደሆነ ለመግለፅ ነው” ብለዋል አንድ ሰልፈኛ ለዩሮ ኒውስ በሰጡት አስተያየት።
ሌላ ሰልፈኛ በበኩሉ “እኛ ፀረ የዘረኝነት እንቅስቃሴ ነን። ምክንያቱም ቤተሰቦቻችን የተለያየ ከለር እንዲኖራቸው የሆኑት መርጠውት አይደለም።”
“ጣልያን እና አውሮፓ ፖሊሲዎቻቸው መቀየር ይኖርባቸዋል። ህዝብ ማእከል ያደረገ አካሄድ ሊኖራቸው ይገባል።” ብለዋል ለጣልያኑ ሚድያ ራይ ቲቪ።
ቤፒ ሳላ የሚላን የሶሻል ዲሞክራት ፓርቲ ከንቲባ ናቸው። ሰልፉ እንደ አንድ ወሳኝ ሚና የሚጫወት እንቅስቃሴ ይገልፁታል።
የራይት ዊንግ ህዝበኛ ፓርቲ ሀላፊ የሆኑት ማቲው ሳሊቪኒ ማርች 2018 ላይ ተወዳድሮ በምርጫ ስልጣን ከያዘ ወዲህ ፀረ ህገ ወጥ ስደት የሆኑ ፖሊሲዎች አውጥተዋል። ማቲው ሳሊቪኒ በምርጫ ዘመቻው ጊዜ ወደ 400,000 የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ሀገር ቤታቸው ለመመለስ ቃል ገብተው ነበር።
በመሆኑም ወደ ስልጣን ከመጡበት ግዜ ጀምሮ ወደ ጣልያን የሚገቡ ጀልባዎች እንዲመለሱ አድርጓል። የሀገሪቱ የጠረፍ ጠባቂዎች በማተርያል እና በእውቀት እንዲታጠቁ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል። ይህ በማድረግ ብዙ ስደተኞች ወደ መጡበት የሊብያ በር እንዲመለሱ አድርጓል። ስለሆነም የሊብያ የጠረፍ ጠባቂዎች እንደገለፁት በ2018 በሜዲትራንያን ባህር ላይ 15 ሺ ስደተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ወደ ሊብያ መመለስ ትክክል አይደለም ብለው በምያምኑ የተባበሩት መንግስታት እና አጋሮቻቸው ውግዘት ሲደርሰው ቆይተዋል።
ሳሊቪኒ ግን አሁንም የመንግስታቸው አዲስ ፖሊሲ “የተሻለች ጣልያን” በመፍጠር በኩል የራሱ አወንታዊ ሚና እንደሚጫወት ነው የሚናገሩት። ባለፈው ሰፕቴምበር ወር የሆነ ስደተኛ ወንጀል ሲሰራ ከተገኘ በቀጥታ ወደ ሀገሩ የሚላክበት ህግ ማውጣቱ ይታወሳል።
TMP – 4/03/2019
ፎቶ ከሬዲት: ማይክ ዶታ / ሻተርስቶክ. የፀረ ዘረኝነት ሰለማዊ ሰልፍ በሚላን-ጣልያን
ፅሑፉን ያካፍሉ