ጣልያን ስደተኞችን ያለቤትና ከለላ የሚያስቀር አዲስ ህግ አወጣች

የጣልያን ፓርላማ ስደተኞችን ያለ ከለላና ቤት አልባ የሚያደርግ አዲስ የደህንነትና የውጭ አገር መውጫ ውሳኔ በማስተላለፉ በጣልያን የሚገኙ ስደተኞች ወደ በረንዳዎችና ጎደናዎች እየተወረወሩ (እየተጣሉ) መሆናቸው ታውቋል። ይህም የተወሰነው ህዳር 28/20018 / በማቴው ሳክቪኒ የአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ (ደህንነት ሚኒስቴር) የተሰየመው የሳልቪኒ ህግ በመባል የሚታወቅ (የሚል ቅፅል ስም የተሰጠው) ከፀደቀ በኋላ ነው።

የስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ታስቦ የወጣው ይህ አዲስ ህግ ከበድ ያሉ እርምጃዎች ማለት ህገወጥ የሆኑትና ያልተመዘገቡት የሰዎችን መጠልያ ማፈራረስ የስደተኞችን የእስር ጊዜ ማራዘም ወደ አገራቸው የማባረር ስራ ለመስራት ገንዘብ መመደብ የህገወጥ ወንጀል ዝርዝሮችን ማራዘምና የስደተኛው የማቆያ ጊዜ መቀልበስን የመሳሰሉት ይገኙበታል።

አዲሱ ህግ የስደተኞችን ተገን (ከለላ) ጥያቄ መስፈርቶችን የሚያሻሽል በስደተኛ መጠልያ ማእከል የሚቆዩበትን የሚወስን ይሆናል። ከሁን በኋላ ወላጅ አልባ ህፃናትና ለአለም አቀፍ መስፈርት የሚያሟላ ስደተኞች ብቻ በማቆያ  ስፍራዎች እንዲኖሩ ይደረጋል ተብሏል።

ይህንን አዲሱ ህግ መውጣቱን ተከትሎ ክሮቶን  የሚገኘው የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ 24 ስደተኞች ከማእከሉ እንዲወጡ (እንዲባረሩ) ተእዛዝ አስተላልፏል። ከማእከሉ ከተባረሩት ስደተኞች መካከል 5 ወር የሆነው ህፃን የያዙት ባልና ሚስት አንድ የአእምሮ ችግር ያለበት ወንድ ልጅ እና ሁለት የህገወጥ አዘዋዋሪዎች ሰለባ የሆኑት ሴቶች ይገኙበታል።

ናይጄራዊቷ ብሌሲንግ የተባለች 31 ዓመት ወጣት እንግሊዝ ኣገር ለሚገኘው የጋዜጣ ሪፖርተር ዘጋርድያን እንደገለፀችው ፖሊሶች መጥተው ከሁን በኋላ እዚህ መቆየት አትችሉም ሲሉን ጀሮየን ማመን አቃተኝ ትላለች። ንብረታችን (ጓዛችን) በሙሉ ወሰዱት (ቀሙን) አባረሩን ይህ ድርጊት የሚያናድድና የሚያሳዝን ነው፡፡ እኔ ህጋዊ የማቆያ ፍቃድ ኣለኝ፡፡ መጠልያ ላይኖረኝ ነው ማለት ነው፡፡  በጣም ሰግቻለሁ ስትል ትናገራለች።

የቀይ መስቀል ማህበር ከከተማው አስተዳደርና ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በመተባበር ከመጠለያው ለተባረሩት ስደተኞች ጊዝያዊ መጠለያ በመስጠት ጥረት አድርጓል፡፡  የአከባቢው የቀይ መስቀል ሃላፊ ክሮቶን ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይቶ ይህ ፍፁም እብደት ነው፣ እንዴት ረዳት የሌላቸውን ሰዎች ሜዳ ላይ ይጣላሉ ፡፡ ይህ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡ ሲል ፍራንቼስኮ ፓሪሲ ተናግሯል።

የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች (ፓተንዛ የሚገኙት) ባሲሊካያ ካሴርታ አከባቢ የሚገኙትም በቅርቡ ከማእከሎች ተባረዋል፡፡ በሚቀጥሉት ሳምንታትም በመቶዎች የሚቆጠሩ ተመሳሳይ እድል እንደሚጠብቃቸው ታውቋል።

የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኤጀንሲ ቃል አቀባይ ካርታሎ ሳሚ የተባለችው ስደተኞችን የማባረሩ ስራ በመቃወም እንዲህ ስትል ትገልፃለች። በዚህ አጭር ጊዜ ያልገባን ነገር ለምንድነው የመኖርያ ፈቃድ ያላቸውም ጭምር እንዲወጡ የሚያደርጉት ህጉ እኮ ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም ፡፡ ለምንድ ነው ውጡ የሚሏቸው ስትል ትጠይቃለች።

እስካሁን ድረስ እያየን ያለነው ነገር ለተጋላጭ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ለጣልያን ህብረተሰብም ባጠቃላይ ወደ ህገወጥ ስራ እየገባ ነው።

TMP – 14/12/2018

ፎቶ: ክሪስቲ ብሎኪን/ ሻተርስቶክ።  መስከረም 4/2018 / የአፈሪቃ ስደተኛ በበረንዳ ላይ ተጥሎ ይታያል።  

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ