የሴት ስደተኞች በሞሮኮ የደህንነት ሃይሎች የፆታ ጥቃትና እንግልት እንደሚገጥማቸው ተገለፀ

ከሰሃራ በታች ካሉት የአፍሪቃ ሃገራት የሚሰደዱ ሰዎች በተለይም ሴቶች በሞሮኮ የፀጥታ ሃይሎች ለተለያዩ ኣካላዊና ስነኣእምራዊ ጥቃቶችና እንግልት እንደሚጋለጡ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የሚድያ ኤጀንሲዎች ገልፀዋል፡፡

የሞሮኮ የሰብአዊ መብቶች ማህበር እና የስደተኞች ፀረዘረኝነት ተከላካይ (ተሟጋች) ድርጅት የተባሉ ሁለት የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች በስደተኞች ላይ የሚደርሱትን በደሎችና ብዝበዛዎች ሲሰንድ እንደቆየ ተገፀዋል:: እንደ ድርጅቱ ዘገባ ከሆነ ባለፉት ሃምሌና ነሃሰ ወራት 7,700 የሚሆኑ ስደተኞች የዚህ አደጋ ሰለባዎች እንደሆኑና ህገወጥ እስርና ማባረር እንደተፈፀመባቸው ታውቋል:: የሰለባዎቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ኢንግሊዝ አገር የሚገኘው ቴሌግራፍ የተባለ ጋዜጣ በህዳር ወር 2018 / .. ተከታታይ የሆኑ ዘገባዎች ማውጣቱና በተለይም የሴት ስደተኞች ያገኘው መረጃ ጠቅሶ ሴቶቹ የፍተሻ ኬላዎች፣ ድንበሮችን ለመሻገር ሴቶች ፆታዊ ግንኙነት እንዲፈፅሙ ይጠየቁ እንደነበር ገልፀዋል ሲል ዘግቧል ::

ኣንድ የካሜሮን ስደተኛ ሴት ለዘ ቴሌግራፍ እንደተናገረችውአንድ የፖሊስ አባል በጩቤ አስፈራርቶ እንደደፈራት ገልፃለች:: ይህም የሆነው በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ስደተኞቹ ታጉረውበት የነበረውን ታንጀየር የተባለች የወደብ ከተማ የእስር ቤት ድንገት በፖሊሶች በተወረረበት ጊዜ መሆኑ ገልፃለች :: ጩቤውን  መዞ የምጠይቅሽን ነገር ካላሟላሽ እንደምጎዳሽ እወቂ ብሎኛል ስትል ገልፃለች::

ወደ ጀልባ እንድትሳፈር ቢፈቅድላትም ጀልባዋ እንደተነሳች ወድያውኑ በጠረፍ (የባህር ጠረፍ) ጠባቂዎች እንደተያዘችና ጉዞዋ እንደተሰናከለም ማርገዝዋ ማወቅዋና ዋሽታ ከባለቤትዋ ገንዘብ እንደተቀበለች (ፅንሱን ለማስወረድ) ገልፃ በጉዘዋ ያጋጠሙዋትን ስቃይና እንግልት እንዲሁም ብቸኝነት በምሬት ስትገልፅ ይህ ሁሉ የደረሰበት ችግር በሏ ቤተቦችዋ ምንም ነገር እንደማያውቁ ገልፃለች::

በሷ የደረሰው ችግርና እንግልት ለሷ ብቻ እንዳልሆነ፤ በሞሮኮ የድህንነት ሃይሎችና የጠረፍ ባለስልጣናት ሁሌም የሚደረግ መሆኑም ትገልፃለች:: 28 ዓመት ወጣት የጊኒ ስደተኛም ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማትና ይህም በተመሳሳይ ጀልባ ተሳፍራ ከካሜሮን ለመሻገር ስትሞክር መሆኑ ገልፃ፤ 60 ከመቶ የሚሆኑ ሴት ስደተኞች በፖሊሶች እንደተደፈሩ ትናገራለች::

31 ዓመት ወጣት ሴኔጋላዊትም ጠረፉን ለመሻገር ስትሞክር ሁለት የሞሮኮ ፖሊሶች ጎርጎራት በተባለችው ከተማ እንደደፈርዋትና ይህም ድንበሩን ለመሻገር የተጠየቀችውን ገንዘብ መጠን መክፈል ባለመቻልዋ መሆኑ ገልፃለች::

ሞሮኮ ከአውሮጳ ህብረት 807 ሚልዮን ዩሮ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ ላለፉት አራት ዓመታት ስትጠቀም ለሚቀጥሉት ስደተኞችን ለማስቆምና ለመቆጣጠር 107 ሚልዮን ዩሮ ለማግኘት ሞሮኮ ከሰሃራ በታች ላሉት ሰደቶኞችን ለማስቆም ጠበቅ ያለ ቁጥጥር እያደረገች መሆኑና፤ በዚህ ዓመትም የሃገሪቱ ባህር ሃይል ወደ 70,000 ህገወጥ ስደተኞች እንደያዘና እንዳስቆመ እንዲሁም ወደ 120 ህገወጥ የአዘዋዋሪዎች መረብ እንደበጣጠሰ ታውቋል::

በዚህ ዓመት መሰከረም ወር የአውሮጳ ህብረት መሪዎች ከምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ቱኒዝያ ግብፅና ሊቢያን ጨምሮ የጠረፍ ጥበቃና ቁጥጥር ስምምነት ማድረጉ ይታወቃል:: በሊቢያ ያለዉን ሁኔታ በመጠቀም የምዕራብ ሜዲትራንያን የባህር ጉዞ ከሞሮኮ ወደ ስፔይን ከዛም ወደ አውሮጳ ለመሻገር በህገወጥ ስደተኞች ተመራጭ ቀጠና እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል::

ሞሮኮ በታህሳስ ወር 2018 / የሚደረገውን ኮንፈረንስ እንደምታስተናግድ ኮንፈረንሱንም የዓለም ሃገራት የአለም ስደተኞችን ደህንነትና ህጋዊ ስደትን ለማበረታታት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል:: ከአውሮጳ ህብረት ብዙ ሃገራት ዩኤስ አሜሪካና አውስትራልያም ስምምነቱን ከማይደግፉ  ሃገራት (ከማይፈርሙት መሆናቸው) ታውቋል::

ፎቶ ዋለን/ ቴሌግራፍ የስደተኞች ማእከል ሞሮኮ ኦጅዳ አጠገብ የሚገኘው

ስለ ስደት ማወቅ የምትፈልጉት ማነኛውም አይነት ጥያቄ በኢመይል አድራሻችን ልታገኙን ትችላላችሁ።

ጥያቄዎቻችሁ በኢመይል አድራሻችን ላኩልን። ባልደረቦቻችን በፍጥነት ይመልሱላቹኋል። ሁሉም የኢመይል መልእክት
ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው።

ስደት አስበዋል? ለምክር አገልግሎት ይደውሉልን


ፈረንሳይ ውስጥ ከሆኑ

ዓለም እየተጓዘ ነው

ዓለማችን በጉዞ ላይ ነው ያለችው። በሚልዮን የሚቆጠሩ ሕዝብ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የስደት መከራ እየደረሰባቸው ይገኛል።

የስደት መረጃ፣ ከምንጩ፡ ከመዳረሻና መሸጋገሪያ መንግስታት እስከ ሕገ ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች፣ መገናኛ ብዙሀን፣ ምሁራን እና የስደተኞች የመረጃ ሰንሰለት በተለያዩ ለስደተኞች የማያግዙ ዓላማዋች የተሞላ ነዉ።

ተጨማሪ ያንብቡ