ፈረንሳይ አዲስ የስደተኞችን ህግ አፀደቀች

በሚያዝያ 22 እ.ኤ.አ የፈረንሳይ ብሄራዊ ምክር ቤት ስደተኞች የመጠግያ ጥያቄአቸውን የምያፋጥን፣ ወደ መጡበት የሚመለሱ ከሆነም ይሄኑኑ የምያፋጥን እንዲሁም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ፈረንሳይ በሚገቡ ስደተኞችን የአንድ አመት እስራት እንዲቀጡ የምያደርግ አዲስ ህግ አፅድቃለች።

የህጉ ሰነድ ከሁለት ሳምንታት በፊት ሲታይና ሲጠና ቆይቶ በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካኝነት ሊፀድቅ ቀርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ህግ የምንቀበላቸው ስደተኞች በስርዓት እና በአግባቡ ለመቀበል እንዲሁም ፈረንሳይ ላይ መቆየት የማይገባቸው ደግሞ ተሎ ወደ መጡበት እንዲመለሱ የምያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

የህጉ አንድ ዐላማ መጠግያ (asylum) ጠይቀው ተቀባይነት ያላገኙ ህገ ወጥ ስደተኞች በፈረንሳይ የስደተኞች ካምፖች ላይ እስከ 135 ቀናት ብቻ እንዲቆዩ ማድረግ ነው።

ሌላ ዐለማው ደግሞ አንድ ስደተኛ የመጠቅያ ጥያቄ የምያቀርብበት ፈረንሳይ ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት ባሉ 120 ቀናት ውስጥ የነበረውን ወደ 90 ቀናት ዝቅ እንዲል ማድረግ ነው።

በአዲስ ህግ መሰረት ተቀባይነት ያላገኙ ስደተኞች ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄ የምያቀርቡበት መንገድ ይከለክላል። እናም በ15 ቀናት ውስጥ ከፈረንሳይ እንዲወጡ ያዝዛል። ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ከወሰኑም የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸው ይሸኛሉ።

የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ገራድ ኮሎምብ እንዳሉት ይሄንን ህግ ያስፈለገበት ምክንያት “ለተሻለ የስደተኞች የቁጥጥር ስርዐት” ሲባል ነው። በመሆኑም ይህ ህግ ስደተኞች ፈረንሳይ ላይ የሚቆዩበት ጊዜ በመገደብ፣ 6 ወር ሲፈጅ የነበረውን የመጠግያ ጥያቄ ለመቀነስ እንዲሁም “የቁጠባ ስደተኞች” የሚባሉትን ተሎ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ያስችላል ተብለዋል።

የግራ ሀይሎች ይሄንን ህግ በተለይ ደግሞ መጠግያ ጠያቂዎቹ ጥያቄአቸው የምያቀርቡበት ጊዜ ከአራት ሳምንት ወደ ሁለት ሳምንት ማውረዱ ተገቢ አይደለም ሲሉ ይከራከራሉ። እንደምክንያት የምያስቀምጡት ደግሞ ስደተኞቹ ምክንያታቸው የምያስረዱበት ጊዜ ያጥራቸዋል የሚል ነው።

የሰብአዊ መብት ጠባቂ (Human Rights Watch) እንዳለውም ይህ የጊዜ ገደብ በተለይ ደግሞ በጣም ተጠቂነት ከሚበዛባቸው ሀገራት ለሚመጡ ስደተኞች ይጎዳል ሲሉ ተችተዋል፤ “በጣም ተጋላጭነት ያላቸው ስደተኞች የጊዜ ገደቡ ሊያልፍባቸው ይችላል።” በማለት።

ፈረንሳይ ባለፈው ዐመት ብቻ 100,000 መጠግያ ጥያቄ ያቀረቡ ስደተኞች በመያዝ ክብረ ወሰን ይዛለች። ይህ ሪኮርድ የምያሳየው ላለፉት ተከታታይ ዐመታት የሌላ አውሮፓውያን ሀገራት የስደተኞች ብዛት እየቀነሰ በመጣበት ወቅትም የፈረንሳይ እያደገ መምጣቱን ነው። ስለዚህ የዚህ አዲስ ህግ መፅደቅ የሚደገፉ ሌሎች ሀይሎችም ተባርከተዋል።

ኤምፒ የህግ ሰነዱ ለውይይት ባቀረበበት ወቅት ከ100 በላይ ጦማርያን ከግራም ከቀኝም ተሳትፈው ድምፃቸው አሰምተዋል። እነዚህ በዋነኝነት የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ ከጣልያን፣ ሃንጋሪ፣ ዳን፣ አውስትራልያ፣ እንግሊዝ እና ጀርመን የተውጣጡ ተሟጓቾችም ነበሩ። እነዚህ አካላት ስደተኞች የሚገቡባቸው ጫፎች ላይ በተለይም በጣልያን አልፕስ አከባቢ የቁጥጥር ስርዐት እንዲዘረጋ ተነጋግረዋል።

ጦማርያኑ ጠንካራ አቋም በመያዝ “አውሮፓን እንታደግ” የሚሉ ፅሁፎች የያዙ ባነሮች ለጥፈው ተከራክረዋል። በጣልያን አዋሳኝ ቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ተራሮች በእንግልዝኛ “Border closed. You will not make Europe home. No way. Back to your homeland.” የሚል ፅሁፎች ለጥፈዋል። ትርጉምም “ድምበር ተዘግተዋል። አውሮፓን ቤታችሁ ማድረግ አትችሉም፤ በፍፁም! ወደ ሀገር ቤታችሁ ተመለሱ።”

 

ፎቶ፤ ቤት አልባ አፍሪካውያን ስድተኞች በአንድ የፈረንሳይ የስደተኞች ካምፕ አቅራብያ በመንገድ ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ያሳያል

 

TMP – 09/06/2018