ሌሎች 10 ስደተኞች እንግሊዝ የባህር ጠረፍ ላይ ተያዙ

በያዝነው የፈረንጆች አመት ፌብራሪ 14 ላይ በሁለት ቀላል ጀልባዎች የእንግሊዝ ጠረፍ ለማቋረጥ አስበው ሲጓዙ የነበሩ 10 ስደተኞች ተይዘዋል። እነዚህ ስደተኞች ወደ ፈረንሳይ አልያም ወደ ሌላ የአውሮፓ ህብረት አባል የሚመለሱ ናቸው። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ በዱብሊን ረጉሌሽን የተባለው ስምምነት መሰረት ስደተኞች አሳይለም መጠየቅ ያለባቸው መጀመርያ እግራቸው በረገጠበት ሀገር መሆኑን ተከትሎ ነው።  

የመጀመርያው  ጀልባ የተያዘችው ከጥዋቱ 2፡15 ሲሆን ወደ ዶቮር ወደብ አቅራብያ አከባቢ ነው፡ እንደ የእንግሊዝ ሀገር የውስጥ ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ። የኤችኤምሲ ታዛቢ ጉዳዩ እንድያየው ተደርጓል።

ወደ 4:30 ሲሆን ደግሞ ሁለተኛው ጀልባ መምጣቱን ተከትሎ በጠረፉ ፓትሮል ቨዝል ሊያዝ ችለዋል። ሁሉም ስደተኞች የስደተኞች ጉዳይ ሰዎች እንድያገኙዋቸው እና ቃለመጠይቅ እንዲደረግላቸው ተደርገዋል።   

የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊው “10 ስደተኞች ጤንነታቸው ብደህና ሁኔታ አግኝተናቸዋል። ዜግነታቸው በሚመለከት በሂደት የምናየው ይሆናል።”  በለዋል።

ሀላፊው  ቻርሊ ኢሊፊክ  “ባደረግነው ዘመቻ ምክንያት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ አጠቃላይ የስደተኞች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ቢሆንም እነዚህ አዳዲስ ሁነቶች ግን ለምን እንደታዛቢ ዝም ብለን በታዛቢነት እንደምናየው ግልጽ አይደለም።” ብለዋል።   

ለዚህ ነው ደግሞ  በፈረንሳይ የወደብ ጠረፎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የምያስፈልገው። ይህ በማድረግ የህገወጥ የሰው ንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ይቻላል።

ከኖቨምበር ወር ጀምሮ ይህ አደገኛው መንገድ የማቋረጥ ሁነት እየጨመረ መምጣቱ እና በዚህ ጊዜው ውስጥ ቢያንስ 300 የሚሆኑ ስደተኞች ከፈረንሳይ ወደ ደቡባዊ እንግሊዝ በሚሄዱበት ሰዓት በቁጥጥር ስር ሊዉሉ ችለዋል።  

እነዚህ ስደተኞች ከእንግሊዝ ወደ ፈረንሳይ እንዲመለሱ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተነግረዋል።   

ጽ/ቤቱ ጨምሮ የዱብሊን ረጉሌሽን በሚፈቅደው እና በተስማማበት መንገድ ስደተኞችን የመመለስ ጉዳይ በተቻለ ፍጥነት ለማከናወን እየተሰራ ነው።” ብለዋል። አክሎም “ እንግሊዝ ከ ፈረንሳይ እና ከሌሎች የህብረቱ አባላት ጋር በመሆን በትናንሽ ጀልባዎች የሚመጡትን ስደተኞች በመያዝ አደገኛው የማቋረጥ መንገድ ነጻ እንዲሆን እንሰራለን።” ብለዋል።

TMP – 23/02/2019

ፎቶ: የእንግሊዝ የጠረፍ ሀይልና ብሄራዊ የወንጀል ቁጥጥር ኤጀንሲ ቀላል ጀልባዎቹ ሲፈትሽ፡ 31 ደሰምበር 2018   

ክሬዲት: ሱሳን ፒልቸር/ሸተርስቶክShutterstock