የእንግሊዝ መንግስት በጀልባ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ስደተኞች እየመለሰ ነው፤ ህጋዊ ያልሆነውን ጉዞ ድጋፍ በማድረግ የተጠረጠረ ግለሰብ ሊቀጣ ነው።
በኬንት በኩል ወደ እንግሊዝ ሀገር በመግባት ላይ የነበሩ ሰላሳ ስድስት ስደተኞች በሀገሪቱ የወሰን ጥበቃ ሀይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ስደተኞቹ በዱብሊን ሬጉሌሽን መሰረት ወደ ፈረንሳይ እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የሚመለሱ ይሆናል።
አፕሪል 22 ቀን 2019 እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር 36 ስደተኞች አሳፍረው ሲሄዱ የነበሩ ሰስት ትናንሽ ጀልባዎች ናቸው በእንግሊዝ የወሰን ጥበቃ ሀይሎች ሊያዙ የቻሉት። ከተያዙ በኋላ ጉዳያቸው ሊታይ ወደ ዶቨር ተወስደዋል። ስደተኞቹ ዜግነታቸው ገና እየተጣራ ያለ ቢሆንም ኢራቃውያን አልያም ኢራናውያን ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚጠቁሙ ዘገባዎች እየወጡ ነው።
እነዚህ ስደተኞች ከሌሎች በተመሳሳይ ሁነት ላይ የተገኙ ስደተኞች በጋራ ወደ ፈረንሳይ ወይም ሌላ የህብረቱ አባል ሀገር ይመለሳሉ ተብለዋል። በሁሉም የአውሮፓ ህብረት ሀገራት የተፈረመውን የዱብሊን ሬጉሌሽን እንደሚለው አንድ ስደተኛ አሳይለምም ጥበቃም መጠየቅ ያለበት መጀመርያ እግሩ በረገጠበት ሀገር ላይ ነው።
“የቆየ አሰራር ነው። አንድ ስደተኛ ጥበቃም አሳይለምም መጠየቅ ያለበት መጀመርያ በገባበት የአውሮፓ ሀገር ነው። በመሆኑም ከጃንዋሪ ጀምሮ እስካሁን ከ 20 በላይ ስደተኞች በትናንሽ ጃልባዎች ወደ እንግሊዝ ሀገር የገቡ ስደተኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደርገዋል።” ብለዋል የእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ፅ/ቤት።
ፈረንሳይ የባዮሜትሪክ ዳታቸው ማናኛውም የህብረቱ አባል ሀገር የሞሉ ስደተኞች ለመቀበል ፈቃደኝነትዋ አሳይታለች። ባዮሜትሪክ ዳታ ማለት የህብረቱ አባላት ያወጡት ዩሮዶክ በመባል የሚታወቅ ሲስተም ሲሆን አንድ ስደተኛ ማመልከቻ ማስገባቱ እና አለማስገባቱ ወይም በህገ ወጥ መንገድ መግባት አለመግባቱ የምያሳይ የሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ ለመስጠት የምያግዝ ዳታ ያለበት ሲስተም ነው።
ከ2018 መጨረሻ አከባቢ ጀምሮ የእንግሊዝ ወሰን በመጣስ እየገበሩ ያሉ የህገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር ጭማሬ እያሳየ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ህገ ወጥ ደላሎች የተላለዩ ሴራዎች እየተጠቀሙ ነው። ለምሳሌ የወሰን አከባቢ የፀጥታ ጉዳዮች ያደፍረሳሉ። በመሆኑም እንግሊዝ ከፈረንሳይ ጋር ጥብቅ ትብብር በመመስረት ከአደገኛው የስደት ጉዞ ለመከላከል እየተሰራ ነው ተብለዋል።
በቅርቡ እንግሊዝ ሳርባስት ሞሃመድ ሃማ የተባለውን የ31 ዕድሜው ግለሰብ አደገኛውን ጉዞ በማስተባበር ለህገ ወጥ ስደት ምክንያት ሆነዋል በሚል ወደ ፍርድ አቅርባዋለች። የተነሳበት ጥርጣሬ 27 ስደተኞችን ወደ አደገኛው የስደት ጉዞ እንዲገቡ ምክንያት ሆነዋል በሚል ነው።
የመጀመርያው ሁነት ያጋጠመው በ2018 የገና በዓል ማለዳ ላይ ሲሆን አንድ ህፃን ያለበት 13 ስደተኞችን የተያዙበት ቀን ነው። ከእነዚህ ስደተኞች አንድም ሰው የአደጋ መከላከያ ልብስ ሳይዙ ነበር ሲጓዙ የነበሩት።
ተጠርጣሪው ማርች 27 ላይ የተያዘውን ስደተኞች ጭኖ ይሄድ የነበረውን ጀልባ ላይም የእሱ እጅ እንዳለበት ተነግረዋል። በግዜው የተያዙት ሰዎች ዘጠኝ ኢራቃውያን እና ሁለት ኤራናውያን ስደተኞቹ መሆናቸው ተነግረዋል። ይህ ቡድን አንድ ሴት እና ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተገልፀዋል። የተያዙትም ወደ እንግሊዝ ወሰን በሚወስድ ፎልክስቶን በተባለው አከባቢ መሆኑ ተነግረዋል።
ህገ ወጥ ደላሎች በሺዎች ዶላር የሚቆጠር የገንዘብ እና የአመታት የእስር ቅጣት ይጣልባቸዋል። ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ ፍርድቤቶች በህገ ወጥ ደላሎች ላይ ረጅም የእስር አመታት እየጣሉ ነው።
ሳርባስት ሞሃመድ ሃማ በተጠረጠረበት ወንጀል ወደ ፍርድቤት የቀረበ ሲሆን ለመይ 15 ቀን 2019 ቀጠሮ ተሰጥቶታል። የተጠረጠረበት ወንጀል ወንጀለኛ ሆኖ ከተገኘበት ህገ ወጥ ስደት በማገዝ በሚል ለረዘም ያሉ አመታት እንደሚታሰር ይጠበቃል።
TMP – 29/04/2019
Photo credit: ሱሳን ፒችለር / ሻተርስቶክ
Photo caption: የእንግሊዝ የወሰን ጥበቃ ሀይሎች በፊልክስቶን በኩል ወደ እንግሊዝ ሊገቡ የነበሩ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ፎልክስቶን–ኬንት–እንግሊዝ–ፌቡራሪ 24 ቀን 2019
ፅሑፉን ያካፍሉ